Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ ሆኑ

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ ሆኑ

ቀን:

ከቁጭት ለመድረኩ የሚያበቃ ሥራ ይቅደም

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና የ2018 ሴቶች የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫን ታስተናግዳለች፡፡ በማጣሪያው ከጫፍ ደርሶ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በአልጀሪያ አቻው ተሸንፎ ከጋናው የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆኗል፡፡ ቡድኑ በሜዳውም ከሜዳው ውጪም መሸነፉ ከቁጭት ይልቅ ለመድረኩ የሚያበቃ ሥራ እንደሚያስፈልግ አመላክቷል የሚሉ አሉ፡፡

በአሠልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ሲዘጋጁ የከረሙት ሉሲዎቹ ከ15 ቀን በፊት ወደ አልጀሪያ አምርተው 3 ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፉ መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሮ መመለሱ በሜዳው ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ የተሻለ ውጤት አስመዝግቦ የጋናውን የአፍሪካ ዋንጫ ትኬት ይቆርጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም፣ በተቃራኒው 3 ለ2 መሸነፉ ብዙ ሲባልለት የቆየው የሴትች እግር ኳስና የሉሲዎቹ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ማነጋገር ጀምሯል፡፡

ለውጤቱ መበላሸት ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚወስዱ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት እንስቷ የሉሲዎቹ ዋና አሠልጣኝ፣ በአልጀሪያ አቻቸው ቀድሞ የተቆጠሩባቸው ጎሎች አሁንም፣ ቡድናቸው ጎል ለማስቆጠር በነበረበት ጉጉት መልሶ ማጥቃትን የመጀመርያ ዕቅድ አድርገው ወደ ሜዳ የገቡት አልጀሪያውያን ያገኙትን አጋጣሚ በመጠቀም ጎል ሊያስቆጥሩ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም የሉሲዎቹ የጋና ተሳትፎ በአጭሩ ተቋጭቷል፡፡

የአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አዘዲን ቼ በበኩላቸው፣ ውጤቱ በዚህ መልክ ይቋጫል ብለው እንዳልጠበቁ ይሁንና ጨዋታውን በታክቲክም ሆነ በቴክኒክ ተቆጣጥረውት የነበሩት ተጨዋቾቻቸው ጣፋጩን ውጤት አስመግበው ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ መብቃታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱን አስመልክቶ አሠልጣኙ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የሜዳ ላይ እንቅስቃሴያቸው ኳስን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ምናልባትም እንደተጀመረ አካባቢ ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ቢጠቀሙ ኖሮ ውጤቱ በተቃራኒው ለመሆኑ የሚያጠያይቅ አልነበረም፡፡ ይሁንና ለሰሜን አፍሪካውያኑ አስቸጋሪ የነበረውን የአዲስ አበባን የአየር ፀባይ ተቋቁመው ጨዋታውን በተረጋጋ መልሶ ማጥቃት ላይ በመመስረት ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የእኛ ተጨዋቾች ውጤቱን ቀልብሰውታል፤›› ብለዋል፡፡

 በአህጉራዊው መድረክ ከወንዶቹ ይልቅ የተሻለ የሚባል ተሳትፎ የነበራቸው ሉሲዎቹ፣ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ውጤታቸው እያሽቆለቆለ መሆኑን የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች፣ ሽንፈቱ በአጠቃላይ የሚያመላክተው እግር ኳሱ እየተጓዘበት ያለው መንገድ በፍፁም ትክክል አለመሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱን አስመልክቶ አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ‹‹ብዙዎቻችን ብሔራዊ ቡድናችን ሽንፈት ባጋጠመው ቁጥር ከአንድ ሳምንት የማያልፍ ቁጭት ካልሆነ ስፖርቱ ምን ይፈልጋል? እግር ኳሱ ከሙያተኛው አቅምና ከሚሰጠው ሥልጠና እስከ ላይኛው የአስተዳደር እርከን ያለው ከሌሎች አገሮች አኳያ እንዴት እየሄደ ነው?›› ተብሎ ሊፈተሽ እንደሚገባ ጭምር ይናገራሉ፡፡

በሌላ በኩልም የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ)፣ የግንቦት ወር የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ባደረገው መሠረት፣ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ውጤት አሽቆልቁሎ 151ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...