Sunday, June 16, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ደላላ ወዳጃቸው ይደውልላቸዋል

[ለክቡር ሚኒስትሩ የአጎታቸው ልጅ ስልክ ደወለላቸው]

 • ሄሎ ጋሼ፡፡
 • እንዴት ነህ ጎረምሳው?
 • በጣም ሰላም ነኝ ጋሼ፡፡
 • ዛሬ ከየት ተገኘህ?
 • ጋሼ እኔ እኮ ቤት ስመጣ አላገኝህም፡፡
 • ሥራዬን እያወቅከው ቤት ምን አደርጋለሁ ብለህ ነው?
 • እሱማ ቢዚ እንደሆንክ አውቃለሁ፡፡
 • ለመሆኑ ባለቤትህ እንዴት ሆነች?
 • የእሷን ነገር አታንሳው፡፡
 • የባለፈው ገንዘብ ደርሶሃል አይደል?
 • ደርሶኛል አመሠግናለሁ ጋሼ፡፡
 • ታዲያ ሆስፒታል አልወሰድካትም እንዴ?
 • ምን ሆስፒታል አለ ብለህ ነው ጋሼ?
 • ገንዘቡን ጠጥቼበት ጨረስኩት እንዳትለኝ?
 • ምነው ጋሼ ምን አጠፋሁ?
 • ምን ሆንክ?
 • ይኼን ያህል አረመኔ ነው ብለህ ታስባለህ?
 • ምንድነው የምታወራው?
 • ለሚስቴ መታከሚያ የሰጠኸኝን ገንዘብ ጠጣህበት ወይ ብለህ ስትጠይቀኝ አዝኜ ነዋ?
 • ታዲያ እዚህ አገር ምን ሆስፒታል አለ ስትለኝ ምን ላድርግ?
 • ጋሼ አንተ አለ ብለህ ታስባለህ?
 • እንዴ ስማ ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ በዓለም አቀፍ መድረክ ምን ያህል እንደምትወደስ ስለማታውቅ ነው፡፡
 • ጋሼ አንተ የሆስፒታሎቹን ችግር ለምን እንደማታውቅ እኔ ጠንቅቄ ነው የማውቀው፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ለመሆኑ ታመህ ታውቃለህ?
 • ምን?
 • ይቅርታ ለካ በየቀኑ ነው የሚያምህ፡፡
 • እኔ ጠፋሁ፡፡
 • ማለቴ ጋሼ ያው ደም ግፊትና ስኳር ስላለብህ ብዬ ነው፡፡
 • ቢኖርብኝስ ታዲያ ምን ይጠበስ?
 • አይ ጋሼ አንተ ቢያምህም ኢትዮጵያ ውስጥ ታክመህ ስለማታውቅ ነው፡፡
 • ምን ለማለት ፈልገህ ነው?
 • ያው ሁሌ ለቼክ አፕ ሳይቀር ውጭ ስለምትሄድ የአገሪቱን የጤና ዘርፍ ችግር በቅጡ አታውቀውም ብዬ ነው፡፡
 • የምን ችግር አለ?
 • ጋሼ ሰው ቶንሲል ታሞ በእግሩ ሄዶ በሳጥን የሚመለስበት አገር ውስጥ ሆስፒታል አለን ብለን መኩራራት ያስችለናል ብለህ ነው?
 • እና ሆስፒታል የለም እያልከኝ ነው?
 • በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ከዚያም አልፎ መድኃኒት ከጠፋ ሰነባበቷል፡፡
 • ለምን?
 • ይኸው ሚስቴ በመድኃኒት ዕጦት እየተሰቃየች ነው፡፡
 • ለካ በሰጠሁህ ገንዘብ አሳክመሃት ነበር?
 • ጋሼ ብትታከምም በዶላር እጥረት ሳቢያ የታዘዘላትን መድኃኒት ማግኘት ተስኖኛል፡፡
 • ወይ ይኼ ዶላር?
 • አሁን ሕክምናውን ትቼ በየቀኑ የቤተ ክርስቲያንን ደጅ መጥናት ሆኗል ሥራዬ፡፡
 • እዚያ ዶላር አለ እንዴ?
 • ኧረ ፈጣሪዬን ለሚስቴ ጤና እንዲሰጣት ለመማፀን ነው፡፡
 • ታዲያ ምን ልርዳህ?
 • ዛሬ ሌላ ነገር ላስቸግርህ ነበር የደወልኩት፡፡
 • ሌላ ምን?
 • ጋሼ ኮንዶሚኒየም ደርሶኝ ብድር ፈልጌ ነበር፡፡
 • ሌላ ብድር?
 • አዎን ጋሼ፡፡
 • ስማ አንተ ልክ እንደ ኢትዮጵያ የብድር ጣሪያውን ስላለፍክ ማዕቀብ ጥዬብሃለሁ፡፡
 • የምን ማዕቀብ?
 • የብድር!

 [አንድ የቀድሞ ታጋይ ዊልቸሩን እየገፋ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባ]

 • ዛሬ እንዴት ትዝ አልኩህ?
 • ይተውኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምን ሆነሃል?
 • ከዚህ በላይ ምን ልሁን?
 • ምንድን ነው የሚያስለቅስህ?
 • ለምን አላለቅስ ክቡር ሚኒስትር?
 • እኮ ምን ሆነሃል?
 • ማንነቴ ሲሸጥ እንዴት አላለቅስ?
 • ማን ነው ማንነትህን የሸጠው?
 • እናንተ ናችኋ፡፡
 • ምንድነው የምታወራው?
 • ክቡር ሚኒስትር ከዚህ በኋላ ሁለት ዜግነት ያለው ሰው ሆኛለሁ፡፡
 • የምታወራው እየገባኝ አይደለም?
 • ክቡር ሚኒስትር ሁለት እግሮቼን በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት እንዳጣሁ ያውቃሉ አይደል?
 • አንተ እኮ የአገር ጀግና ነህ፡፡
 • አሁን ግን ማንነቴ ተሸጠ፡፡
 • ኧረ በፈጠረህ ዝም ብለህ አታልቅስ?
 • ይኸው ከወገብ በላይ ኢትዮጵያዊ ከወገብ በታች ኤርትራዊ ሆንኩ፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • ሁለቱ እግሮቼን እኮ ባድመ ነው ያጣሁዋቸው፡፡
 • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
 • ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን› ብለዋል አይደል እንዴ?
 • አዎን ብለዋል፡፡
 • ስለዚህ እግሮቼ ኤርትራ ሆኑ ማለት አይደል?
 • እ. . .
 • የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንቀበላለን አላላችሁም እንዴ?
 • ልክ ነው ብለናል፡፡
 • ስለዚህ በዚያ መሠረት ባድመ ለኤርትራ መሰጠቷ ነው እኮ?
 • ምን መሰለህ አሁን ከኤርትራ ጋር ያለን ፖሊሲ ምንም እየጠቀመን ስላልሆነ እኮ ነው?
 • ቢሆንስ ታዲያ ዝም ብሎ ይወሰናል እንዴ?
 • ውሳኔው እኮ በፊት ነው የተወሰነው፡፡
 • እኔ የምለው ኢሕአዴግ አሁን የወሰነውን ውሳኔ ነው?
 • አልገባኝም?
 • ቢያንስ ከሕዝብ ጋር ሳትወያዩ ዝም ብላችሁ ይኼንን ትልቅ ዕርምጃ እንዴት ትወስዳላችሁ?
 • ያው የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ሁሌም መቅደም ያለበት የሕዝብና የአገር ጥቅም ነው፡፡
 • እሱማ ልክ ነው፡፡
 • ስለዚህ ባድመን ከሰጣችሁ እኛም ሌላ እንጠብቃለን፡፡
 • ሌላ ምን?
 • በባድመ ፈንታ የምንፈልገው ቦታ አለ፡፡
 • የቱን ቦታ?
 • አሰብን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • የሰሞኑ የመንግሥት ውሳኔ በጣም ነው የገረመኝ፡፡
 • የትኛው ውሳኔ?
 • መቼም ቢሆን እነ ቴሌን ፕራይቬታይዝ ታደርጓችዋላችሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር?
 • ስሚ አገሪቱ እኮ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ውስጥ ናት ያለችው፡፡
 • ቢሆንም ልማታዊ መንግሥት የሚኮራባቸውን ድርጅቶች ይሸጣቸዋል ብዬ አስቤ ስላማላውቅ ነው፡፡
 • ምን እናድርግ አገሪቷ ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ ጠፋ እኮ?
 • ለዚያ ነው የቤት ዕቃ እያወጣችሁ መሸጥ የጀመራችሁት?
 • ነገርኩሽ እኮ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ነው ያለው፡፡
 • ከምትሸጡ ግን ለምን አትበደሩም?
 • የሚያበድረንም ጠፋ፡፡
 • ለነገሩ ይኼ ለእኛ ምርጥ አጋጣሚ ነው፡፡
 • እንዴት?
 • ሁሌ የምነግርህን ስማ የምልህ ለዚህ ነበር፡፡
 • ምን እያልሽኝ ነው?
 • ያን ሁሉ የዘረፍነውን ገንዘብ በዶላር መቀየራችን ጥቅሙ አሁን ነው፡፡
 • ምን አስበሽ ነው?
 • አሁን እንደ እኛ አትራፊ ሰው አይኖርም፡፡
 • እ. . .
 • ብሩን ብቻ ታቅፈነው ቢሆን ኖሮ ገደል ገብተን ነበር፡፡
 • እኔማ ያኔ ከብላክ ማርኬት መቀየራችን ቆጭቶኝ ነበር፡፡
 • አሁን እጥፍ ነው የምናተርፈው፡፡
 • እንዴት አድርገን?
 • ለሽያጭ የሚቀርቡት ድርጅቶች እኮ እጅግ አትራፊዎች ናቸው፡፡
 • እሱማ ልክ ነው፡፡
 • ስለዚህ ወዲያው ነው የምንገዛው፡፡
 • ምኑን?
 • አክሲዮኑን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ደላላ ወዳጃቸው ይደውልላቸዋል]

 • ክቡር ሚኒስትር ምን ተሻለ?
 • ለምኑ?
 • ምንም መሥራት አልቻልንም እኮ፡፡
 • ምን ሆንክ ደግሞ?
 • አውሎ ንፋሱ ሥራ ሊያሠራን አልቻለም፡፡
 • የምን አውሎ ንፋስ?
 • ውጭ ያሉ ወዳጆቻችን ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ገብተዋል፡፡
 • በምኑ?
 • በአውሎ ንፋሱ፡፡
 • ኢትዮጵያ ውስጥ አውሎ ንፋስ ተነስቶ ነበር?
 • አገሪቱ ውስጥ የሉም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • ስማ እንኳን ኢትዮጵያ ዓለም ላይም ስለተነሳ አውሎ ንፋስ ምንም አልሰማሁም፡፡
 • ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዶዎታል ልበል?
 • የምን እንቅልፍ?
 • አውሎ ንፋሱ ያስነሳው ጎርፍ ሲወስድዎት ያኔ ይነቃሉ፡፡
 • ሰውዬ የምታወራው ነገር ግራ እያጋባኝ ነው፡፡
 • ምን ሆነዋል ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ሆንኩ?
 • አገሪቱ ውስጥ የሚነፍሰው የለውጥ አውሎ ንፋስ እየተሰማዎት አይደለም?
 • እሱን ነው እንዴ የምትለው?
 • ክቡር ሚኒስትር ፕሮጀክቶቻችን እኮ መና ሊቀሩ ይችላሉ፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • ይኸው ለውጡ ብዙ ነገሮችን እየቀያየረ ነው፡፡
 •  ታዲያ እኛ ምን አገባን?
 • ክቡር ሚኒስትር ነገሮች እንደ ድሮው ላይቀጥሉ ይችላሉ፡፡
 • የምትለው አልገባኝም?
 • ከፍተኛ ኮሚሽን የምናገኝባቸው ፕሮጀክቶች ላይሳኩ ይችላሉ፡፡
 • ለምን ተብሎ?
 • ይኸው የእኛ ወሳኝ ሰዎች እኮ እየተፐወዙ ነው፡፡
 • እ. . .
 • የውጭ ወዳጆቻችንም ደውለው ግራ ተጋብተናል እያሉኝ ነበር፡፡
 • ምንም ሥጋት አይግባችሁ በላቸው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ሁኔታውማ በጣም አሥጊ ነው፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • አለቃችሁ እኮ እየተጫወተባችሁ ነው፡፡
 • ምን?
 • ቀዩን ያዬ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...