Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና​መንግሥት በአገሪቱ የተከሰቱ ችግሮችን በውይይት እንዲፈታ ኢዴፓና ኢራፓ አሳሰቡ

​መንግሥት በአገሪቱ የተከሰቱ ችግሮችን በውይይት እንዲፈታ ኢዴፓና ኢራፓ አሳሰቡ

ቀን:

ኢዴፓና ኢራፓ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች እየተከሰተ ያለው ችግር ወደለየለት ቀውስ እንዳያመራ፣ መንግሥት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግልጽና ቀጥተኛ ውይይት በማድረግ መፍትሔ እንዲፈልግ ጠየቁ፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተከሰቱ ግጭቶችንና አለመረጋጋቶችን አስመልክቶ ሁለት መግለጫዎች ማውጣቱን ያስታወሰው ኢዴፓ፣ ችግሮች ከመሻሻል ይልቅ መባባስ እንደሚታይባቸው፣ ‹‹አገራችን ወደለየለት ቀውስ ውስጥ እንዳትገባ መከላከል የሁሉም ኃላፊነት ነው›› በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫው አስታውቋል፡፡

‹‹ከችግሩ መባባስ ጋር የመንግሥት የኃይል ዕርምጃ ተባብሶ የቀጠለ መሆኑ ሲታይ፣ መንግሥት ችግሮችን በተገቢው ጊዜና ሁኔታ በአግባቡ ለመፍታት የሚያስችል ትክክለኛ አቅጣጫ እየተከተለ አለመሆኑን ያሳያል፡፡ መንግሥት እየተከተለው ያለው ችግሩን በሀቀኛ ውይይትና መግባባት የመፍታት ሳይሆን፣ በኃይል ዕርምጃ የማፈን አቅጣጫ እንደማያዋጣ ተገንዝቦ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያስችል አቅጣጫ መከተል እንዳለበት ፓርቲያችን አበክሮ ያሳስባል፤›› ሲል የኢዴፓ መግለጫ ያትታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

 ‹‹በአንዳንድ ቦታዎች ላይ እንደታየው ዘርንና እምነትን አስታኮ የሚፈጸም ጥቃት ይህችን አገር ወደማያባራ ግጭት ውስጥ ሊከት የሚችል አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ኅብረተሰቡ፣ መንግሥት፣ የፖለቲካ ኃይሎችና የመገናኛ ብዙኃን በኅብረት ሊታገሉት ይገባል፤›› ሲልም ኢዴፓ አሳስቧል፡፡  

በተመሳሳይ በአገሪቱ ለተከሰቱ አለመግባባቶችና ግጭቶች መንግሥት አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት፣ ችግሩን በኃይል ሳይሆን በውይይት እንዲፈታ ኢራፓ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

‹‹ምክንያቱና መነሻው ምንም ይሁን ምን መንግሥት በኦሮሚያ፣ በአማራና በተቀሩትም የአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚጠቀማቸው ተመጣጣኝ ያልሆኑ የኃይል ዕርምጃዎችን በአስቸኳይ ያቁም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአሸባሪነት ከተፈረጁና አዋጅ ከወጣባቸው ኢትዮጵያውያን የትጥቅ ትግል ኃይሎች ጋር የግንኙነት መስመር ለመክፈት ይሞክር፡፡ አዋጁም በሌላ አዋጅ የሚሻሻልበትን መንገድ ያስብበት፤›› በማለት ኢራፓ በመግለጫው ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ቅርፀ ብዙ የአፀፋ ዕርምጃዎችንና ኃይልን መጠቀም በአማራጭነት ለመውሰድ በመነሳሳት፣ ከዴሞክራሲ መርህና ባህሪይ ውጪ የአምባገነንነት መገለጫዎችን በራሱ ሕዝብ ላይ ለማሳረፍ ከመንቀሳቀስ እንዲታቀብ ኢራፓ ጥሪ አድርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...