Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት በገንዘብ ድጋፍ ዕጦት መቸገራቸውን ገለጹ

​የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት በገንዘብ ድጋፍ ዕጦት መቸገራቸውን ገለጹ

ቀን:

በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ተቋማትና ማኅበራት የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ለማከናወን የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ እያጡ በመሆናቸው፣ አገልግሎታቸውን በተጠናከረ መንገድ ለመስጠት እንዳልቻሉ አስታወቁ፡፡

የበጎ አድራጎት ተቋማቱና ማኅበራቱ ይህን ያስታወቁት፣ የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት መድረክ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. አባላቱን እየተፈታተናቸው ስላለው የገቢ ዕጦት አስመልክቶ ለጋሽ አካላትና የመንግሥት ተወካዮች በተገኙበት በካሌብ ሆቴል በተካሄደ ዓውደ ጥናት ላይ ነው፡፡

‹‹የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 ሥራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ብዙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እየተቋቋሙ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ 4,000 የሚጠጉ ተቋማት ተፈጥረዋል፡፡ መፈጠራቸው በጎ ሆኖ ሳለ መንቀሳቀስ አቅቷቸው ወደ መዘጋት የሚሄዱ ተቋማትም ተስተውለዋል፡፡ ለተቋቋሙለት ዓላማና ለማገልገል ላሰቡት ኅብረተሰብ የሚፈልጉትን ድጋፍ ያገኙ እንዳልሆነ ተመልክተናል፤›› ሲሉ የመድረኩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ነጋሽ ተክሉ እየገጠማቸው ያለውን የገንዘብ እጥረት አስመልክቶ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለይ ይህ ችግር በክልሎች የራሱ ጠንካራ መገለጫዎች እንዳሉት ገልጸው፣ ‹‹ይበልጡን ደግሞ ኋላቀር በተባሉ እንደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ አፋርና በሶማሊ ክልሎች ችግሩ የባሰ ነው፡፡ በጣም በሚያሳስብ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡ ልንደርስለት ያሰብነው የኅብረተሰብ ክፍል በተለይም እንደ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ላይ ያተኮሩ ሥራዎችን ለመሥራት የሚፈለገውን ያህል ድጋፍ እየተገኘ አይደለም፤›› በማለትም ለችግሩ በአፋጣኝ መፍትሔ መፈለግ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

‹‹የተዘጉትም ሆነ ለመዘጋት በመንገድ ላይ ናቸው የምንላቸው ተቋማት ብቸኛው መንስዔ ገንዘብ ስላጡ ነው የሚል መደምደሚያ የለንም፡፡ የውስጣችንንም የውጪውንም ተፅዕኖ እንይ፡፡ ሁለቱን አስተሳስረን በምናይበት አቅጣጫ መሠረት ነው ይህን ስብሰባ የጠራነው፤›› ሲሉም የስብሰባውን ምክንያት አስረድተዋል፡፡

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሠረት ገብረ ማርያም በበኩላቸው፣ የሚባለውን ያህል የለጋሽ አካላት የገንዘብ ዕርዳታ አለመቀነሱን ጠቅሰው ችግሩ ከተቋማቱ የአቅም ውስንነት ጋር የተገናኘ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ብሩ አልቀነሰም፡፡ በመድረኩ የተገኙ ለጋሾችም ብር በየዓመቱ እየጨመረ መሄዱን እንጂ እየቀነሰ እንዳልሆነ መናገራቸውን ከመድረኩ አድምጠናል፡፡ ብቁ የሆኑና አቅም ያላቸውንና ሥራቸውን ውጤታማ የሚያደርጉትን እየመረጡ ነው፡፡ ከእነዚህ ከመረጧቸው ጋር እየሠሩ ነው፡፡ ነገር ግን አቅም የሌላቸውና የሚሠሩትን ወደ መሬትና ወደ ተገልጋዩ ማውረድ የማይችሉትን ዋስትና ሊሰጧቸው አይችሉም፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡   

አቶ መሠረት ገንዘቡን ይዞ ወደ ኅብረተሰቡ ወርዶ ውጤታማ ሥራ እሠራለሁ ለሚል ተቋም የተመቻቸ ሁኔታ እንዳለም አመልክተዋል፡፡

በዚሁ ጉዳይ ላይ የመድረኩ ሰብሳቢ አቶ ነጋሽ ሲናገሩ፣ ‹‹ገንዘብ አይገኝም የምንለው ራሳችንን ሳንፈትሽ አይደለም፡፡ በአፈጻጸም ረገድ ያለንን አቅም ውስንነት መፈተሽ እንዳለብን ተገንዝበናል፡፡ ምን ያህል ተቋማት ናቸው ከቆሙለት ዓላማ አንፃር አስተማማኝነትና ግልጽነት ፈጥረውና ተጠያቂነት አዳብረው ችግሩን ቀምሰው ሁኔታውን ለመወጣት እየሞከሩ ያሉት የሚለውን ጉዳይ ተመልክተናል፤›› በማለት ከአቅም ጋር የተያያዘ ችግር ቢኖርም ግን የገንዘብ እጥረቱ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

‹‹ቀጣይ አቅጣጫን በተመለከተ አጠቃላይ ችግሩ እንዳለ ተማምነናል፤›› በማለት የገለጹት አቶ ነጋሽ ከመንግሥት፣ ከለጋሽ አካላትና ከተቋማቱ ጋር የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ኅብረተሰቡን ለመጥቀም በሚያስችል መንገድ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት መድረክ የተመሠረተው በ2005 ዓ.ም. ሲሆን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ አስተዳደራዊ ዕውቅና ለማግኘት የቆመው ግብረ ኃይል ያከናውናቸው የነበሩትን ተግባራት በመተካት በሦስቱም ዘርፎች የሚገኙ ኅብረቶች፣ ጥምረቶች፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አማካይነት የተቋቋመ የጋራ መድረክ ነው፡፡

ይህ መድረክ ሦስቱንም ዘርፎች ማለትም ኢትዮጵያዊ፣ የኢትዮጵያ ነዋሪና የውጭ የሆኑ በጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ማኅበራትን የሚያስተባብር ነው፡፡ እነዚህ አካላት የሚገጥሙዋቸውን ተግዳሮቶች የሚቀርፉበትና መልካም ተሞክሮዎቻቸውን የሚያጎለብቱበት የጋራ መድረክ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...