የፊልም ምርቃት
ዝግጅት፡- ገነነ መኩሪያ የጻፈው ‹‹ኢሕአፓና ስፖርት››ን መነሻ በማድረግ የተሠራው ‹‹የነገን አልወልድም›› ፊልም ይመረቃል፡፡ አዘጋጁ አብርሃም ገዛኸኝ ሲሆን፣ ብርሃኑ ድጋፌ፣ ተስፋዬ ይማምና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡
ቀን፡- የካቲት 23 ቀን 2008 ዓ.ም.
ሰዓት፡- 10፡30
ቦታ፡- ኦሮሞ ባህል ማዕከል
አዘጋጅ፡- ፎርሞድ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን
የዳይሬክተሪ ምርቃት
ዝግጅት፡- ሀገር አቀፍ መረጃዎችና የሥራ ዘርፎችን በቅደም ተከተል የያዘ ብሔራዊ የመረጃ ዳይሬክተሪ በመጽሐፍ፣ በሲዲ፣ በድረ ገጽና በሞባይል አፕልኬሽን ይመረቃል
ቀን፡- የካቲት 24
ሰዓት፡- 12፡00
ቦታ፡- ሐርመኒ ሆቴል
አዘጋጅ፡- ዌብ ፕላኔት አይቲ ሶሉሽን
የሽልማት ፕሮግራም
ዝግጅት፡- ቶም የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ማሠልጠኛ ተቋም ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡ በዕለቱ በተማሪዎች የተሠሩ ፊልሞች በ7 ዘርፍ ተወዳድረው ‹‹ቶም አዋርድ›› በሚል ይሸለማሉ፡፡
ቀን፡- የካቲት 26
ሰዓት፡- 2፡30 – 6፡00
ቦታ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
አዘጋጅ፡- ቶም የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ማሠልጠኛ ተቋም
ፌስቲቫል
ዝግጅት፡- ‹‹ኑ እናንብብ 2›› በሚል የልጆች የንባብ፣ የባህልና የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል፡፡
ቀን፡- የካቲት 26 እና 27
ቦታ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማዕከል (ስብሰባ ማዕከል)
አዘጋጅ፡- አማራጭ ሚዲያና ኢንተርቴይመንትና ኢጋ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን
ኮንሰርት
ዝግጅት፡- ጃማይካዊው የሬጌ ዘፋኝ ጃ ኪዩር ኢትዮጵያ ውስጥ ሙዚቃዎቹን ያቀርባል
ቀን፡- የካቲት 26
ቦታ፡- ትሮፒካል ጋርደን
ሰዓት፡- 12፡00
አዘጋጅ፡- አፍሪካን ታይም