Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለም​ልዩነቶች ያጠሉበት የዘንድሮ ኦስካር ሽልማት

​ልዩነቶች ያጠሉበት የዘንድሮ ኦስካር ሽልማት

ቀን:

በሆሊውድ ዶልቢ ቴአትር የተካሄደው እ.ኤ.አ. የ2016ቱ 88ኛው አካዳሚ አዋርድ (ኦስካር) ሽልማት የቀለም ልዩነት ጐልቶ የወጣበትና ጥቁር ተዋንያን ራሳቸውን ያገለሉበት ሆኖ ተጠናቋል፡፡

እሑድ የካቲት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. የተካሄደው የኦስካር ሽልማት ብዝኃነት ይጐድለዋል፣ ፖለቲካ አጥልቶበታል ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎችና የፊልም ተዋናዮች ትችት ወርዶበታል፡፡

በምርጥ ፊልም፣ ዳይሬክተር፣ ተዋናይ፣ ተዋናይት፣ ተባባሪ ተዋናይ/ተዋናይት፣ ኦርጅናል ስክሪን ፕሌይ፣ አዳፕትድ ስክሪን ፕሌይ የሚሉትን ጨምሮ በ24 ዘርፎች በተካሄደው ውድድር፣ ዕጩ ተወዳዳሪዎቹም ሆኑ አሸናፊዎቹ በሙሉ ነጮች ሆነዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አሸናፊዎች

‹‹ስፖት ላይት›› እ.ኤ.አ. በ2015 ተሠርቶ በ2016 የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም ዘርፍ አሸናፊ የሆነ ፊልም ነው፡፡ በምርጥ ዳይሬክተርነት ዘርፍ ‹‹ዘ ሬቨናንት››ን ዳይሬክት ያደረገው አሊሃንድሮ ጐንዛሌዝ ሲያሸንፍ፣ በዚሁ ፊልም ላይ መሪ ተዋናይ ሆኖ የሠራው ሊዮናርዶ ዲ ካፕሪዮ የምርጥ ተዋናይ ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡

ካሪ ላርሰን ‹‹ሩም›› በሚለው ፊልም ምርጥ ተዋናይት ስትሆን፣ ማርክ ሬይላንስ ምርጥ ተባባሪ ተዋናይ በሚለው ተሸልሟል፡፡

‹‹ዘ ዳኒሽ ገርል›› ላይ የምትተውነው አሊሺያ ቪካንደር ምርጥ ተባባሪ ተዋናይት፣ እንዲሁም ፔት ዶክተር በምርጥ አኒሜትድ ፊቸር ፊልም ተባባሪ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በምርጥ የውጭ ቋንቋ ፊልም ዘርፍ ላስጊኦ ኒሚስ ሲያሸንፍ፣ ኢኒኦ ሞሪከን ደግሞ የምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ለውድድር ከቀረቡት ፊልሞች ‹‹ዘ ሬቨናንት›› በ12 ዘርፎች ተወዳድሮ ሦስት ሽልማቶችን፣ ‹‹ማድ ማክስ ፈሪ ሮድ›› በ10 ዘርፎች ተወዳድሮ ስድስት ሽልማቶችን፣ እንዲሁም ‹‹ስፖት ላይት›› በስድስት ዘርፎች ተወዳድሮ በሁለት ዘርፎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የ2016 የኦስካር ሽልማት ትችት

እስካሁን ከተካሄዱት የኦስካር ሽልማቶች እንደ 88ኛው ትችት የበዛበት እንደሌለ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ዩኤስ ዊክሊ እንደሚለው፣ የ88ኛው ኦስካር ውዝግብ ያጠላበት ነበር፡፡ በሁሉም ዋና ዋና የውድድር ዘርፎች የቀለም ልዩነት ጐልቶ ታይቶበታል፡፡ ይህም በአካዳሚው ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን ውዝግብ አስነስቷል፡፡ ውድድሩም የፆታ፣ የቀለም፣ የፆታዊ ግንኙነት ምርጫን ያላገናዘበ ነው በማለት ስፓይክ ሊ፣ ጄ ፒንኬት ስሚዝ፣ ዊል ስሚዝ እንዲሁም የዚህ ዓመት ምርጥ የማጀቢያ ሙዚቃ ዕጩ አኖኒ በሥነ ሥርዓቱ ከመካፈልም ሆነ የውድድሩ ተሳታፊ ከመሆን ራሳቸውን አግልለዋል፡፡

ማኅበራዊ ድረ ገጾች፣ ‹‹ኦስካር ኢዝ ፎር ዋይትስ›› የሚለውን የኮሜዲያንና የተዋናይ ክሪስ ሮክ ቀልድ አዘል አባባል በመድገም፣ የኦስካር ሽልማት በተለይ የዘንድሮው ዘርን መሠረት ያደረገና የዘር ፖለቲካ ያጠላበት እንደሆነ ያሳያሉ፡፡ ሚዲያውም ቢሆን የጥቁርና የነጭ ውዝግብ አድርጐ አቅርቦታል፡፡

ዕውቅ ተዋናዮችና የአካዳሚው አባላት ደግሞ የኦስካር ሽልማት በዘር ወይም በፆታ፣ በበላይና በበታች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በብቃት ላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አይስ ኪዩብ፣ ሁፒ ጐልድበርግ፣ ሚካኤል ኬንን የመሳሰሉ ዕውቅ የፊልም ባለሙያዎችና የአካዳሚው አባላት ተዋናዮች ጥቁር በመሆናቸው ሳይመረጡ ቀርተዋል የሚለውን እንደማይቀበሉት፣ ጥቁር ተዋናዮች ዕጩ እንዲሆኑ በግላቸው ካርዳቸውን የሰጡ እንዳሉም ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ በዘር ላይ መሠረት አድርጐ እየሠራ አይደለም ሲሉም ተሟግተዋል፡፡

የተቋማዊ ለውጥ ጥያቄ

አካዳሚው በኦስካር ሽልማት አካሄድ ላይ ተቋማዊ ለውጥ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ በፊልሙ ዘርፍ ያሉ አንዳንድ ተዋናዮች ይገልጻሉ፡፡

አንዳንዶች በ88ኛው አካዳሚ ሽልማት ላለመሳተፍ ራሳቸውን ሲያገሉ፣ ከዚህ ቀደም የኦስካር አሸናፊ የነበሩት ሪስ ዊዘርስፑንና ሉፒታ ንዮንግ ኦስካር ተቋማዊ ለውጥ ያስፈልገዋል በማለት ባለፈው ወር ውትወታ አድርገዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ አካዳሚው መልስ ሰጥቷል፡፡ የአካዳሚው ቦርድ በአካዳሚው አባልነት፣ በውሳኔ ሰጪ አካላትና የመምረጥ መብት ባላቸው አባላት ላይ መሠረታዊና ሁሉንም ሊያሳትፍ የሚችል ለውጥ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

እንደ ጆርጅ ክሎኒ፣ ደስቲን ሆፍማንና ሁፒ ጐልድበርግ ያሉ ዝነኞች ችግሩ ከአካዳሚው አቅም በላይ ነው ቢሉም፣ የአካዳሚው ቦርድ ሁሉንም ያማከለ አሠራር እንዲኖር ያስችላሉ ያላቸውን ነጥቦች አፅድቆ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል፡፡

የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ቼሪ ቦኔ አይዛክ በአስተዳደራዊና በምርጫ አካሄድ ላይ የተደረገው ለውጥ በአባላት ስብጥር ላይ በጐ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

አካዳሚው ‹‹የተሰባጠረ አባላት ማብዛት›› የሚለውን ግቡን እ.ኤ.አ. በ2020 ለመምታትም፣ አዳዲስ አባላት በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ እንዲሳተፉ፣ ሦስት ተጨማሪ የውሳኔ ሰጪ አካላት መቀመጫ እንዲጨመር ቦርዱ አፅድቋል፡፡ በተለይ አዳዲስ አባላት በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ለመካተት መቻላቸው፣ የሚሰጡ ውሳኔዎች ፍትሐዊ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

በነበሩት አሥርት ዓመታት ውስጥ የተለያዩ የዘር ሐረግ ያላቸውን ባለማካተት ኦስካር የፊልም ሽልማት ይተቻል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ወስጥ ደግሞ ጉዳዩ የባሰ ሆኗል፡፡ አምና ተሠርተው ዕውቅናና አድናቆት ከተቸራቸውና በጥቁሮች ሕይወት ላይ ከሚያጠነጥኑት እንደነ ‹‹ክሪድ›› እና ‹‹ስትሬይት አውታ ከምፕተን›› ያሉት ፊልሞች ኦስካር ዕውቅና ሳይሰጥ ዘሏቸዋል፡፡ በተለይም በጥቁር የፊልም ማኅበር ውስጥ ጥያቄ የተፈጠረውም በእነዚህ ፊልሞች ውስጥ ነጭ ተዋናዮች ማለትም ሲልቨር ስታሎን በ‹‹ክሪድ›› ፊልምና ነጭ ጸሐፊዎችን በ‹‹ስትሬይት አውታ ከምፕተን›› ፊልም የሽልማት ዕጩ በማድረጉ ነው፡፡ በእነዚህ ፊልሞች ላይ የተሳተፉት ጥቁር ፊልም ዳይሬክተሮችና ተዋናዮች የተዘለሉት ‹‹ሆን ተብሎ›› ነው በማለት ብዙዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ፊልሞች ቦክስ ኦፊስ አጣበው የከረሙ ነበሩና ነው፡፡

የዘንድሮው የኦስካር ሽልማት ከዚህ ችግር በተጨማሪ፣ በቴሌቪዥን የተመልካቾች ድርቅ መመታቱ ተገልጿል፡፡ ለእዚህ ምክንያቱ ደግሞ የዘር ልዩነት ያጠላበት የዘንድሮው ኦስካር ሽልማት ሥነ ሥርዓትን ብዙዎቹ በቴሌቪዥን ላለማየት በመወሰናቸው እንደሆነ የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

 

 

   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...