- 1 ኪሎ ዝኩኒ
- 3 ቲማቲም፣ በስሎ የተቆረጠ
- 2 መካከለኛ ሽንኩርት፣ የተከተፈ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
1. ዝኩኒ አጥቦ ሁለት ቦታ ከፍሎ ፍሬውን ማውጣት፡፡
2. የተቆረጠውን ዝኩኒ ቅባት የተቀባ መጋገሪያ ላይ ማድረግ፡፡
3. ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ቅቤ ቀላቅሎ በተራ ቁጥር 2 የተዘጋጀውን ዝኩኒ ጨምሮ መክደን፡፡
4. ሙቀቱ 350 ዲግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ለአርባ አምስት ደቂቃ ማብሰል፡፡
5. ከበሰለ በኋላ ሳህን ላይ ገልብጦ ትኩሱን ማቅረብ፡፡
- ከስድስት እስከ ስምንት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)