Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ብሔር ተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ገለጹ

የአማራ ብሔር ተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ገለጹ

ቀን:

ከኦሮሚያናቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ሕይወታቸውን እየገፉ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፣ በተለይም ከሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች መፈናቀላቸውን ይፋ ባደረገ በወራት ልዩነት መፈናቀሉ እንደገና አገርሽቷል፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ከጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን፣ ከኦሮሚያ ክልል ደግሞየካቲት ወር ጀመሩን ተፈናቃዮቹ ይናገራሉ፡፡

ሪፖርተር ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ ከሁለቱ ክልሎች የተፈናቀሉ 420 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ያገኘ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ በሁለት ቡድን ተከፍለው በአብያተ ክርስቲያናትና በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እየኖሩ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ተፈናቃዮች ውስጥ 135 ያህሉ ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በቅርብ ርቀት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በክልሉ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ግቢ ውስጥ በጊዜያዊ መጠለያነት አንድ ድንኳን ተሠርቶላቸው እየኖሩ ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካሉ ተፈናቃዮች መሀል ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ሲኖሩ፣ በዋናነት የቀይ መስቀል በሰጣቸው ሸራ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት ሥር በሚገኙ ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ሪፖርተር አይቷል፡፡

 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሼ ዞን የተፈናቀሉና በአሁኑ ጊዜ በቅዱስ ጊዮርጊስ በቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ የሁለት ልጆች አባት፣ ‹‹ከአማራ ክልል መንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ አላገኘንም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ከዚህም ብሶ ባለሥልጣናት ወደ እኛ መጥተው ሲያስፈራሩን ያለን አማራጭ የትውልድ ወረዳችን ቤተሰቦቻችን ዘንድ፣ ወይም ደግሞ ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ተመልሰን መሄድ ብቻ አንደሆነ በተለያየ ጊዜ ሲነግሩን ነበር፤›› ሲሉ ተፈናቃዩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

1997 ዓ.ም ጀምሮ እንደ አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጅ ተፈናቃዮች በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በግብርና እና በንግድ ተሰማርተው ይኖሩ እንደነበር የገለጹት እኚህ ተፈናቃይ፣ የመጀመሪያው ከጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ አንድ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ የጉምዝ ብሔር አባል የሆነ ወጣት በመገደሉ ሳቢያ በተከሰተው ግጭት፣አማራ ብሔር ተወላጆችንፈናቀል እንደተጀመረ ይናገራሉ፡፡ ከቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈናቀሉት ሰዎች ምስክርነት መሠረት ከ13 በላይ የአማራ ተወላጆች በበቀል ተገድለዋል፡፡

ስሙን መግለጽ ያልፈለገ በ20ዎቹ ዕድሜ መገባደጃ ላይ የሚገኝ ተፈናቃይ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ በንብረቶቻቸውናቤቶቻቸው ላይ ጥቃት ደርሷል፡፡ የፌዴራል የፀጥታ ኃይል ከገባ በኋላ በተወሰነ ደረጃ መረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር፣ ነገር ግን በወቅቱ በሥፍራው መቆየት አስተማማኝ ስላልነበር መፈናቀሉ እንደተከተለ ወጣቱ አስረድቷል፡፡

ተፈናቃዮቹ ወደ አማራ ክልል ከመጡ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲበታተኑ ቢደረግም፣ ለሳምንታት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከቆዩ በኋላ አብዛኛዎቹ ወደ ባህር ዳር ከተማ በመሄድ የክልሉ አስተዳደር መፍትሔ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ይገልጻሉ፡፡

ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሌላ ጥገኝነት እየጠየቁ ከቆዩ በኋላ 135 የሚሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲጠለሉ ሲፈቀድላቸው፣ ቀሪዎቹ ማለትም 286 ያህሉ በአሁኑ ጊዜ በክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ግቢ ውስጥ ናቸው፡፡

ከእነዚህም ውስጥ በአብዛኛው ማለትም 170 የሚሆኑት ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌና ጅማ ዞን ተፈናቅለው የመጡ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ነው፡፡ ከኦሮሚያ የተፈናቀሉት ከየካቲት 2010 ዓ.ም. ጀምሮሁለቱ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ተፈናቅለው እንደመጡ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ዞኖች የተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆች እንደገለጹት ማፈናቀሉ በቡድን በተደራጁ ወጣቶች እንደተካሄደ፣ በወቅቱ የአካባቢው ባለሥልጣናት ድርጊቱን ለማስቆም ምንም ዓይነት ዕገዛ እንዳላደረጉ ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል፡፡

ቡኖ በደሌ ወረዳ ውስጥ ይኖሩ የነበሩአራት ልጆች አባት፣ እሳቸውና ጓደኞቻቸው ማፈናቀሉ በተጀመረበት ወቅትወረዳው ኃላፊዎች ቤታቸውን እንኳን መሸጥ እንደማይችሉ እንደነገሯቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከ20 ዓመታት በላይ በወረዳው በእርሻ ተሰማርተው እንደነበር የገለጹት እኚህ አባት፣ ሁለትክታር ስፋት ያለው መሬት እንደነበራቸው በያዙት ሕጋዊ ሰነድ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እሳቸውና ሌሎች የአማራ ተወላጆች ከኦሮሚያ ክልል ቢፈናቀሉም፣ የኦሮሚያ ክልልም ሆነ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት መፈናቀል አንደነበር ከመግለጽ መቆጠባቸው ይታወሳል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፣ በማፈናቀሉ ድርጊት ተባባሪ የሆኑ የክልሉ አመራሮች ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹም በቅርቡ ወደነበሩባቸው ቀዬ እንዲመለሱ ክልሉ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃለፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አንዳንዶቹ የአማራ ብሔር ተፈናቃዮች የዞን ባለሥልጣናት ቢለምኗቸውም በፈቃደኝነት ወደ አማራ ክልል መሄድን እንደመረጡ፣ ነገር ግን የኃይል ማፈናቀል እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከማፈናቀሉ ጋር ተያይዞ ከኃላፊነት ተነስተዋል ተብሎ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ስለተሠራጨው መረጃ ተጠይቀው፣ መረጃ የለኝም ሲሉ በስልክ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ሰኔ 5 ቀን 2010 .ም. የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው፣ ከሁለቱም ክልሎች ማለትም ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል አመራሮች ጋር ምክክር መደረጉን ገልጸው ነበር፡፡

‹‹በጥቅምት ወር በተከሰተው ግጭት ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ከማሼ ዞንናኦሮሚያ ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖችን ወደነበሩባቸው አካባቢዎች ለመመለስና ለመደገፍ በአማራ፣ በቤንሻንጉልናኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች አመራሮች አማካይነት ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል፤›› ብለዋል፡፡

ሆኖም በቤተ ክርስቲያንና በጊዜያዊ ድንኳን ውስጥ የሚገኙት ተፈናቃዮች በአማራ ክልላዊ መንግሥት ድጋፍ አላገኘንም ሲሉ ተፈናቃዮቹ ላነሱት ቅሬታ፣ ለአቶ ንጉሡ ሪፖርተር በተደጋጋሚስልክ ጥሪና አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ቢላክላቸውም ምላሽመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ሪፖርተር በቦታው እንደታዘበው ተፈናቃዮቹ በአንድ ድንኳን ውስጥ በተጨናነቀ ሁኔታ እየኖሩ ነው፡፡ ከተፈናቃዮቹም ውስጥ አጥቢዎችና ሕፃናት እንደሚገኙበት ለማየት ተችሏል፡፡

ሪፖርተር ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተፈናቃዮቹ እንደገናስልክ እንደተነገረው፣ክልሉ በአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን በሠራላቸው ድንኳን ውስጥ ከሚኖሩት ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች በተቅማጥ ሕመምየተጠቁ ናቸው፡፡ ወረርሽኙም በየቀኑ ከሚቀርብላቸው ንፅህናው ከተጓደለ ምግብ እንደሚያያዝ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በየቀኑ ቢያንስ አሥር ሰዎች በተቅማጥ ሕመም እየተጠቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያገኙት ከባህር ዳርና በዙሪያዋ ከሚገኙ ወረዳዎች ነዋሪዎች ብቻ እንደሆነ፣ ከአማራ ክልል ተመሳሳይ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ በምሬት ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በአደጋ መከላከል ኮሚሽን ውስጥ ወደሚገኘው ጊዜያዊ መጠለያ ጉብኝት ከተደረገ በኋላ፣ በመግቢያው በር ላይ ያለው ጥበቃ እንደተጠናከረና ማንም ሰው ወደ ውጭ ወይም ውስጥ እንዳይገባ እንደተከለከለ ተፈናቃዮቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...