Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናፓርላማው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማብራሪያ ጠራ

  ፓርላማው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማብራሪያ ጠራ

  ቀን:

  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገሪቱ ወቅታዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ።

  የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በመጪው ሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በምክር ቤቱ ተገኝተው ከሕዝብ ተወካዮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

  አሳማኝ ምክንያት በማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ጠይቀው ተቀባይነት ካላገኙ በስተቀር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማውን ጥሪ ተቀብለው መገኘትና ማብራሪያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።

  የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው የፈለጉበት ዋነኛ ጉዳይ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰብስቦ ባሳለፋቸው ሁለት መሠረታዊ ውሳኔዎች ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

  የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ መቀበሉና የልማት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...