Sunday, December 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ እግር ኳስና የባለሙያው ቅኝት

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የባለሙያው ቅኝት

ቀን:

እግር ኳስ በኢትዮጵያ እንዲህ እንደ አሁኑ ባልዘመነበት በ1910ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አውሮፓውያንና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አማካይነት ቀስ በቀስ እየተስፋፋና እየተለመደ መምጣቱ በዘርፉ የተጻፉ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ይሁንና ስፖርቱ የዕድሜውን ያህል ዕድገት ማሳየት ተስኖት በተለይም በአሁኑ ወቅት ትንሣኤው ሳይሆን ውድቀቱ መነጋገሪያ ሆኖ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለበርካቶች ዋንኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ፣ መፍትሔ ይሆኑታል በሚል የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችና ምርምሮች እንዲሁም የመድረክ ውይይቶች ተደርገውበታል፡፡ ውጤቱ ግን ዛሬም እንደ ካሮት ሥር ወደታች ሆኗል፡፡ ይባስ ብሎ ለሰዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ‹‹የጭቃ ውስጥ እሾክ›› ሆኖ ለአካል ጉዳትና ለንብረት ውድመት ምክንያት በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ በጊዜ ሒደት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጥንቅጦች ሆነው ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ታሪኩንና ተግዳሮቶቹን በወጉና በሥርዓት ይዘው ለትውልድ የሚያስተላልፉ እምብዛም ናቸው፡፡ በርካቶች በሙያው ቢያልፉም፣ ባለፉበት የሙያ ዘርፍ  ስለ ስኬታቸውም ሆነ ውድቀታቸው እንዲሁም በዘርፉ የሚታዩ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ምን እንደሚመስሉ ለመዳሰስ ከሞከሩ ባለሙያተኞች መካከል የካፍ ኢንስትራክተርና አሠልጣኝ አብርሃም ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው፡፡

ኳሱ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ችግሮቹን አብጠርጥሮ በመለየት ሊነገርለት የሚገባው ወቅት ላይ ይገኛል፡፡ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ተመልክቶ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥለት እውነተኛና ደፋር ባለሙያኛ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በመነሳት ይመስላል አሠልጣኝ አብርሃም ‹‹እግር ኳሳችንና የኋሊት ዕርምጃው›› በሚል ርዕስ የእግር ኳሱን ተጋዳሮቶች የዳሰሱት፡፡   

አሠልጣኙ ‹‹ድፍረት ባይሆንብኝ›› ብለው በመጽሐፋቸው ካካተቷቸው ዕይታዎች መካከል፣ የሩቁን ትተው ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ብቻ ፌዴሬሽኑን ሲያስተዳድሩ የቆዩ አካላት ስለ ፕሮፌሽናል እግር ኳስና ሊግ መቋቋም በተለያዩ ሙያተኞች፣ ክለቦችና መገናኛ ብዙኃን ጥያቄው በተደጋጋሚ ቢቀርብም፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ግን እስካሁን ምንም ዓይነት መልስ ሊሰጥ ባለመቻሉ፣ ክለቦች በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት እየበጀቱ መርሐ ግብሮቻቸው በሞግዚት እንዲተዳደር ግድ ብሎት ይገኛል፡፡

ስፖርቱ በአጠቃላይ ይህ ነው የሚባል ተቋማዊ ቅርፅና የቁርጠኛ አመራር ዕጦት ውስጥ እንደሚገኝ የሚያትተው መጽሐፉ፣ ለዚህ ሁሉ የዕውቀት ማነስ ዋናውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እግር ኳሱ በተለይ የውድድር ደንብና ሥርዓት፣ የዳኝነትና የመሳሰሉት ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሌለበት አማተራዊ አሠራር እየተዳደረ ስለመገኘቱም ይተርካል፡፡ ስፖርቱ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ አዲስ አስተሳሰብና ሥርዓት ፈጥሮ መታደስ ይቅርና አዲስ ሰው ሲመጣ እንኳ ዓይናቸው ደም የሚለብስ የሚበዙበት መሆኑን የሚዳስሰው መጽሐፉ፣ በዙሪያው የሚንቀሳቀሱት ብዙዎቹ የሚያምኑበትን ሥራ መሥራት፣ በሚያምኑበት እምነት መጽናት፣ የሚያምኑበትን አቋም መግለጽና ማራመድ ወዘተ. ማድረግ የማይችሉ ስለመሆናቸው ጭምር ያብራራል፡፡

የአገሪቱ እግር ኳስ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው፣ ዘርፉ ዘመኑ የሚሻውን ዘመናዊነት ይዞ ወደ ፕሮፌሽናል ደረጃ ማደግና መጓዝ ሲችል ብቻ እንደሆነ፣ የፕሮፌሽናሊዝም አመለካከትና አስተሳሰብ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ሥራ በፕሮፌሽናል ባለሙያተኞች መመራት እንዳለበትም የአሠልጣኙ ዕይታ ያትታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከጊዜው ጋር አብሮ ሊራመድ የሚችል ተቋማዊ ቅርፅና ይዘት ሊኖረው ግድ እንደሚልም ያብራራል፡፡ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአማተርና የፕሮፌሽናል እግር ኳስ አንድነትና ልዩነት በአግባቡ መለየት ባለመቻሉ፣ አንዱ በአንዱ ላይ እየተደረበ መላ ቅጡ በጠፋው የአሠራር ሥርዓት ውስጥ እግር ኳሱ እንዲዳክር ምክንያት ሆኖት እንደሚገኝ የሚያትተው የአሠልጣኙ መጽሐፍ፣ ስፖርቱን ተከትሎ የሚስተዋሉ አለመግባባቶችና ውዝግቦች ሁሌም የማይጠፉት ሊዚህ ነው ይላል፡፡

የተግባር እንጂ የንድፈ ሐሳብ ችግር የሌለበት የኢትዮጵያ እግር ኳስ፣ በተለይ ተተኪ ወጣቶችን በሚመለከት፣ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካይነት እየተዘጋጀ በትምህርትና በውድድር መስኮች እንደሚሰጥ የሚያወሳው መጽሐፉ፣ በርካታ ወጣት እግር ኳሰኞች መፍራታቸውን፣ ለዚህም በቀድሞ የስፖርት ኮሚሽነር በነበሩት አቶ መላኩ ጴጥሮስ ጊዜ አሁንም ድረስ በመጫወት ላይ የሚገኙት አንዱ ዓለም ንጉሤ፣ ሳላዲን ሰዒድ፣ አዳነ ግርማና የመሳሰሉትን ይጠቅሳል፡፡

የታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች እግር ኳስ ልማት ዓላማ አድርጎ የሚነሳው የእግር ኳስ ዘርፍ፣ ሥራው መሠራት ካለበት ከሌሎች አገሮች ጋር ተፎካካሪና ብቁ ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ አሸናፊ ቡድን ለመፍጠር እንጂ ተሳታፊ ቡድን ብቻ ለማደራጀት እንዳልሆነ ጭምር የእግር ኳሱን ተግዳሮቶች የሚዳስሰው ይኼው መጽሐፍ፣ በዚህ ወቅት ግዙፍና በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሚያንቀሳቅሰው የእግር ኳስ ኢንዱስትሪ፣ ኢትዮጵያ ስለምን ተገለለች ብሎ መጠየቅ መቻል ያስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያ አንድ ክፍለ ዘመን የሚጠጋ ዓመታት የአፍሪካ እግር ኳስ ተቋምን ከመሠረቱ ነባርና ቀደምት አገሮች ተርታ እንደምትመደብ የሚያወሳው የአሠልጣኙ ዕይታ፣ አሁንም ከ‹‹ነበርን›› ያለፈ አፈ ታሪክ ላይ እንደምንገኝ ይናገራል፡፡ ይኸም በመሆኑ ከፍተኛ የሠለጠነ የሰው ኃይል፣ ፋይናንስና ፋሲሊቲ የሚያስፈልገው የሕፃናትና ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ልማት ፕሮግራም መተግበር በቀላሉ ሊታሰብ የሚችል እንዳልሆነ፣ ሕፃናትና ታዳጊ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለቁም ነገር ማብቃት የሚቻለው ደግሞ፣ ሥልጠናውን በአግባቡና በወጉ ሊሰጡ የሚችሉ በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠኑ አሠልጣኞች ማፍራት ግዴታ ስለመሆኑም ያብራራል፡፡

እግር ኳስን ለማልማት የዓመታት ልፋት፣ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር መዋለ ንዋይ፣ የሠለጠነ የሰው ኃይልና ምቹ የእግር ኳስ መሠረተ ልማቶች እንደሚያስፈልጉ ለአፍታ እንኳ ሊዘነጋ እንደማይችል፣ ለዚህ ደግሞ የእግር ኳሱ ባለድርሻና  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከምሥረታው አሁን እስኪሚገኝበት ድረስ እየገጠሙት ስላሉት ችግሮችና  በወፍ በረር የተመለከታቸውን እንዲሁም የእግር ኳሱን ክፍተቶችና መፍትሔዎቻቸውን ጭምር ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...