Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ሊተከሉ ነው

ከአራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ሊተከሉ ነው

ቀን:

ከተያዘው ሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ በኢትዮጵያ ከ4.3 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስትር የደን ልማት ምዝገባ ፕላንና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ሔይሩ ሰብራና አህመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ችግኞቹ የሚተከሉት ከአንድ ሚሊዮን ሔክታር በላይ በሆነ ገላጣና ተራራማ ቦታዎች ላይ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ያለው የደን ሽፋን መጠን 15.5 በመቶ እንደሆነ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ግን ይህ መጠን ወደ 20 በመቶ ያድጋል የሚል እምነት እንዳለ አስረድተዋል።

ቀደም ሲል የነበረውን የደን ሽፋን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየታገዘ ባለመጠናቱ ትክክለኛውን መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ እንዳደረገው፣ ከዚህም የተነሳ ግማሹ ሦስት በመቶ ሲል እኩሉ ደግሞ ዘጠኝ በመቶ እያለ እንደሚያስቀምጠው ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ ያለውን የደን ሽፋን መጠን ግን የተለካው ከጂአይኤስ ጋር ግንኙነት ባለው በሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲሆን፣ ለትክክለኝነቱም ጥርጣሬ እንደማያሳድር አመልክተዋል። 

እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ በየዓመቱ 92‚000 ሔክታር የሚመነጠር ሲሆን የሚለማው ደግሞ 19‚000 ሔክታር ነው።

የ15.5 በመቶ የደን ሽፋን ሲገለጽ

የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ኤጀንሲ በ2007 ዓ.ም. የመሬት አጠቃቀምና ሽፋን ካርታን ባስመረቀበት ወቅት፣ ከ1995 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ያለው የደን ሽፋን መጨመሩንና 15 በመቶ ስለመድረሱ በካርታ ሥራው የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ ማስታወቁ ይታወሳል።

የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴርም በኢትዮጵያ የደን ሽፋኑ 15.5 በመቶ መድረሱን ከካቻምና በፊት ሲያስታውቅ እንደጠቆመው፣ የደን ሽፋኑ እዚህ ላይ የደረሰው የተፈጥሮ፣ የሰው ሠራሽና የወንዝ ዳር ደኖች በደን ሽፋን ብያኔ ሥር በመካተታቸው ነው። በቀደሙት ዓመታት የደን ሽፋን ሦስት በመቶ ነው ይባል የነበረው የተፈጥሮ ጥብቅ ደንን ብቻ ታሳቢ በማድረግ እንደነበረ መገለጹም ይታወሳል። 

የደን ሽፋን 15.5 እንደደረሰ የተገለጸው፣ በደን ልማት ዘርፉ ላይ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ያጠኑት ዶ/ር ተሾመ ተሰማ እንዳመለከቱት፣ በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ዕትእ) ከተተከሉ ችግኞች መካከል 58 በመቶ ያህሉን ማፅደቅ መቻሉን፣ በዚሁ የዕትእ ዘመን ለማልማት ከተያዘው የደን ልማት 58 በመቶ ያህል ማሳካት መቻሉን ተረጋግጧል።

 ችግኝ መትከል ብቻውን የመጨረሻ ግብ አይደለም። ችግኞች በወል፣ በግልና በመንግሥት መተከላቸውና አሁንም እየተተከሉ መሆኑን በሚያወሳው ጥናት እንደተመለከተው፣ ለችግኞች መፅደቅና ውጤታማነት በወል፣ በግልና በመንግሥት ባለቤትነት ባሉት ይዞታዎች ላይ በተደረገው ምዘና በአፈጻጸም ደረጃቸው በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ የያዙት የግል፣ የመንግሥትና የወል ናቸው። በችግኞች የመፅደቅ ደረጃ የወል ችግኞች ዝቅተኛ አፈጻጸም የተመዘገበው ከድኅረ ችግኝ እንክብካቤና አያያዝ ጉድለት ችግኞቹ በእንሰሳት በመበላት፣ በሰዎች መቀጠፍና የኩትኳቶ ውኃ የማጠጣትና ማዳበሪያ የመጨምር ክፍተት በመኖሩ ምክንያት እንደሆነም መመልከቱ ይታወሳል።

ዘንድሮ የሚተከሉትን ችግኞች በኃላፊነት የመንከባከብ ተግባር በቅድመ ችግኝ ተከላ፣ በችግኝ ተከላና በድኅረ ችግኝ እንክብካቤ ሒደት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንዳለበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...