Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረት​አንበጣ

  ​አንበጣ

  ቀን:

  አንበጦች መካከለኛ የሰውነት መጠን ካላቸው ነፍሳት ይመደባሉ፡፡ ሳር በሚገኝበት በማንኛውም የዓለም ክፍል የሚኖሩት አንበጦች፣ ረዥም ርቀት በመዝለል ችሎታቸው ይታወቃሉ፡፡

  11 ሺሕ ያህል የአንበጣ ዝርያዎች ሲኖሩ፣ አብዛኞቹ እስከ ሁለት ኢንች፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ አምስት ኢንች ድረስ ያድጋሉ፡፡

  ኑሮዋቸው በሞቃታማ ሥፍራዎች ነው፡፡ ሳር፣ ሰብል፣ የዛፍ ቅጠልና ቅርፊት ደግሞ ምግባቸው ነው፡፡ አንድ አካባቢ ላይ በመስፈር በአካባቢው የሚገኝ ሰብልና ዛፍን ባንዴ የማውደም አቅም አላቸው፡፡ ሦስት የሰውነት ክፍል፣ ሁለት ጥንድ ክንፍ፣ ስድስት እግር፣ እንዲሁም ሁለት አንቴና አላቸው፡፡

  አንቴናቸው ከሰውነታቸው ርዝመት የሚበልጥ ሲሆን፣ በአካባቢያቸው ያለውን ነገር ለመለየት ይረዳቸዋል፡፡ ከስድስት እግሮቻቸው ከኋላ ያሉትን ሁለቱን ለመዝለል ሲጠቀሙባቸው፣ ከፊት ያሉት አራቱን ምግባቸውን ለመያዝ ይገለገሉባቸዋል፡፡

  ለወፎች፣ ለተሳቢ እንዲሁም ለአጥቢ እንስሳት ምግብ ሲሆኑ፣ በአፍሪካ አንዳንድ አገሮችና በእስያ ለሰዎች ምግብነትም ይውላሉ፡፡

  የዕድሜ ዘመናቸው አንድ ዓመት ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ዘጠኙን ወር የሚያሳልፉት በእንቁላል ውስጥ እያሉ አፈር ውስጥ ተቀብረው ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...