የሥዕል ዐውደ ርዕይ
‹‹ዛሬ ትላንት ነገ›› የተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ከየካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በላፍቶ አርት ጋለሪ ይታያል፡፡ የለይኩን ግርማ፣ አሌክሳንደር ታደሰ፣ አብርሃም ደበበ፣ ጋሻሁን ካሳሁንና አሸናፊ መስቲካ ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡
በጎተ ኢንስቲትዩት ደግሞ ‹‹ኢንዲጂኒየስ ክላውድስ›› በሚል የታምራት ገዛኸኝ ሥራዎች እየታዩ ነው፡፡
የብርሃን አስማማው ሥዕሎች ‹‹ሒድን ላይት›› በሚል ርዕስ ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 5 በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲዝ ይታያሉ፡፡
በተመሳሳይ የሴት ሠዓሊያን ማኅበር አባላት ሥራዎቻቸውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ከመጋቢት 1 ጀምሮ ያሳያሉ፡፡
ውይይት
ዝግጅት፡- ‹‹የሕይወቴ ታሪክ›› በተሰኘው የተክለጻዲቅ መኩሪያ መጽሐፍ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡
ቀን፡- የካቲት 27
ሰዓት፡- 8፡30
ቦታ፡- ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና መጻሕፍት ኤጀንሲ (ወመዘክር)
አዘጋጅ፡- ጎተ ኢንስቲትዩትና እናት ማስታወቂያ