Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊሕገወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውርን ለመቆጣጠር አነፍናፊ ውሻዎች ሊሰማሩ ነው

ሕገወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውርን ለመቆጣጠር አነፍናፊ ውሻዎች ሊሰማሩ ነው

ቀን:

በዱር እንስሳትና ውጤታቸው ዙሪያ የሚደረገውን ሕገወጥ ዝውውር ለመቅረፍ አነፍናፊ ውሾች ጥቅም ላይ ሊውሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን አገልግሎቱን ለመጀመር ከባለድርሻ አካላት ጋር ድርድር ላይ መሆኑን፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ማግኘቱንና እንቅስቃሴው ከተጀመረ ዓመት እንደሆነው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በመሥሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

‹‹የዱር እንስሳትና ውጤታቸው ሕገወጥ ዝውውር በዓለም ላይ ውስብስብ ወንጀል ሆኗል፡፡ ወንጀሎቹን ለመከላከልም የተለያዩ ስልቶችን መጠቀም ግድ ይላል፤›› ያሉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳውድ ሙሜ፣ በመጀመሪያው የዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ውስጥ አውሮፕላኖችን ተጠቅመው የዱር እንስሳት ውጤቶችን በሕገወጥ መንገድ ለማዘዋወር የሞከሩ 700 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር አነፍናፊ ውሾችን በመጠቀምና በኤክስሬይ ማሽን የፍተሻ ሒደቱን በማጥበቅ ሳይታወቁ በሕገወጥ መንገድ የሚወጡ የእንስሳት ውጤቶችን ለማስቀረት እንደሚሠራ ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

- Advertisement -

በሌላ በኩል በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ጐረቤት አገሮች የሚሰደዱ የዱር እንስሳትን ለመጠበቅ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል፡፡ ‹‹በዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ኅብረት ደንብ መሠረት ሁለት የፖለቲካ ድንበርን የሚያቋርጡና አዋሳኝ የሆኑ የጥበቃ ቦታዎች በጋራ የልማትና ጥበቃ አሠራር ሥርዓት ይዘረጋላቸዋል ይላል፤›› የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ በጋምቤላና በደቡብ ሱዳን በሚገኘው ቦማ መስመር ላይ ድንበር ተሻጋሪ የጥበቃ ቦታ መመሥረቱን፣ ዲንደር ናሽናል ፓርክና በኬንያና ኢትዮ ሶማሌ ድንበር ላይ የሚገኘውን ገራይስ ፓርክ (በሱዳን የሚገኝ ፓርክ ነው) እና አልጣሽ ፓርክም የጋራ የልማትና ጥበቃ አሠራር ሥርዓት ዘርግተው በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በጋምቤላና በቦማ በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የዱር እንስሳት እንደሚመላለሱ ይህም በዓለም ሁለተኛው ከፍተኛ የዱር እንስሳት የስደት መስመር መሆኑን አክለዋል፡፡ የተመሳሳይ አሠራሮች መበራከትም አገሪቱ ያላትን የዱር እንስሳት ሀብት ለማስጠበቅ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የአየር ፀባይ መዛባት በዱር እንስሳት ሀብት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የሚናገሩት አቶ ዳውድ በፓርኮች ዙሪያ ማረስ፣ ከብቶች ለግጦሽ ማሰማራት፣ የመዝናኛ ቦታዎች ግንባታ በእንስሳት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ13 የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ላይ በተደረገ ጥናት ላይም 114 ሚሊዮን ቶን የካርቦን ልቀት እንዲኖር ምክንያት መሆናቸውን ተጠቁሟል፡፡ ይህንንም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የበጀት ዓመት 50 በመቶ ያህል በመቀነስ የእንስሳቱን ደኅንነት ለመጠበቅ መታቀዱን አቶ ዳውድ ገልጸዋል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የዱር እንስሳት ቀን ከመጋቢት 3 ቀን 2008 ጀምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወሩን ሙሉ እንደሚከበር የመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱም ከመጋቢት 24 እስከ 26 በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚሆን አቶ ዳውድ ገልጸዋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ የተወሰኑት ዝርያዎች ከኢትዮጵያ ውጪ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ በአገር ውስጥ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ ዝርያዎችም አሉ፡፡ 36 ዓይነት አጥቢ፣ 18 ዓይነት አዕዋፋት፣ 15 ዓይነት ተሳቢ፣ 41 ዓይነት የዓሳ ብርቅዬ ዝርያዎች በአገሪቱ ከመገኘታቸው በተጨማሪም አምስቱ የአፍሪካ ታላላቅ የዱር እንስሳት ዝሆን፣ አውራሪስ፣ ጐሽ፣ አንበሳና ነብር ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ከ6,000 እስከ 7,000 የሚደርሱ ታላላቅ የዕፀዋት ዝርያዎች አሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...