Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የአሽከርካሪዎች ሥልጠና በተለየ መንገድ ሊሰጥ ነው

በአዲስ አበባ የአሽከርካሪዎች ሥልጠና በተለየ መንገድ ሊሰጥ ነው

ቀን:

– በሒደት ፈተናውም ይለወጣል

በአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሥር በቃሊቲ ማሠልጠኛ ይሰጥ የነበረው የአሽከርካሪዎች ሥልጠና እንደሚቀየር ቢሮው ለሪፖርተር አስታወቀ፡፡

የባለሥልጣኑ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ቁጥጥር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ፉፋ እንደገለጹት፣ ሥልጠናው ከአሁን በኋላ በአንድ ማዕከል በቃሊቲ ማሠልጠኛ ብቻ ሳይሆን፣ ምሥራቅና ምዕራብ ተብሎ በአያትና በአየር ጤና ዓለም ባንክ ማሠልጠኛዎች ይሰጣል፡፡ በዚህ መሠረት የአሽከርካሪ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቶች ተከፋፍለው በሁለቱ ማዕከሎች እንዲሠሩ ይደረጋል፡፡

‹‹አደጋ በዛ፡፡ ተማሪዎች በአንደኛና በሁለተኛ ማርሽ የታጠረ ማሠልጠኛ ውስጥ እየሠለጠኑ ለማሽከርከር ብቁ ናቸው ማለት ቸገረን፤›› ያሉት አቶ ታምሩ፣ አዲሶቹ ማሠልጠኛዎች የተከለሉ ሳይሆኑ የተወሰነ መደበኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ  የሚታይባቸው ቦታዎች እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡ ቢሆንም ግን ቦታዎቹ መነሻና መድረሻ ላይ ሠልጣኞች መኖራቸውን የሚያሳይና ሌሎች የትራፊክ ምልክቶችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡

ይህ የሥልጠና አሰጣጥ እንደ ትግራይ ባሉ ክልሎች ተጀምሯል፡፡ በአዲስ አበባ አሠራሩ ተግባራዊ እንዲሆን ከአንድ ወር በፊት መመርያ የተላለፈው ከፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሆኑን የገለጹት አቶ ታምሩ፣ የሥልጠናውን አካሄድ መለወጥ ያስፈለገው እየደረሱ ላሉት የትራፊክ አደጋዎች የአሽከርካሪዎች ብቃት ችግር አንዱ ምክንያት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የተሽከርካሪ ሠልጣኝ ጥመርታ (አንድ ተሽከርካሪ በቀን ስንት ሠልጣኞች የሚያስተናግዱበት አሠራር)፣ እንዲሁም ሠልጣኞች መሠልጠን ያለባቸውን ሰዓት በሙሉ መሠልጠናቸውን ማረጋገጥ ካልተቻለ ሥልጠናው የሚሰጥበትን መንገድ መለወጥ በራሱ ለውጥ ያመጣል ወይ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ታምሩ፣ የተሽከርካሪ ሠልጣኝ ጥመርታ በቀን አሥር መሆኑን በምሳሌነት ጠቅሰው ነገር ግን በዚህ ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ቢሆንም ግን እነዚህን ጉዳዮች የሚመለከተውን መመርያ ተፈጻሚ ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለጊዜው በዚህ ቀን ተብሎ ባይቀመጥም በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎች ከቃሊቲ እንዲወጡና በተመደቡበት የሥልጠና ጣቢያ እንዲሰማሩ ይደረጋል፡፡ ሥልጠናውን ብቻም ሳይሆን የፈተና አሰጣጡም በሒደት እንደሚቀየር አቶ ታምሩ ገልጸዋል፡፡

በቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ለዓመታት የሠልጣኞች ፈተና በካሜራ የታገዘ የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሲሲ ቲቪ ካሜራው በመበላሸቱ እስካሁን ፈተናው እየተሰጠ ያለው በሰው ኃይል ነው፡፡ የተበላሸው የካሜራ አዳብተር ካሜራውን በገጠመው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ እየተፈለገ መሆኑን በሚመለከተው አካል መገለጹን ሪፖርተር ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል፡፡

የተበላሸውን አዳብተር ለመለወጥ በአገር ውስጥ ዓለም አቀፍ ጨረታም መውጣቱን፣ አዳብተሩን ማግኘት ካልተቻለ ግን ሙሉ ሲስተሙን በመቀየር ፈተናውን በካሜራ ወደ ማድረግ እንደሚመለሱ አቶ ታምሩ ገልጸዋል፡፡ እዚያው ቃሊቲ አካባቢ ሌላ ማሠልጠኛ ለመክፈት መሬት መረከባቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ለውጡ ምናልባትም በአዲስ አበባ ተግባራዊነቱ ለሦስት ወራት እንዲዘገይ ከተደረገውና በአዲስ አበባ የታክሲ ማኅበራት እንዲሻሻል ከተጠየቀው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 208/2003 የሚያያዝ እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው፣ ‹‹ለውጡ የሚያያዘው ከአደጋ መብዛት ጋር ነው፤›› በማለት አቶ ታምሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...