‹‹ሁላችሁም ራሳችሁን እንድትጠይቁ የምፈልገው ዓለም በየዓመቱ 500 ቢሊዮን ሲኒ ቡና በሚጠጣበት ወቅት፣ ይህንን ሲኒ ለሚሞላው ገበሬ ምን ያህል ፍትሐዊ ክፍያ እንደሚከፈለው ነው::››
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. አራተኛውን የዓለም የቡና ጉባኤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ አዳራሽ በከፈቱበት ወቅት ካደረጉት ንግግር ውስጥ ይህ አንቀጽ ትኩረትን ስቧል፡፡ ‹‹የቡና መገኛና ብዝኃነት›› የሚል መሪ ቃል ባነገበው መድረክ 1400 ጉባኤተኞች ተሳትፈውበታል፡፡