ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ይናገር ደሴን (ዶ/ር) የብሔራዊ ባንክ ገዥ አድርገው ሾሙ፡፡
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ በቃሉ ዘለቀ ምክትል ገዥ ሆነው ተሹመዋል፡፡
የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ለረዥም ዓመታት በገዥነት አገልግለዋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት የነበሩት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ልማት ጥናት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት እንደሚሾም ሲጠበቅ በተመሳሳይ ለብሔራዊ የፕላን ኮሚሽንም አዲስ ኮሚሽነር ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡