Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና​የጣሊያን ፕሬዚዳንት የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ይገባሉ

​የጣሊያን ፕሬዚዳንት የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ይገባሉ

ቀን:

የጣሊያን ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ የአምስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ይህ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ከሃያ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ጉብኝቱ ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደሚቆይ የጣሊያን ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ወቅት ከፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው፣ የሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ ተጠቁሟል፡፡

ማታሬላ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡኑ ማቲያስ ጋር ተገናኝተው የሚወያዩ መሆኑን፣ በተጨማሪም አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት ሥር የመታሰቢያ ጉንጉን አበባ እንደሚያስቀምጡም ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ትስስርና ዕድገት፣ አካባቢያዊ ሰላምና መረጋጋት፣ እንዲሁም የአውሮፓ አገሮች የወቅቱ ራስ ምታት የሆነው የስደተኞች ጉዳይ ዋነኛዎቹ የውይይት አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ አገሮች ትምህርትና ባህልን በተመለከተ እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

በዚህም መሠረት የጣሊያን የትምህርት፣ የዩኒቨርሲቲና የምርምር ሚኒስትር ስትፋንያ ጂያኒኒና ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርዮ ጂሮ ከፕሬዚዳንቱ ጋር አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው የጣሊያን ልማት ድርጅት ዕርዳታ የሚያደርግለትን የጋምቤላ የስደተኞች ካምፕንና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጎብኘት ዕቅድ ይዘዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአኅጉሪቱን ቀጣይ ተስፋ ብሩህ ለማድረግ የጣሊያን መንግሥት ሊያበረክተው ስለሚችለው አስተዋጽኦ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ከዶ/ር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም እንዲሁ ተገልጿል፡፡

ሰርጂዮ ማታሬላ የተወለዱት እ.ኤ.አ. በ1941 ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2015 የጣሊያን ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት አገራቸውን በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ በዚህም መሠረት እ.ኤ.አ. ከ1983 እስከ 2008 ድረስ የአገሪቱ የፓርላማ አባል፣ ከ1989 እስከ 1990 የትምህርት ሚኒስትር፣ ከ1999 እስከ 2001 የመከላከያ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ፣ ከ2011 ጀምሮ እስከ 2015 ድረስ የአገሪቱ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ሰርጂዮ ማታሬላ 12ኛው የጣሊያን ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ ከሲሲሊ የተወከሉ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...