Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ የሚያስችል የመጨረሻ ውይይት በፓርላማ ተደረገ

ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ የሚያስችል የመጨረሻ ውይይት በፓርላማ ተደረገ

ቀን:

የሁለት ኤጀንሲዎች ፈቃድ ተሰረዘ

ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመላክ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የሁለትዮሽ ስምምነት አስፈላጊ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መላክ የሚቻልበትን ሁኔታዎችን በሚመለከት የመጨረሻ ውይይት ማክሰኞ  ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ተደረገ፡፡

የፓርላማው ማኅበራዊና የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምሥግና አረጋና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሥራ ሥምሪት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ብርሃኑ አበራ፣ እንዲሁም የውጭ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የቦርድ አባላት ሠራተኞች ከመላካቸውና ከተላኩ በኋላ ስለሚኖሩ ጉዳዮች መወያየታቸው ታውቋል፡፡

ለቋሚ ኮሚቴው ያስረዱት የሚኒስቴሩና የኤጀንሲዎቹ ቦርድ አባላት እንዳብራሩት፣ በተለይ ለቤት ሠራተኛነት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን በሕግ ተደንግጎ ከወጣው መብትና ግዴታ በተጨማሪ ሳዑዲ ዓረቢያ እንደደረሱ የባንክ ሒሳብ እንዲከፈትላቸውና ችግር እንዳይገጥማቸው፣ በማንኛውም ሁኔታ ኮንትራት የፈረመው ኤጀንሲ እንዲረዳቸውና ሌሎችንም እንክብካቤዎች እንዲያደርግላቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የኤጀንሲዎቹ ተወካይ የቦርድ አባላት ለቋሚ ኮሚቴው ያነሱት ጥያቄ በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ኤጀንሲዎችና ኩባንያዎች መሆናቸውን ጠቁመው፣ በተለይ ኩባንያዎቹ ሠራተኞቹን ፈርመውና ተዋውለው ከተቀበሉ በኋላ በኪራይ ይጠቀሙባቸዋል እንደሚባል አንስተዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ጉዳይ በመንግሥት በኩል ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰባቸውም ተጠቁሟል፡፡ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ ፈቃድ ከወሰዱ 96 ኤጀንሲዎች መካከል አብዛኛዎቹ ልዩ ትኩረት የሚሰጣቸው መሆኑንም አክለዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እንኳን በመንግሥት ተፈቅዶ ይቅርና የሁለትዮሽ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት እንደተፈቀደ አስመስለው ዜጎችን በሕገወጥ መንገድ ሲልኩ የተገኙና መንግሥትም ተከታትሎ ዕርምጃ መውሰዱን ማስረዳታቸው ተገልጿል፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ይርጋለም እንደገለጹት፣ ሥምሪት ባልተጀመረበትና ገና የሁለትዮሽ ስምምነቱ በሒደት ላይ እያለ ሠራተኞችን እየመለመለ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሲልክ የነበረው ኢትዮጵያዊ ዜግነት በሌለው ግለሰብ የተቋቋመው አልተያር የተባለ ኤጀንሲ፣ ከሁለት ወራት በፊት ከመጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ፈቃዱ መሰረዙን አስታውቀዋል፡፡ ሌላው ከሦስት ጊዜ በላይ ዕገዳ እያለበት አዋጁን ጥሶ ሲሠራ የነበረና ከሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ፈቃዱ መሰረዙን አቶ አሰፋ የገለጹት አልሎዲ የተባለ የውጭ አገር የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲን ነው፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱት ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን አውቀው ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...