Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የመጀመርያው የጀርመን መኪና በኢትዮጵያ

ትኩስ ፅሁፎች

በዓለም ታዋቂው የጀርመኑ ቢኤምደብሊው መኪና ኩባንያ በመጋቢት መባቻ የተመሠረተበትን 100 ዓመት ማክበሩን በድረ ገጹ የዘገበው ዶቸቬሌ፣ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት 1900 ዓ.ም. ገደማ ጀርመናዊው ነጋዴ አርኖልድ ሆልዝ ወደ ኢትዮጵያ የጀርመንን መኪና ማስገባቱን ያወሳል፡፡ በጀርመን የመንጃ ፈቃዳቸውን የያዙት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የልጅ ልጅ አቶ ታደለ ይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ያወጉትንም አትሟል

«በእኛገር የመኪና አመጣጥ ታሪክ እንደዚህ ነው። 1900 .ም. ለአፄ ምኒልክ መኪና ለማምጣት አርኖልድ ሆልዝ የሚባል ጀርመናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ በትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ተሰማርቶ ነበር። በዚያን ጊዜ በወርቅ ማዕድን ንግድና በሌሎች እንዲያውም በባንክም ጭምር ሐሳብ የነበረው ይመስለኛል። ቴክኖሎጂ አፍቃሪ የነበሩትን አፄ ምኒልክን ለማስደሰት ጥር 15 ቀን 1900 ዓ.ም. መኪናውን ይዞ አዲስ አበባ ገብቶአል። ነገር ግን እሱ አዲስ አበባ መኪና ይዞ ከመምጣቱ 15 ቀናት በፊት ቤንዝ ሌይ የሚባል እንግሊዛዊ ሌላ መኪና ከእንግሊዝ ከአንድ ጓደኛው ጋር ይዞላቸው መጥቶ ነበር። የመጀመርያ የምትባለው መኪና ኢትዮጵያ የገባችው እንግሊዛዊው ይዞመጣት ነች። ነገር ግን የኛን የመኪና ታሪክ ከጀርመን ጋር በጣም የሚያገናኘው ጀርመናዊው አርኖልድ ሆልዝ ይዞ የመጣው ነው። ከነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ፓስፖርት እንዳየሁት ከሆነ ከዚያ በኋላ የካቲት 23 ቀን አፄ ምኒልክ ለነጋድራስ አስታጥቄ ወልደጻድቅ ለኪዳነ ወልድና ለነጋድራስ ለሦስቱ በአንድ ወረቀት ላይ ወደ አውሮፓ እንዲሄዱ የላኩበት ፓስፖርትን ጽፈዋል። ወደ ጀርመን ተልከው የሄዱት ልዑካን እስከ 1902 ዓ.ም. ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ቆይተዋል

ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ግን እዚያ ቆይተውጀርመን በመኪና መንዳትና በጥገና በመሠልጠን የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ሆነው ከተመለሱ በኋላ በቤተ መንግሥት የመኪኖች ኃላፊ ሆነው እስከ 1903 ዓ.ም. ሌሎች ኢትዮጵያውያንን መኪና መንዳትንና ጥገና ሞያን አሠልጥነዋል።

******

‹‹እሹሩሩ. . .››

‹‹እሹሩሩ ማሞ እሹሩሩ

ልጄ እሹሩሩ

ስበላም አዝዬ

ስሠራም አዝዬ …››

እኚህ የምናያቸው እንስት የሴራሊዮን የአገር ግዛትና የገጠር ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳያኔ ኮኖማኒያ ናቸው፡፡ በሥራ ገበታቸው፣ በሚኒስቴሩ ልዩ ጽሕፈት ቤታቸው ሥራቸውን እያከናወኑ ያሉት ልጃቸውን ባገራቸው አንቀልባ አዝለው ነው፡፡ የኬንያው ዘ አፍሪካን ኒውስ ፖስት ‹‹አርአያነት ያለው ተግባር›› ብሎ ብቻ አልቆመም፡፡  ኬንያውያት ሚኒስትሮችስ ምን ያስባሉ? ብሎ አክሎበታል፡፡

******

‹‹እውነትን ከመጠቆምና ከማሳሰብ ቸል አልልም››

ሶክራቲስ በሐሰት ተከሶ በሀገሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት ከመቀበሉ በፊት ተግባሩን፣ ሥነ ምግባሩን በመከላከል (አፖሎጊያ) ከተናገረው ባጭሩ እንጠቅሳለን፡፡ ስለ ነፍስ ማሰብ መጠንቀቅ (ኤፒሜሊያ ፕስሂስ) እንደሚገባ በተነገረው ላይ እናተኩራለን፡፡

‹‹አቴናውያን ወገኖቼ ሆይ! ምንም እንኳ ብወዳችሁና ባከብራችሁ ከእናንተ ይልቅ ለሰማይ መታዘዝን እመርጣለሁ፡፡ እስከ መጨረሻው ጥበብን ከመከታተል አላቋርጥም፡፡ እንዲሁም በመንገድ ለምትገጥሙኝ ሁሉ እውነትን ከመጠቆምና ከማሳሰብ ቸል አልልም፡፡ እንደ ልማዴ እንዲህ እያልኩ፡፡

‹‹መልካም ወዳጄ ሆይ! በጥበባት ሀብት ዝነኛ የሆነችው የታላቋ ከተማ የአቴና ዜጋ ነህ፡፡ ብልጽግናን፣ ክብርን፣ ዝናን፣ የመሰሉትንም ሁሉ ለማከማቸት ይህን ያህል ስትደክም ለጥበብ፣ ለዕውቀት ለነፍስህ መሻሻል ምንም አለማሰብህ አያሳፍርህምን ለነዚህ ነገሮች የሚያስብ መሆኑን በመግለጽ ቢቃወመኝ ወዲያው ትቼው መንገዴን አልቀጥልም፡፡ እጠይቀዋለሁ፡፡ እፈትሸዋለሁ፡፡ የሚወደውን በጎነት (አሬቲ) እንደሚለው ያልያዙ ሆኖ ካገኘሁት እጅግ ውድ የሆኑትን ነገሮች ርካሽ አድርጎ፤ ዋጋ ቢስ የሆኑትን ውድ አድርጎ በመቀበሉ ሳልወቅሰው አላልፍም፡፡

‹‹ለሚገጥመኝ ሁሉ ሽማግሌም ሆነ ወጣት፤ በተለይም ወገኖቼ፣ ሕዝቤ ለሆናችሁ ለእናንተ ይህን ከማድረግ አልቆጠብም፡፡ ይህ የግዜር ትእዛዝ ነው፡፡ አትጠራጠሩ፡፡ እኔ ለዚህ አገልግሎት ከመቆሜ የተሻለ ሌላ ዕድል አቴናውያን እንዳልገጠማችሁ አምናለሁ፡፡

 እናንተን ከመምከር በስተቀር ሌላ ሥራ የለኝም፡፡ ወጣትም፣ ሽማግሌም ለአካላችሁ፣ ለሀብት ለንብረት ከምታስቡት የበለጠ ለነፍሳችሁ መሻሻል አስቡ፡፡ ለዚህኛው ቅድሚያ ስጡ፡፡ ደግነት ከሀብት የሚገኝ አይደለም፡፡ ሀብትንና ማናቸውንም ሌላ ነገር ሁሉ በግልም በማኅበራዊም ኑሮ ረገድ ለሰው ዋጋማ የሚያደርገው ደግነት ነው፡፡ ይህን በመናገሬ ወጣቶችን አሳስተሃል ትሉኝ እንደሆነ ግድ የለኝም፡፡››

  • እጓለ ገብረ ዮሐንስ ‹‹ብፁዓን ንጹሐነ ልብ›› (2005)

***********************

ትንጎራደዳለች ውበት ተጎናጽፋ

ትንጎራደዳለች ውበት ተጎናጽፋ

እንደ ሌላ አገሮች ሌቱ ደመና አልባ

ጨለማውም ይሁን ብርሃኑም የላቀ ከዋክብት የሞላ፤

የተወሃሃዱት ዓይኗን ገጽታዋ

እንደዚህ ስትፈካ በለስላሳው ብርሃን

እግዜር የነፈገው ለጠራራው ቀን።

ቅንጣት ጥላም ትሁን፤ ብታንስ አንዲት ጮራ፤

ግማሽ ያጎድለዋል ያን ስም የለሽ ፀጋ

የተጎነጎነው በጥቁር ጎፈሬ ሹርባዋ ዞማ፤

ወይ ለስላሳው ብርሃን ፊቷ ላይ ያበራ

የመሠከሩበት ሃሳቦች የጣሙ በጥሞና እርጋታ

ውብም ነው ተወዳጅ ያረፉበት ቦታ።

በዚያች ጉንጭና ቅንድብ ሽፋሽፍት፤

ለስላሳም፤ የረጋ፤ ሆኖም የተሟላ ርቱዕ አንደበት፤

ፈገግታዋ ኃያል፤ ቀለሟ የጋለ፤

ደግሞም የሚያሳብቅ በምሥራች ቀናት በደስታ የዋለ፤

ሰላማዊው መንፈስ፤ ከዚያም በታች ያልፋል፤

የልቧ ፍቅርም በቅንነት ሞልቷል።

  • ከጆርጅ ጎርደን ባይረን/ነፃ ትርጉም በዳዊት ዘኪሮስ

******

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች