Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎችን የአስተዳደር ወሰን ለማካለል የክልሎቹ ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትብብር ተጠየቀ

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎችን የአስተዳደር ወሰን ለማካለል የክልሎቹ ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትብብር ተጠየቀ

ቀን:

የበርካቶችን ሕይወት በቀጠፈው ግጭት ተሳትፈዋል የተባሉ አመራሮችን ሙሉ በሙሉ መያዝ አልተቻለም

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የአስተዳደር ወሰን ውዝግብን ለመፍታትና አስተዳደራዊ ወሰኖችን ለማካለል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና የማካለል ሥራውን በሰላማዊ ሁኔታ ለማከናወን የሁለቱም ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲተባበሩና እንዲከታተሉ፣ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጠየቁ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ ሐሙስ ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚኒስቴሩን የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሁለቱን ክልሎች በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ባለፈው ዓመት የተፈጠረው ግጭት የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈና ከ700 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ያፈናቀለ መሆኑ የሚታወስ መሆኑን፣ ለዚህ ግጭት መንስዔ ነበሩ ከተባሉት ውስጥ መሠረታዊ የሆነውን የአስተዳደር ወሰን ለማካለል ሚኒስቴሩ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የአስተዳደር ወሰኑን ለማካለል አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ማለትም በ1997 ዓ.ም. የተከናወነው ሕዝበ ውሳኔና የሰላም ስምምነት ሰነዶች ተለይተው መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች መካከል መካሄድ ያለበት የሰላምና የዕርቅ ኮንፍረንስ ሙሉ በሙሉ ተካሂዶ ከተጠናቀቀ፣ የማካለል ሥራውን ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተገምግሞ እንደሚጀመርም ተናግረዋል፡፡

የማካለል ተግባሩን በሰላማዊ ሁኔታ ለመተግበር ይቻል ዘንድም የሁለቱ ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ልዩ ትኩረት እንዲሰጡና የማካለል ተግባሩን የሚያከናውኑ ብቁ አመራሮችን በመወከል እንዲተባበሩ የጠየቁት ሚኒስትሩ፣ ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች የማካለል ተግባሩን በቅርበት ሆነው በልዩ ጥንቃቄ እንዲመሩት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወደ ማካለል ተግባሩ ከመግባቱ በፊት በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ሙሉ በሙሉ መፈታት እንዳለበት፣ በግጭቱ ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች የተፈናቀሉትን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረግና በዘላቂነት ማቋቋም እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ረገድ ባለፉት 11 ወራት የተከናወነው ሥራ ዝቅተኛ መሆኑን ሚኒስትሩ ያቀረቡት ሪፖርት ያሳያል፡፡ የተፈናቀሉትን ዜጎች በተመለከተ በመንግሥት የተሰጠው አቅጣጫ ይኖሩበት ወደነበረው ቀዬ መመለስ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ከ700 ሺሕ በላይ ከሚሆኑት የግጭቱ ሰላባ የሆኑ ተፈናቃዮች መካከል ባለፉት 11 ወራት ውስጥ ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የተደረጉት 227 ሺሕ ያህል ናቸው፡፡ የዘንድሮው ክረምት ወቅት በመግባቱ አስቀድሞ ሁሉንም ተፈናቃዮች ከመጠለያ ካምፖች በማስወጣት ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው የመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ከ500 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በአስከፊ ሁኔታ በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ክረምቱን የማሳለፍ ፈተናን ተጋፍጠዋል፡፡

በተቻለው አቅም የምግብ አቅርቦት ለተፈናቃዮቹ እያደረሰ ቢሆንም በርካታ ነፍሰ ጡሮች፣ አራስ እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት በካምፖቹ መገኘታቸው ችግሩን አሳሳቢ እንዳደረገው፣ በተለይ ደግሞ ለእነዚህ ልዩ እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ተፈናቃዮች መቅረብ የነበረበት የተመጣጠነ አልሚ ምግብ ቢሆንም ይኼንን ማድረግ አለመቻሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ከሶማሌ ከተፈናቀሉት መካከል የተወሰኑ በ11 የኦሮሚያ ከተሞች ለማስፈር የ11 ሺሕ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ስድስት ሺሕ የሚሆኑት ተጠናቀው ለ33 ሺሕ ተፈናቃዮች መከፋፈላቸውን አስረድተዋል፡፡ በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል የቤቶች ግንባታ በማከናወን ላይ መሆኑንና ከዚህ ውስጥ አንድ ሺሕ ቤቶች በአሁኑ ወቅት መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች መካከል ባለፈው ዓመት ባጋጠመው አሰቃቂ ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ አመራሮችንና ግለሰቦችን በመለየት ለሕግ እንዲቀርቡ፣ በሁለት ቡድኖች የተዋቀረ የፌዴራል መርማሪ ቡድን የማጣራት ሥራውን አሁንም እንደቀጠልበት ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ተናግረዋል፡፡

እየተከናወነ ባለው ምርመራም በሰባት መዝገቦች ተጠርጣሪዎች የተለዩ ቢሆንም፣ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዳልተቻለ አስረድተዋል፡፡ በሁለቱም ክልሎች ያሉ አመራሮች ትብብር ለማድረግ  ባለመፈለጋቸው፣ ተጠርጣሪዎቹን በሙሉ በቁጥጥር ሥር ማዋል አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ ተፈናቃዮችን በቀሪው ጊዜ በፍጥነት ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ተግባር ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች የፌዴራል መንግሥት አመራሮች ጋር በመመካከር ተጠርጣሪዎች ለሕግ እንዲቀርቡ አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...