Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመሬት ሊዝ ጨረታ በግርግር ታጅቦ ተከፈተ

የመሬት ሊዝ ጨረታ በግርግር ታጅቦ ተከፈተ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱ ባበለፀገው አዲስ ሶፍትዌር ታግዞ ይፋ ያደረገው 29ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ በግርግር ታጅቦ ተከፈተ፡፡ ጨረታው ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዝቅተኛው 12 ሺሕ ብር ከፍተኛው 100 ሺሕ ብር የመወዳደሪያ ዋጋ ቀርቧል፡፡

       የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ተግባራዊ ያደረገው አዲስ ሶፍትዌር፣ ካሁን በፊት ተግባራዊ ሲሆን የቆየውን የሊዝ ጨረታ ሒደት የቀየረ በመሆኑ፣ ጨረታው በተከፈተበት ወቅት ከፍተኛ ግርግርና መተራመስ ተፈጥሯል፡፡

      በሰባቱ ክፍላተ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡትን 100 ቦታዎች ለማግኘት የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመጨረሻውን ቀን ሳይጠብቁ  መረጃቸውን ቀድመው ቢሮው ባዘጋጀው ኮምፒዩተር ላይ መጫን ይጠበቅባቸው ነበር፡፡

      ነገር ግን በርካታ ተጫራቾች ሰነዳቸውን በመጨረሻው ቀን ይዘው በመቅረባቸው ከፍተኛ ሠልፍ፣ ግርግርና መተራመስ ተፈጥሯል፡፡ ከዚህ ባለፈም ተራቸው ሳይደርስ ወደ ውስጥ ለመግባት የሞከሩ ተጫራቾች እርስ በእርስ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡

      በመጨረሻ ሰዓት ሰነድ ገዝተው ሲፒኦ አሠርተው የቀረቡ መሬት ፈላጊዎች በጨረታው ሳይወዳደሩ ቀርተዋል፡፡

      ለጨረታ የቀረቡት 100 ቦታዎች ከመቶ ካሬ ሜትር እስከ 1‚244 ካሬ ሜትር ድረስ ስፋት አላቸው፡፡ ለጨረታ የቀረቡት ቦታዎች የሚውሉትም ለቢዝነስ፣ ለመኖሪያና ለቅይጥ አገልግሎቶች ነው፡፡

      የከንቲባ ድሪባ ኩማ አስተዳደር በሥልጣን ዘመኑ መጨረሻ ዓመት ላይ 29ኛውን የሊዝ ጨረታ ግንቦት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. አውጥቷል፡፡ ተጫራቾች ያቀረቡት ሰነድ አዲስ በተዘጋጀው ሶፍትዌር ሲሞላ ቆይቶ፣ ማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከፍቷል፡፡

      በወቅቱ ለአንድ ቦታ የተወዳደሩ በሰጡት ዋጋ መሠረት ከአንድ እስከ ሦስት ድረስ የወጡ ተወዳዳሪዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ ይህ አዲስ አሠራር ከዚህ በፊት የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን፣ ጣልቃ ገብነቶችንና ከተጫራቾች ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ይፈታል ተብሏል፡፡

      የመሬት ፈላጊዎች ቁጥር በየጊዜው እያደገ ቢመጣም፣ የከተማ አስተዳደሩ ግን መሬት ለጨረታ የሚያቀርብበት ጊዜም ሆነ ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ የአሁኑ ጨረታ እንኳ ከዘጠኝ ወራት ቆይታ በኃላ የወጣ ነው፡፡ የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ መሬት በብዛትና በፍጥነት እስካልቀረበ ድረስ የመጫረቻ ዋጋው እየጨመረ ይሄዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...