የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገባ ታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ባለፈው ሳምንት የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት የልዑካን ቡድን እንደሚልኩ በይፋ በተናገሩት መሠረት፣ የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተናግረዋል።
ልዑካኑ የሚገቡበትን ትክክለኛውን የተቆረጠ ቀን በቀጣይ እንደሚያሳውቁ አቶ መለስ ተናግረዋል።