የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ከምክትል ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ፡፡
አቶ ሲራጅ በአቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተተክተዋል፡፡
አቶ ሲራጅ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን፣ በቅርቡ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
ትናንት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለቅቀው በቦታቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል መተካታቸው ይታወሳል፡፡