Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርና ሁለት ምክትል ኮሚሽነሮች ተሾሙ

ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርና ሁለት ምክትል ኮሚሽነሮች ተሾሙ

ቀን:

ከሦስት ሳምንታት በፊት ምክንያቱ ሳይገለጽ ከኃላፊነታቸው በተነሱት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይህደጎ ሥዩም ምትክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ ኮሚሽነር ሾሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ በተጠረጠሩበት ‹‹ኃላፊነትን አለመወጣት›› ወንጀል በቁጥጥር ሥር ውለው በታሰሩት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ምትክ፣ ሁለት ምክትል ኮሚሽነሮችን ሾመዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ  ኮሚሽን ኮሚሽነር ተደርገው የተሾሙት ሜጄር ጄኔራል ደግፌ በዲ ናቸው፡፡ በምክትል ኮሚሽነርነት የተሾሙት ደግሞ ረዳት ኮሚሽነር ሐሰን ነጋሽና አቶ ዘለዓለም መንግሥቴ ናቸው፡፡

- Advertisement -

 ሜጄር ጄኔራል ደግፌ በዲ፣ እንዲሁም የረዳት ኮሚሽነር ሐሰን ነጋሽና የአቶ ዘለዓለም መንግሥቴ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...