Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፓርላማው ባቀረበው ወቀሳ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተመደቡ ጥንድ ባለትዳሮችን የማቀያየር ሥራ ተጀመረ

ፓርላማው ባቀረበው ወቀሳ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተመደቡ ጥንድ ባለትዳሮችን የማቀያየር ሥራ ተጀመረ

ቀን:

/ አስቴር ማሞ ከቀረበላቸው አማራጭ ሥራ መልቀቅን እንደመረጡ ታወቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዲፕሎማቶች አመዳደብ ጋር በተያያዘ ከአንድ ወር በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ላይ የሰላ ትችት ከቀረበ በኋላ፣ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየው (/) የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ መጀመራቸውና እስካሁንም በሁለት ኤምባሴዎች የተመደቡ ጥንዶችን መቀየራቸው ታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስካሁን ዕርምጃ ከወሰዱባቸው የምደባ ችግር ከታየባቸው ኤምባሴዎች መካከል በቤልጂየም ብራሰልስና በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሴዎች ላይ መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ተናግረዋል። በካናዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር / አስቴር ማሞ በዲፕሎማትነት ተመድበው አብረዋቸው እየሠሩ ከሚገኙት ባለቤታቸው ጋር መመደባቸው፣ እንዲሁም በቤልጂየም ብራሰልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ እውነቱ ብላታ አብረዋቸው ከሚሠሩት ባለቤታቸው ጋር መመደባቸው፣ ለፓርላማው የቅሬታ ምንጭ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

‹‹የአገራችን የዲፕሎማሲ ሥራዎች ከሚከናወኑባቸው መንገዶች አንዱ፣ ከአገር ጥቅም አኳያና ከስትራቴጂካዊ ወዳጅነት አንፃር በየአገሮች ሚሲዮኖች መክፈት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ለኤምባሲዎች የሚመደቡ አምባሳደሮች ወቅቱ ከሚጠይቀው የዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታ አኳያ፣ የቢዝነስ ዲፕሎማሲውን ለማሳለጥና የአገሪቱን ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ባላቸው ብቃትና ክህሎት መሠረት አድርጎ መሾም ሲገባ፣ አንዳንዶቹ አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶችን ሲመሩ ውጤታማነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባ ነበሩ፡፡ እነዚህን ተሿሚዎች ወይ በጡረታ መሸኘት ወይም ሌላ ቦታ መመደብ ሲገባቸው በአምባሳርነት መመደቡ፣ በዲፕሎማሲ ሥራ የአገርን ጥቅምና ገጽታ ከማስቀደም አኳያ በብቃትና በልምድ ላይ ያልተመሠረተ ሹመትና ምደባ ለምን ይሰጣል፤›› ሲል የዲፕሎማቶችን አመዳደብ የተቸው የፓርላማው የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ‹‹ወቅቱ ከሚጠይቀውና ከዲፕሎማሲ ውጤትና ከዲፕሎማቶች አመዳደብ አዋጁ በተቃራኒ ባልና ሚስት (ጥንዶች) በአንድ ሚሲዮን እንዴት ሊመደቡ እንደቻሉ ማብራሪያ ይሰጥበት፤›› በማለት ጠይቆ ነበር።

በወቅቱ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ የአምባሳደሮቹ ምድባ በትምህርትና በብቃት ላይ ተመሥርቶ ብቻ መሆን አለበት የሚለውን እንደሚቀበሉት ገልጸዋል፡፡ የአምባሳደርነት አመዳደቡ በሁለት ዓይነት መንገድ እንደሚከናወን ያስረዱት ሚኒስትሩ፣ አንደኛው ሚኒስቴሩ ከታች እርከን ጀምሮ የሚያበቃቸውን ሠራተኞች በመምረጥ ሲሆን፣ ሌላው በመንግሥት ከተለያዩ ተቋማት ለሚመጡ ምደባ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን በነበረው አሠራርም ቢሆን በተመደቡ አምባሳደሮች የአገሪቱን ፍላጎት በማሳካት ረገድ የታየ ችግር አልነበረም ብለዋል፡፡ ተመሳሳይ ቅሬታ ከሕዝቡም እየተነሳ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ወደፊት ግን በብቃትና በክህሎት ላይ ተመሥርቶ ግልጽ የሆነ የአሠራር መመርያ እንደሚያስፈልግና ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሠራሩን ለማስፈጸም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የተሿሚ ዲፕሎማቶች ባልና ሚስት አመዳደብን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ በግልጽ የማወቅ መብት ስላለው፣ የሁለቱን ባልና ሚስት ማንነት አሳውቀው ነበር። በዚሁም መሠረት / አስቴር ማሞ ከእነ ባለቤታቸው፣ እንዲሁም አቶ እውነቱ ብላታ ከእነ ባለቤታቸው መሆናቸውን በግልጽ ተናግረው ነበር፡፡ ‹‹ጥያቄ የተነሳባቸው አምባሳደሮች (/ አስቴር እና አቶ እውነቱ) ልምድ የነበራቸው መሆኑ በአምሳደርነት ከመመደባቸው በፊት የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም አምባሳደሮች ከእነ ባለቤቶቻቸው አንድ ቦታ የተመደቡት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በተሰጠ ውሳኔ ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን አንድ ቦታ መሥራት አለባቸው ብለን አናምንም፡፡ ተገቢም አይደለም፡፡ አሁንም ቢሆን ማስተካከል አለብን፤›› ሲሉ በወቅቱ ለፓርላማው መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሚኒስትሩ የሁለቱን ሰዎች ጉዳይ በተመለከተ ጥያቄው በሕዝቡም ውስጥ ያለ በመሆኑ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግሮች ቢኖሩ እንኳ መፍትሔ መኖር ስላለበት፣ በቅርቡ ዕርምጃ በመውሰድ ይስተካከላል በማለት ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡ ይኼንንም ተከትሎ ሰሞኑን ሚኒስትሩ በወሰዱት ዕርምጃ ለተጠቀሱት ጥንድ ዲፕሎማቶች ሁለት ምርጫ እንደቀረበላቸው ምንጮች ገልጸዋል።

የተሰጣቸው አማራጭ በተለያዩ ኤምባሲዎች የሚሰጣቸውን ምደባ መቀበል አልያም ወደ አገር መመለስ ሲሆን፣ በብራሰልስ ኤምባሲ በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ እውነቱና ባለቤታቸው በተለያዩ ኤምባሲዎች ለመመደብ ፈቃደኛ በመሆናቸው አቶ እውነቱ በቤልጂየምአምባሳደርነት እንዲቆዩ፣ ባለቤታቸው ደግሞ አየርላንድ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲዘዋወሩ መወሰኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።

በካናዳ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑት / አስቴር ግን የቀረቡትን አማራጮች ወደ ጎን በመተው፣ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ በመወሰን ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች አስረድተዋል።

በዚህ መሠረት / አስቴር ያቀረቡትን ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደተቀበሉትና ከሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደርነታቸው እንደሚያበቃ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...