Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለአምስት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሠራጭ ማከፋፈያ ማዕከል የእሳት አደጋ ደረሰበት

ለአምስት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሠራጭ ማከፋፈያ ማዕከል የእሳት አደጋ ደረሰበት

ቀን:

የችግሩን መንስዔ የሚያጠና ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩ ተገልጿል

ከአዲስ አበባ በ245 ኪሎ ሜትር ላይ በጅማና በሰኮሩ ከተሞች መካከል በሚገኘው፣ ሰኮሩ በመባል በሚታወቀው ለአምስት ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያሠራጭ ኃይል ማከፋፈያ ማዕከል ላይ የእሳት አደጋ ደረሰበት፡፡  

ማክሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ከንጋቱ 12፡45 ሰዓት ላይ መነሻው ያልታወቀ የእሳት አደጋ ደርሶ፣ በማከፋፈያ ጣቢያው ካሉ አራት ትራንስፎርመሮችና አንድ ሪአክተር (ማካካሻ ዕቃ) መካከል አንዱ በመቃጠሉ በጅማ፣ በአጋሮ፣ በሚዛን፣ በቴፒና በሰኮሩ ከተሞች ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ካህሳይ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የማከፋፈያ ጣቢው ከተገነባ 16 ዓመታት ከታደሰ ደግሞ አሥር ዓመታት እንደሆነው የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው ከግልግል ጊቤ አንድና ሁለት፣ ከወልቂጤና ከጌዶ ኃይል በመቀበል ለተጠቀሱ ከተሞች እንደሚያሠራጭ አክለዋል፡፡

 ከጊቤ ሁለት፣ ሁለቱ ትራንስፎርመሮች እያንዳንዳቸው 250 ሜጋ ቮልቴጅ አምፔር እንደሚያገኙ የጠቆሙት አቶ አበበ፣ የተቃጠለው አንዱ ትራንስፎርመር በመሆኑ ኃይል የተቋረጠባቸው ከተሞች ከቀትር በኋላ በዕለቱ ኃይል እንዲያገኙ መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

የቃጠሎውን ምክንያት የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ ወደ አካባቢው መላኩንና መንስዔው እንደታወቀም ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...