Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየበጎ ፈቃደኞች ረቂቅ ፖሊሲ በዚህ ዓመት ተግባራዊ አይሆንም

የበጎ ፈቃደኞች ረቂቅ ፖሊሲ በዚህ ዓመት ተግባራዊ አይሆንም

ቀን:

ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን እንደሚያሳትፍ የተነገረለት የዘንድሮው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስምሪት በይፋ ተከፍቷል፡፡ በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአዲስ አበባ ብቻ 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ ዓምና በአገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ሥራ በበጎ ፈቃደኞች ተሠርቷል፡፡

     በኢትዮጵያ በየዓመቱ ክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ የሚያስገኘው ውጤትም በዚሁ መጠን እያደገ መጥቷል፡፡ ይኼንን የበጎ ፈቃድ ተግባር በፖሊሲ ለመደገፍ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ረቂቅ ፖሊሲ የማዘጋጀቱን ሥራ የጀመረው 2009 ዓ.ም. ላይ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚሆን በወቅቱ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

     ይሁንና ተጨማሪ አስተያየት እንዲካተትበት በሚል ተግባራዊነቱ ወደ ቀጣዩ ዓመት እንዲሸጋገር ተደርጓል፡፡ የፖሊሲው ዝግጅት የተጠናቀቀ ቢሆንም አጠቃላይ የበጎ ፈቃደኞችን ባካተተ መልኩ እንዲዘጋጅ ሲባል ነው እንዲዘገይ የተወሰነው፡፡ ረቂቅ ፖሊሲው ከወጣቶች በጎ ፈቃድ ፖሊሲ ‹‹የዜጎች በጎ ፈቃድ ፖሊሲ›› በሚል አካታች ስያሜ ተሰይሟል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከሕግ አንፃር አስተያየት እንዲጨምርበት የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዚያም ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ይቀርባል፡፡

     የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥትና የግል ተቋማት ተቀናጅተው እንዲሠሩ ዕድሉን እንደሚፈጥርላቸው የተነገረለት ይህ ረቂቅ፣ በጎ ፈቃደኞች በሥራ ላይ ለሚያጋጥማቸው ከለላ የሚያገኙበትና የሚደገፉበት መንገድ ማካተቱም ታውቋል፡፡ በበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ለሚሰጡ ዜጎች ለሰጡት አገልግሎት እንደ ሥራ ልምድ ሆኖ የሚያገለግል እውቅና እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ነው፡፡

      ፖሊሲው እንደሌሎች አገሮች የበጎ ሥራ ባህል እንዲሆን ያግዛል፡፡ ሰነዱ በዋናነት ወጣቶች በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ በበጎ ፈቃድ ሥራ ላይ ከተሰማሩ የሥራ ልምድ እንዲጻፍላቸው የሚደረግ ሲሆን፣ አስፈላጊው ማበረታቻም እንዲሰጣቸው የሚያደርግ ነው፡፡

      በዓምናው የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ መርሐ ግብር ከ10 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች በ12 የሥራ ዘርፎች ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ የትራፊክ ደንብ ማስከበር፣ አካባቢ ጥበቃ፣ የከተማ ፅዳትና ውበት እንዲሁም የማስተማር አገልግሎት በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በዋናነት ተከናውነዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ ፖሊሲው ወጣቶች በራሳቸው ፈቃድ ለሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ዕውቅና ለመስጠት የሚያገለግል ሲሆን የበጎ ፈቃድ በአገሪቷ እንዲዳብር ለማድረግ ያግዛል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...