Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዘንድሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል ማግኘታቸው ተገለጸ

ዘንድሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል ማግኘታቸው ተገለጸ

ቀን:

በዘንድሮ በጀት ዓመት በገጠር የሚኖሩ፣ 1.8 ሚሊዮን ወጣቶችን በሥራ ለማሠማራት ግብ ተይዞ እስካሁን በተሠሩ ሥራዎች ለ1‚177‚629  ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደ ተፈጠረላቸው የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የዕቅዱን 87.3 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን፣ በዕድሉ የተካተቱ ወጣቶች በማንኛውም ትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡

      ከሰኔ 22 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዳማ የሚካሄደውን አገር አቀፍ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ኤግዚቢሽንና ባዛርን አስመልክተው ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ እንደገለጹት፣ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው መካከል 842‚512 ወጣት ወንዶችና ሴቶች ቋሚ የሥራ ዕድል ሲያገኙ 335‚117 ወጣት ወንዶችና ሴቶች ደግሞ የተሠማሩት በጊዜያዊ የሥራ መስኮች ነው፡፡

      ወጣቶቹ በቋሚነትም ሆነ በጊዜያዊነት የተሠማሩባቸው የሥራ መስኮች ግብርና ነክና ግብርና ነክ ያልሆኑ እንደ ማዕድን ማውጣት በመሳሰሉ የሥራ መስኮች መሆኑን ገልጸው፣ ለወጣቱ ይሄን ያህል የሥራ መስክ ተፈጥሮለታል ወይ? የሚለውን እስከታች ድረስ ወርዶ የማጥራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

      ለአብነት ያህልም በተለይ በደቡብ ክልል ይህንኑ ጉዳይ የሚያጣራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንደገባ፣ ከዕቅዱ አኳያ ሲታይ ግን ወጣቱን ወደ ሥራ የማስገባቱ ሁኔታ አበረታች ተብሎ መወሰድ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡ በአጠቃላይ ምርታማና ውጤታማ ነው ተብሎ ከሚታሰበው የዕድሜ ክልል ውስጥ 16 በመቶ የሆነው ወጣት ገና የሥራ ዕድል እንዳላገኘ ይህም ቁጥር አሁን ካለበት አኳያ እንጂ ውሎ ሲያድር ቁጥሩ እየጨመረ እንደሚሄድ ጥርጥር እንደሌለው አመልክተዋል፡፡

      በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመጀመሪያ በሆነው በዚሁ አገር አቀፍ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ፣ ከሁሉም ክልሎች የተመረጡና በገጠር አካባቢ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ያሳዩ ውጤታማ የሆኑ ከ50 በላይ ኢንተርፕራይዞች እንደሚታደሙ ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት፡፡

      ኢንተርፕራይዞች በኤግዚቢሽኑና በባዛሩ መሳተፋቸው ሥራዎቻቸውን በፖስተርና በተለያየ መንገድ እንዲያቀርቡ፣ በመካከላቸውም የልምድ ልውውጥ፣ እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁና እንዲተሳሰሩ፣ ምርቶቻቸውንም ለአካባቢው ኅብረተሰብ እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ በማድረግ ረገድ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል፡፡

      ከዚህም ሌላ የክልል አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ፓናሎች እንደሚካሄዱ ከሚኒስትር ዴኤታው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የዝግጅቱ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመጀመሪያ የሆነው የዚህ ኤግዚቢሽኖችና ባዛር ዓላማ በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ አጠቃላይ ንቅናቄና ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡

መንግሥት ሥራ አጥነት የሚያስከትለውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ በመገንዘብ በገጠር ለ4.7 ሚሊዮን ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ፣ በገጠር የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ በመለየት በመመዝገብና በማደራጀት ከ2008 ዓ.ም. በፊት ሥራው በክልሎች ላይ በባለቤትነት አቀናጅቶ የሚመራ አካል በአብዛኛው አልነበረም፡፡ በ2008 ዓ.ም. በፌዴራል ደረጃ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ወዲህ በአገር ደረጃ የሥራ ፈላጊዎች መመዝገቢያና መመልመያ ሞዴል መመርያ በማዘጋጀትና ሥልጠና በመስጠት ክልሎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡  

በሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ የተገባና በ2009 በጀት ዓመት አበረታች ውጤት የተገኘ ሲሆን፣ በቀጣይነት በዘርፉ የሚታየውን አመለካከት የክህሎት፣ እንዲሁም የግብዓት ችግር ለመፍታት ከላይኛው እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳትፍ መጠነ ሰፊ የሆነ የሕዝብ ንቅናቄ መፍጠር ተገቢ መሆኑን በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...