Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልአዝማሪነትን ለመታደግ ያለመው ፍለጋ ፌስቲቫል

አዝማሪነትን ለመታደግ ያለመው ፍለጋ ፌስቲቫል

ቀን:

‹‹አዝማሪና ሙያው ማለት ልክ ባህላዊ ባንድ ማለት ነው፤ ድምፃዊውም እሱ ራሱ ነው፤ ደራሲውም እሱ ራሱ ነው፤ ተጫዋቹም እሱ ራሱ ነው፡፡ መሣሪያውንም የሚጫወተው እሱ ራሱ ስለሆነ እንደ አንድ ባንድ ማለት ነው፤›› ብለው አዝማሪነትን በአንድ ወቅት የገለጹት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓባይ የባህልና ልማት ጥናት ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ሙሉ ቀን አንዷለም (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ማዕከሉ በአዝማሪነት ዙሪያ ጥናት ከማካሄዱ ባለፈ የአዝማሪ ጉባዔ በተደጋጋሚ በማካሄድም የታወቀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ የመጀመርያው አዝማሪ ሥራቸው በሸክላ በጀርመን አገር የተቀረፀላቸው አዝማሪ ተሰማ እሸቴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በጀርመን ከዓመታት በፊት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የአዝማሪ ጉባዔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ስሜነህ በትረ ዮሐንስ ባቀረቡት ጥናትና በዶቼቬሌ እንደተገለጸው፣ አዝማሪ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚተገበረው ሙያ ብዙ ነው፡፡ ጊዜ በሄደ ቁጥር የፖለቲካው የኢኮኖሚው የባህል ለውጥ ልዩነቶች በመጡ ቁጥር የአዝማሪዎች የሥራ ድርሻም እንዲሁ በየጊዜው ሲለያይ ነው የመጣው፡፡ በድሮ ጊዜ አዝማሪ የከፋው ሰው፣ አሊያም በአጠቃላይ የኅብረተሰብ ድምፅ ነበር፡፡ የነገሥታትና የገዥዎችም ድምፅም ነበር፡፡ በኅብረተሰብ በገዥዎች መካከል የነበረውን ፍትጊያና የነበሩትን ቅብብሎሽ የሚያሳይ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዘመናዊ ሙዚቃ ባህል ውስጥ አዝማሪዎች ራሳቸውን በዚያ በኩል ቃኝተው ትልቁ ሥፍራን ይዘውና አስተዋጸኦ እያደረጉ ነው ማለት እንደሚቻል ባለሙያው አመልክተዋል፡፡  

አዝማሪነትን በአሁኑ ዘመን በዋና ዋና ከተሞች በምሽት ቤቶች ጎልቶ የሚታይ ቢሆንም፣ በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑ ይወሳል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የሚጠቀሰው የምሽት ቤቶች የነበሩባቸው አካባቢዎች በመልሶ ማልማት መፍረሳቸው ነው፡፡ ለዚህም በማሳያነት የሚቀርበው በርካታ አዝማሪዎች የሚጫወቱበት የነበረው የካዛንቺስ አካባቢ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በካዛንቺስ 17 አዝማሪ ቤቶች ነበሩ፡፡ የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

በልዩ ልዩ ምክንያቶች እየደበዘዘ በመምጣት ላይ የሚገኘውን አዝማሪነትን ለመታደግ ያለመ እንቅስቃሴ ታዋቂው የእስክስታ ባለሙያና የፈንድቃ ባህል ማዕከል ባለቤት መላኩ በላይ ተግባሩን ‹‹ፍለጋ የአዝማሪ ሙዚቃ ፌስቲቫል›› በሚል መጠርያ ማከናወን ጀምሯል፡፡ ከሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ያከናወነው የአዝማሪ ሙዚቃ ፌስቲቫል በርካቶች ታድመውበታል፡፡

እንደ አርቲስት መላኩ አገላለጽ ከጎንደርና ከወሎ፣ ከትግራይና ከኦሮሚያ አካባቢዎች አዝማሪዎች ተሰባስበው ሥራቸውን በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ፣ በጁፒተር ሆቴልና በፈንድቃ ባህል ማዕከል አቅርበዋል፡፡

በባህል ማዕከሉና የባህል ምሽቱ፣ እንዲሁም በተለያዩ አገሮች እያከናወነ ባለው ሙዚቃዊ ተግባሩ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የ50 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ የሆነው መላኩ፣ በቀጣይ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ አንዱ መሣሪያ የአዝማሪ ሙያ መሆኑን ያምናል፡፡ እንደ አንድ የቱሪስት መስህብ ለማድረግም በታላላቅ ሆቴሎች የአዝማሪዎች መሰናዶም ለማቅረብም ዕቅድ አለ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...