ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ከያዙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላሳዩት ለውጥ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሠልፍ እየተደረገ በነበረበት ወቅት የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት ፓርላማው አወገዘ።
የደረሰው ጥቃት በሰው ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ መብት በሆነው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ ጭምር በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባ የወንጀል ተግባር ነው ብሏል።
ፓርላማው ባፀደቀው የውሳኔ ሐሳብም መንግሥት ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ለሕግ እንዲያቀርብ፣ እንዲሁም የፀጥታ አካላትን ሕዝባዊ ስብሰባዎችንና ሠልፎችን የመጠበቅ ብቃታቸውን እንዲገነባ አሳስቧል።