የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ከክልሉ ምክር ቤት ውጪ መሾም እንዲቻል፣ የከተማ አስተዳደሩን ቻርተር የሚያሻሽል ረቂቅ ለፓርላማው ቀረበ ።
ከዚህ በተጨማሪም ዘንድሮ በአገሪቱ በተከሰቱ የፖለቲካ ቀውሶች ምርጫ ማካሄድ ባለመቻሉ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤትና የከተማው ካቢኔ ምርጫ እስከሚደረግ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ የሚፈቅድ ማሻሻያ ከተማዋን ባቋቋመው ቻርተር ላይ እንዲካተት ረቂቅ ቀርቧል።
ፓርላማው ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓም በቀረበው ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ ለሕግና ፍትሕ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ፓርላማው በዛሬው ውሎው የምሕረት አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡