Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናስኳር ኮርፖሬሽን ሜቴክ በያዛቸው ፕሮጀክቶች ላይ ዕርምጃ እንዳይወስድ በከፍተኛ አመራሮች ዛቻና ማስፈራሪያ...

ስኳር ኮርፖሬሽን ሜቴክ በያዛቸው ፕሮጀክቶች ላይ ዕርምጃ እንዳይወስድ በከፍተኛ አመራሮች ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሰው እንደነበር ገለጸ

ቀን:

  • ‹‹እኛን በየመድረኩ ማስጨነቅ ተገቢ አይደለም›› የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የያዛቸውን አንዳንድ የስኳር ፕሮጀክቶች ውል በማቋረጥ ለማስቆም ሲሞከር የፕሮጀክቱን ባለቤት የስኳር ኮርፖሬሽን አመራሮች፣ ‹‹ይህ ማለት ከግንብ ጋር መጋጨት ነው፣ ወዮላችሁ አርፈችሁ ተቀመጡ፤›› የሚሉ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ሲደርሷቸው እንደነበር ስኳር ኮርፖሬሽን  ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ ይፋ አደረጉ።

በፓርላማው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮርፖሬሽኑን ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሰኞ ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በገመገመበት ወቅት ነው ሥራ አስፈጻሚው ይህንን የተናገሩት።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት የስኳር ፕሮጀክቶቹ ለበርካታ ዓመታት መጓተታቸውን በመጥቀስ፣ ኮርፖሬሽኑ እንደተቋም የሚጠበቅበትን ዕርምጃ አለመውሰዱን ተችተዋል።

ለፕሮጀክቶቹ መጓተት መንስዔና ተጠያቂ መሆን የነበረበት አካል እየታወቀ፣ በኮርፖሬሽኑ አመራሮች ላይ ተደጋጋሚ ትችት መሰንዘር በመቀጠሉ የተበሳጩ የሚመስሉት አቶ እንዳወቅ፣ ‹‹ይህ ቋሚ ኮሚቴ ሳይቀር እኛ የገጠመንን ችግር ግልጽ አድርገን ካስረዳነው በኋላ ፕሮጀክቶቹን ተዘዋውሮ ጎብኝቶ በቴሌቪዥን ለሕዝብ በተላለፈ ዜና ሜቴክን ሲያደንቅ አልነበረም ወይ? የኦሞ ኩራዝ ፋብሪካ 80 በመቶ ደረሷል፣ ወደ መገባደዱ ነው ብሎ መግለጫ አልሰጠም ወይ?›› ሲሉ በጥያቄ ኮሚቴውን ወቅሰዋል።

‹‹ከእኛ አቅም በላይ ከሆነ ምንም ማድረግ አንችልም፣›› ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ‹‹ሁሉም በየፊናው አጨብጭቦ ካደነቀ በኋላ እኛን በየመድረኩ ማስጨነቅ ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡ ይህ ማለት ግን የሚመለከተንን ኃላፊነት አንወስድም ማለት አይደለም፤›› ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...