Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

  በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

  ቀን:

  በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ፀደቀ፡፡

  በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአራት ዓመታት በፊት ደርሶ በነበረው የሞት፣ አካል መጉደልና እንግልት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረጉ ጉዞዎችን ማስቆሙ ይታወሳል፡፡

  መንግሥት ቀደም ብሎ ታውጆ የነበረውን የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 632/2001 በአዋጅ ቁጥር 923/2008 በመቀየር፣ ዜጎች ወደ ሳዑዲ ዓረቢያም ሆነ ወደ ተለያዩ አገሮች ለሥራ በሚሄዱበት ወቅት ላኪ ኤጀንሲዎች ሊያደርጉት የሚገባን ጥንቃቄና ለሥራ የሚሄዱትም ዜጎች ማሟላት የሚገባቸውን መሥፈርት ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ አስፈጻሚ የመንግሥት ተቋማትንም ለይቶ በማስቀመጥ በጥር ወር 2010 ዓ.ም. ዕግዱን አንስቶ ነበር፡፡ ለአራት ዓመታት የቆየው ዕግድ ሲነሳ ለሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን መላክ እንደማይቻል፣ በዋናነት የሚመለከተው የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጾ ነበር፡፡

  ሚኒስቴሩ በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት በፓርላማ ባለመፅደቁ፣ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን መላክ እንደማይቻል ቢገልጽም፣ ለ20 ኤጀንሲዎች የሥራ ፈቃድ የሰጠው ግን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዲልኩ ነበር፡፡ ሁለት የሚጣረሱ ነገሮች በሚኒስቴሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች መሰጠቱ የተለያዩ አሉታዎች ሲሰሙ የከረሙ ቢሆንም፣ ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ባለፈው ሳምንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁለትዮሽ ስምምነት አዋጁን በማፅደቁ በሕጉ የተቀመጡትን መሥፈርቶች ያሟሉ ኤጀንሲዎች መላክ ይችላሉ፡፡

  በወቅቱ የሠራተኛና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂና የሳዑዲ ዓረቢያን መንግሥት በመወከል የሠራተኛና ማኅበራዊ ልማት ሚኒስትሩ ሚስተር ዓሊ ናስር አልጋፊስ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ በዚህ ስምምነት ከሳዑዲ ዓረቢያ ተባረው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ተመልሰው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ እንዳይላኩ የኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት የተጠቀሰ ቢሆንም፣ በፓርላማ ውይይት ወቅት ሳይነሳ በዝምታ መታለፉ ሥጋት እንደፈጠረባቸው አስተያየት ሰጪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ሳዑዲ ዓረቢያ በተለይ በርካታ የቤት ሠራተኞችን የምትፈልግ አገር በመሆኗና ሁሉም ሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች የስምምነቱን መፅደቅ ሲጠባበቁ ስለነበር፣ ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደገም መንግሥት ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙና በኩባንያ የተደራጁ ሠራተኛ ተቀባይና አገናኞች ሠራተኞችን እያከራዩ ስለሚጠቀሙባቸው፣ የሁለቱ አገር መንግሥታት ልዩ ትኩረት ሰጥተው በኤምባሲ ተወካዮቻቸው በኩል ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...