Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን ማክስ አውሮፕላን ተረከበ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢ737 ማክስ 8 የተሰኘውን አዲስ አውሮፕላን ሰኞ ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ተረከበ፡፡

  የቦይንግ ኩባንያ አዲስ ምርት የሆነው ማክስ 8 አውሮፕላን ለመካከለኛ ርቀት የሚሆን 160 መቀመጫዎች ያሉት ዘመናዊ አውሮፕላን ነው፡፡ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲያርፍ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያምና ሌሎች ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት አቀባበል አድርገዋል፡፡

  ሊፕ የተሰኘ ሞተር የተገጠመለት ማክስ 8 አውሮፕላን ለመንገደኞች ምቾት ያለው፣ ነዳጅ ቆጣቢ አውሮፕላን እንደሆነ አቶ ወልደ ተናግረዋል፡፡ ከተመሳሳይ አውሮፕላኖች በ15 በመቶ ያነሰ ነዳጅ የሚጠቀም በመሆኑ ወጪ ቆጣቢና ለአካባቢ ተስማሚ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ 30 ቢ737 ማክስ 8 አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ያዘዘ ሲሆን፣ እስከ መስከረም 2011 ዓ.ም. አምስቱ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡ ኢትዮጵያ ከሞሪታኒያ ቀጥላ የማክስ አውሮፕላን ባለቤት በመሆን ከአፍሪካ ሁለተኛዋ አገር ሆናለች፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2025 በሚባለው ዕቅድ የ120 አውሮፕላኖች ባለቤት ለመሆን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ መቶኛውን አውሮፕላን ቦይንግ 787-900 አውሮፕላን ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. መረከቡ ይታወሳል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች