ከ18 የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉበት ዘጠነኛው የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ጨዋታዎች፣ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ከሰኔ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ በአሥር ስፖርቶች ከ500 በላይ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጨዋታዎች ለአንድ ሳምንት ይቆያል፡፡ ፎቶዎቹ የመክፈቻውን ሥነ ሥርዓትና ከተሳታፊዎች መካከል የአዲስ አበባና የቦትስዋና ዩኒቨርሲቲዎች ልዑካንን ያሳያሉ፡፡