Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎችን ተደራሽ ያደረጉት ኅትመቶች

ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎችን ተደራሽ ያደረጉት ኅትመቶች

ቀን:

‹‹ቅርሶች በታሪክ ምስክርነታቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ሳይንሳዊ ምዝገባና ቁጥጥር ማከናወን፣ ከቅርሶች የሚገኙ ጥቅሞች ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማቶች ዕገዛ እንዲያደርጉ ማስቻል፣ ቅርሶችን ማግኘትና ማጥናት›› የሚሉ ዓበይት ዓላማዎችን የያዘው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) ነው፡፡

በቀዳሚዎቹና በአሁኑ መንግሥታት በተለያዩ አደረጃጀቶች ያለፈው ቅጥጥባ ባለፉት አሥር ዓመታት በሐውርታዊት (ባለ ብዙ ብሔረሰብ) የሆነችው የኢትዮጵያ የተለያዩ ባህላዊ ቅርሶች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ በርካታ መጻሕፍትን አሳትሟል፡፡ በተለይ ከ75 በላይ ብሔረሰቦች የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ምዝገባና ቆጠራ (ኢንቬንቶሪ) የሚያሳዩ ተከታታይ ቅጾች ለኅትመት በቅተዋል፡፡

ተቋሙ ከኢንቬንቶሪ ባለፈ ባለፉት ዓመታት የጀመረው በባለሙያዎቹ አማካይነት የየብሔረሰቡ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎችን የተመለከቱ ዝርዝር ጥናቶችን ለኅትመት እያበቃ ነው፡፡ ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በባለሥልጣኑ አዳራሽ ከተመረቁት የጥናትና ምርምር ኅትመት ውጤቶች መካከል በሰባት ብሔረሰቦች ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎች የተሠሩት ይገኙበታል፡፡ እነዚህም የአፋር ተረቶች ይዘትና ተግባራት (በአበበ ኃይሉ)፣ የሶማሌ ብሔረሰብ ባህላዊ የእንጨትና የቆዳ ውጤቶች አሠራርና ጠቀሜታ እና የአርጐባ ብሔረሰብ አፋዊ ትውፊቶችና መገለጫዎች ጥበቃ ጥናት (በእታገኘሁ አስረስ)፣ የጋሞ፣ የኮንሶ፣ የአፋርና የሶማሌ ብሔረሰቦች ማኅበራዊ ክንዋኔዎችና ሥነ ሥርዓቶች ከፊል ገጽታ (በደጀኔ ደንደና)፣ የገዳ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት (በገዛኸኝ ግርማ) ናቸው፡፡

ቅጥጥባ ከሦስት ዓመት ወዲህ በአርኪዎሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መስክ የተሰባሰቡ ጥናታዊ መረጃዎቹን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የኅትመት ብርሃን እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በሁለት ቅጾች የታተሙት በትግራይና በአማራ እንዲሁም በኦሮሚያ፣ ድሬዳዋና ሐረሪ የተሠሩት ጥናቶች Ethiopia Archaeological & paleontological Areas: Amhara and Tigray Regionsእና Ethiopia Archaeological and Paleontological Areas: Oromia, Dire Dawa and Harari Regions ናቸው፡፡

በኅትመት ውጤቶቹ ምረቃ ላይ የተገኙ የቅጥጥባ የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ደምረው ዳኜ እንደተናገሩት፣ የተደረጉት ጥናቶች ‹‹በልዩ ልዩ ዓለም አቀፋዊ፣ አገራዊና አካባቢያዊ ምክንያቶች የተነሳ በመጥፋት ላይ ያሉ የባህሎች መገለጫ የሆኑት የማይዳሰሱ ቅርሶች ተጠንተውና ታትመው ተደራሽ መሆናቸው ቅርሶቹን እንዳይጠፉ ዕገዛ እያደረጉ ነው፡፡

ኅትመቶቹ ጥናቶቹ ለተካሄዱባቸው ብሔረሰቦች፣ ለተማሪዎች፣ ጥናቶቹ ላልተካሄዱባቸው ክልሎችና ለመገናኛ ብዙኃን በመላክ በባህሎች መካከል መተዋወቅ እንዲፈጠር በማድረግ የጎላ ድርሻ እያበረከቱ መገኘታቸውንም ዳይሬክተሩ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኅትመት ውጤቶቹን በስፋት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር በባለሥልጣኑ ውስንነት ያለ መሆኑን የተቹና በቀጣይም መስተካከል እንዳለበት አስተያየትም ተሰጥቶበታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...