Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ልናገርጥንቃቄ የሚያሻው የኤርትራ ጉዳይ

ጥንቃቄ የሚያሻው የኤርትራ ጉዳይ

ቀን:

(ክፍል አንድ)

በጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታየው ብሩህ ተስፋና ለው በተለያየ አቅጣጫ መራራ ትግል የተደረገበት፣ ከፍተኛ የሕይወት የአካልና የሥነ ልቦና መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑን ለማንም ማስታውስ አያሻም፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የዚህ መራራና የረዥም ጊዜ ትግልና የመስዋዕትነት ውጤት ናቸው። የተከፈለውን መስዋዕትነትና ሕዝቡ ላይ ለዓመታት የደረሰውን ግፍ ግምት ውስጥ በማስገባት እየሰጡ ያሉት አመራርም፣ ሕዝቡን ያስደሰተና ሊበረታታም የሚገባው ነው፡፡ ዶ/ር ዓብይ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጀመረው ለውጥ መሠረትና አቅጣጫ እንዲይዝ እየሰጡት ያለው አመራር የብዙዎቻችንን ልብ አሸንፏል። በጎ ሥራቸውም መደገፍ እንዳለበት ምንም ጥርጥር የለኝም። መደገፍ አለበት ሲባል ግን በጭፍን ይደገፉ ማለት ሊሆንም አይገባውም።

- Advertisement -

አንዳንዶች ዶ/ር ዓብይን እንደ ትግሉ ግብ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የመገንባት ግቡን አቅጣጫ እንዳያስቱት ሥጋት አለኝ። ምንም እንኳን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሳቦች እንዲንሸራሸሩ ቢያበረታቱም፣ ከደጋፊዎቻቸው አንዳንዶቹ ግን የሐሳብ ነፃነትን ለመንፈግ ዶ/ር ዓብይን በመቃወምም ሆነ አንዳንድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ዕርምት እንዲያደርጉ ሐሳብ የሚሰጡ ዜጎችን ሲያዋክቡና አላስፈላጊ ታርጋ ሲለጥፉ ይታያሉ። ይህ ታርጋ የመለጠፍና ሰዎችን የማሳቀቅ የወደቀ የፖለቲካ ባህል በአንድ ሌሊት ይቀየራል የሚል እምነት የለኝም። የተለየ ሐሳብ ያላቸው ሰዎች ወከባውን ወይም ታርጋ ልጠፋውን በመፍራት ሐሳባቸውን ከማጋራት ወደ ኋላ እንዳይሉ ላሳስብ እወዳለሁ።

      እስካሁን ድረስ የዶ/ር ዓብይ አመራር ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች ትኩረት ያላገኙ፣ ግን ትኩረትን የሚሹ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ሆነው በተለይ ሁለት ጉዳዮች ትኩረት ሊያገኙ ይገባል ብዬ አምናለሁ። አንደኛው ጊዜ የማይሰጥና አስቸኳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ጥንቃቄና ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ነው። በእኔ እምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጠቃላይ ትኩረታቸው አገር ውስጥ ያለውን በተለያየ አካባቢ ብቅ ጥልቅ እያለ የሚታየውን የጎሳ/ብሔር ግጭት ማስቆም ብቻ ሳይሆን፣ ዘላቂ መፍትሔ ለማግኘትና በአስተማማኝ ሁኔታ የተረጋጋ አገር ለማድረግ ወደ ብሔራዊ ዕርቅ የምንሄድበትን መንገድ ማዘጋጀት ነው።

      ዶ/ር ዓብይ በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱን የሰው ኃይልም ሆነ የገንዘብ ኃይል በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን ግድግዳ በማፍረስ ድልድይ መገንባቱ ላይ ቢያተኩሩ፣ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተም ጉዳዩን የሚያጠና ኮሚቴ ቢያቋቁሙ ይሻላል ባይ ነኝ። የኤርትራንና የኢትዮጵያን የድንበር ጉዳይ አሁን ለምን ለማየት እንዳስፈለገ ለዚህ ጸሐፊ ግልጽ አይደለም። የኤርትራ ጥያቄ ከድንበር መሬት ጥያቄ የዘለለ ብዙ የተውሳሰቡ ነገሮች ያሉበት ነው። ከዚህ ጸሐፊ ግላዊ ሕይወትም አንፃር በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ዛሬ ሁሉ ነገር ቢስተካከል ምርጫው ነው። ጸሐፊው የኤርትራ ተወላጅ ከመሆኑ አንፃር፣ የእነዚህ ሁለት አገሮች ጉዳይ አገራዊ ብቻ ሳይሆን ግላዊም ነው። በኤርትራና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሁም የማያቋርጥ የኢኮኖሚ ትስስር እንዲኖርም ይፈልጋል። ልክ እንደ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኤርትራም ሕዝብ ተስፋ የሚሰጠው መሪ እንዲኖረውና ኤርትራም ውስጥ ‹‹የህዳሴ አብዮት›› እንዲኖር ይፈልጋል። ‹‹የኤርትራ ጥያቄ›› ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኝ እንጂ፣ ጊዜ እየጠበቀ የሚፈነዳ ‹‹ቦምብ›› እንዳይሆንም ነው ይህንን ደወል የሚደውለው።       

ታሪክ እንደሚያስተምረን ብዙ ጊዜ አገሮች በማያቋርጥ ግጭት ውስጥ የሚዋዥቁት በተገቢ ሁኔታ በዘላቂ መፍትሔ መቋጨት የሚገባቸው ጉዳዮች በአግባቡ ባለመቋጨታቸው ነው። ሕዝብን እሳቤ ባላደረገና በተለይም ሕዝብ ያልወከላቸው መንግሥታት ለአጭር ጊዜ የፖለቲካ ጥቅም ሲሉ የሚወስዷቸው ችኩል ዕርምጃዎች፣ የአስተዳደር ወይም የሰዎች የሥልጣን መተካካት ሲፈጠር ቁስሉ እያመረቀዘ ወደ ሌላ ግጭቶች ያመራሉ። በአገራችንም ያየናቸው የተደጋገሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች የእንዲህ ዓይነት ችኩል የፖለቲካ ዕርምጃዎች ውጤቶች ናቸው። ቋሚ በሚመስሉ ግን ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም በሚወሰዱ ውሳኔዎች ለአገራችን የማይሽር ቁስል ሆኖ የቆየው የኤርትራ ጉዳይ ነው።

የኤርትራ ጉዳይ በ1960ዎቹ በተገቢ ሁኔታ በረዥም ዕይታና ዛሬ ሁለት የሆነውን አንድ ሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም  እሳቤ ውስጥ አስገብቶ መፍትሔ ቢያገኝ ኖሮ፣ አገራችን አሁን ያለችበት አረንቋ ውስጥ አትገባም ነበር። ለ60 ዓመታት ገደማ የኤርትራ ጉዳይ ለኤርትራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ራስ ምታት የሆነ፣ ለበርካቶች  ሕይወትና ንብረትም መጥፋት ምክንያት ሆኖ የቆየ ነው። ያ ‹‹ደም የጠማው መሬት›› ግን የእነዚህን ብርቅዬ ልጆች ደም ጠጥቶ የጠገበ አይመስልም፡፡ ሥር ለሰደደው የኤርትራ ችግር አሁንም ለጊዜያዊ የፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የይድረስ ይድረስ ‹‹መፍትሔ የሚመስል››፣ ግን ዘላቂ መፍትሔ የማይሆን ውሳኔ እየተሰጠ ነው። ዛሬም ሕዝብን እሳቤ ውስጥ ያልከተተ ከሕዝብ ጋር ያልመከረና ኑ ‹‹እንታረቅ›› በሚል ቅን ፍላጎት ግን ጊዜን ጠብቆ በሚፈነዳ ቦምብ የተጠቀለለ በመሆኑ፣ በተለይ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ ያሉ ዜጎች አሁን የሚያሰሙት ዋይታ የወደፊቱን ችግር ያመላክታል።

      የኤርትራን ጉዳይ በሰከነና በረጋ መንገድ ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት እንዲችል በተለይ የግንቦት 1990 ዓ.ም. ጦርነት ለምንና በማን እንደተጀመረ መፈተሽ ያስፈልጋል። ዕርቅ የተቀደሰ ነገር ነው፡፡ በዕርቅ ስም ግን ማንም ከኃላፊነት መሸሽ የለበትም። በዚህ  ርዕስ ሥር ጸሐፊው ወደ ኋላ በመሄድ የጦርነቱን መንስዔ ይጎበኛል፡፡ መፍትሔ የሚለውንም ይጠቁማል። አንባቢያንን እንዳያሰለች ጽሑፉ በሁለት ተከፍሏል፡፡ ይህ የመጀመርያው ክፍል ነው።

የኤርትራ ጉዳይ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሕዝብ ላይ ያስከተለው ጉዳት ብዙ ስለተባለለት፣ የዛሬ ትኩረቴ አሁን ለኤርትራ ይሰጣል የተባለው የአንድ ሺሕ ኪሎ ሜትር ገደማ የድንበር መሬት ነው። ብዙዎች ስለግንቦት 1990 ዓ.ም. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ያላቸው ግንዛቤ ውስን ነው ብዬ እገምታለሁ። በተለይም የኤርትራ የፕሮፓጋንዳ ኃይል ‹‹ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 1998 ኤርትራ ላይ የጦርነት ክተት አወጀች›› እየተባለ የሚነገረው ምንም መሠረት የሌለው ዲስኩር ብዙዎችን አሳስቷል፡፡ ዛሬም እያሳሳተ ነው። በተለይም መላውን ኤርትራን በሕገወጥና ሕዝብ ባልመከረበት ሁኔታ ለሻዕቢያ ያስረከበው የመለስ ዜናዊ መራሹ መንግሥት፣ ለምን ከሰባት ዓመታት በኋላ ኤርትራን ለመውረር ፈለገ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ በቂ መልስ የሚሰጥ የለም። ‹ኢትዮጵያ አሰብን ስለፈለገች ነው› ወረራ ያካሄደችው የሚለው የብዙ ኤርትራውያን ወገኖቼ መላምትም ውኃ አይቋጥርም። ከፖለቲካም አንፃር የወያኔ/ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ሳይወድ በግዱ የገባበት ጦርነት፣ በተለይም በወያኔና በሻዕቢያ በአጠቃላይ ደግሞ በትግራይ ሕዝብና በኤርትራ ሕዝብ መካከል ከፍተኛ መቃቃርን የፈጠረና ብዙ የፖለቲካ ዋጋም ያስከፈለ ነው። በብዙዎች እንደተነገረው የጦርነቱ ምንጭ የድንበር ግጭትም አይደለም፣ አልነበረም። አንድ የምዕራባውያን ጋዜጠኛ እንደገለጸው፣ የድንበር ጦርነት ከሆነ ሁለት መላጦች ለማበጠርያ ሲሉ የመገዳደልን ያህል ነው የሆነው።

      እኔ እንደሚገባኝ የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር መከለል የነበረበት ኢዴሞክራሲያዊው ‹‹የኤርትራ›› ሕዝበ ውሳኔ ከመደረጉ በፊት ነበር። አንድ ሕዝብ የራሱ የሆነ አገር ለማቋቋም ሕዝበ ውሳኔ ሲያደርግ፣ ከዚህ ዳር እስከ እዚህ ዳር ያለው መልከዓ ምድር የእኛ ስለሆነ በዚህ መልከዓ ምድር ክልል የራሳችንን ነፃ መንግሥት እንመሠርታለን ከሚል መነሻ ሐሳብ መሆን ነበረበት። ኤርትራ ግን በሕገወጥ መንገድ በተወሰነ ውሳኔ በ1985 ዓ.ም. ‹‹የራሷን መንግሥት›› ስተመሠርት፣ በሻዕቢያ መራሹና በወያኔ መራሹ መንግሥታት መካከል በተደረገ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስምምነት ምክንያት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር በተገቢና ሕጋዊ በሆነ መንገድ አልተካለለም። ለነገሩ እስከ 1989 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ኢትዮጵያ በሻዕቢያ ቁጥጥር ሥር ነበረች ለማለት ይቻላል። በእነዚህ ሁለት ቡድኖች መካከል የኤርትራ ድንበር የት ድረስ ነው? የሚለው ስምምነት ያልተደረሰበት ጉዳይ ስለነበር፣ ይህንን የድንበር ጉዳይ ለመፍታት በሁለቱ መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተቋቋመ የድንበር ጉዳይ ኮሚሽን አማካይነት ድርድር እየተደረገ ነበር። በጣም የሚገርመውና ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነው በኤርትራ የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም የሚመራው የኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ቡድን አዲስ አበባ ከኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ጋር እየተደራደሩ ነበር፡፡ ግንቦት 4 ቀን 1990 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠር የኤርትራ ሠራዊት ታንክና መትረየሱን ይዞ ባድመ ድረስ ገፍቶ መጣ። በወቅቱ የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ነበሩ።

      በተለይ ከ1989 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በሻዕቢያና በወያኔ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተካረረ መምጣት፣ የኤርትራ ወረራ ለሻዕቢያ ተሟጋች የነበሩትን መለስ ዜናዊን መቆሚያ አሳጣቸው። በድርጅታቸው ከፍተኛ አመራሮች በተፈጠረባቸውም ጫና አቶ መለስ የኢትዮጵያን ፓርላማ የአስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ግንቦት 5 ቀን 1990 ዓ.ም.  ሻዕቢያ ወደ ኢትዮጵያ ያዘመተውን ሠራዊቱን በአስቸኳይ እንዲያስወጣ፣ ይህ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያ የተቃጣባትን ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊውን ዕርምጃ እንደምትወስድ ገለጹ። በጊዜው ይህ ብዙዎችን ያደናገረና ሻዕቢያንም ጨምሮ ብዙዎችን ያስደነገጠ መግለጫ ነበር። ሻዕቢያ ወታደሮቹን ሲያዘምት ‹‹ወያኔ ይፈራል የምንፈልገውንም ይፈጽማል›› ከሚል ትዕቢትም ነበር ወረራው የተጀመረው። በወቅቱ በሳዑዲ የነበሩትን ኢሳያስ አፈወርቂን ከምንም ነገር የበለጠ ያናደዳቸው፣ የአቶ መለስ ወራራውን ለሕዝብ ማሳወቃቸው እንደነበር በብዙ የዜና አውታሮች ተዘግቧል። ወረራው ለሕዝብ ይፋ ከሆነ መለስ በሚስጥር ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆነ። ኢትዮጵያ ወደ ጦርነቱ ለመግባትም ፍላጎት አላሳየችም፡፡ ለዚህም ነበር አቶ ኢሳያስን በወቅቱ በአፍሪካ አንድነት ጽሕፈት ቤት በኩልና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ለማስመከር የተሞከረው። የአፍሪካ አንድነት ጽሕፈት ቤት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥታት ሁለቱም አገሮች ከግንቦት 4 ቀን 1990 ዓ.ም. በፊት ይዘዋቸው ወደ ነበሯቸው ግዛቶች እንዲመለሱና ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ። አቶ ኢሳያስ ግን ለዚህ ዝግጁ አልነበሩምና እንቢ አሉ። ጦርነቱ ካልተጀመረ አቶ ኢሳያስ የሥልጣን ዕድሜያቸው እንደሚያጥር ቁልጭ ብሎ ነበር የታያቸው። በባድመ ሰበብ የተጀመረው ጦርነት ለአቶ ኢሳያስ የተንኮል ምሽግ ሆነ፡፡ እስከዛሬ ድረስም ምሽጋቸው ሆኖ እያገለገለ ነው።

      ስለግንቦት 1990 ዓ.ም. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ስናስብ ልንጠይቀው የሚገባ ለምን ጦርነቱ ተጀመረ? ወረራውስ የተጀመረው በማን ነው? የሚል መሆን አለበት። ሁሉም በአንድ ነገር የሚስማማ ይመስለኛል። የኤርትራ ሕዝበ ውኔ ሲደረግ የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር በቅጡ አልተሰመረም። ሌላው ጭብጥ ደግሞ ድንበሩን በተመለከተ ለሁለቱም አገሮች አውዛጋቢ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ለዚህም ነበር የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን የተቋቋመና በሥራም ላይ የነበረው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ከተማማን ቀጣዩ ጥያቄ ማነው ጦሩን መጀመርያ ያንቀሳቀሰው? የሚል ነው። በይፋ የሚታወቀው ግንቦት 4 ቀን 1990 ዓ.ም. በሺች የሚቆጠ የኤርትራ ራዊት ከታንክና መድፉ ጋር በወቅቱ በኢትዮጵያ ሥር ወደ ነበረው ድንበር ዘልቆ መግባቱ ነው። ይህ በቅጡ መጤን ያለበት ጭብጥ ነው። እነዚህን ጭብጦች በቅ ለተመለከተ መልሱ ግልጽ ነው። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ባድመና ሌላው የኢትዮ ኤርትራ ድንበር እውነተኛ ምክንያት ሆኖ ጦርነት እንዳላስነሳ ፀይ የሞቀው ቅ ነው።

      በኢትዮጵያና በኤርትራ በግንቦት 1990 ዓ.ም. ለተጫረው ግጭት ባድመ ሰበብ እንጂ ዋናው ምክንያት አይደለም። በሻዕያ ፊውራሪነት በወያኔና አጋር ድርጅቶቹ (ኦነግን ጨምሮ) ተባባሪነት ደርግ ከሥልጣን ሲወገድ ሻዕያ በኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባኝም ብሎ ኤርትራ ላይ ጊዜያዊ መንግሥት ቢመርትም ራሱን ከኢትዮጵያ ጥገኝነት ሊያላቅቅ ያልቻለ መንግት ነበር። እንዲያውም ብዙ ጊዜ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ፖለቲካዊ አስተዳደራዊበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውኔዎች እንዲወሰኑም አድርጓል። ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ከፍተኛ ‹‹ሥልጣን›› ስለነበረው በተለይ በሻዕያ ትምክህትና ትዕቢት በሚበሳጩና ሻዕያን በሚደግፉ የወያኔ ባለሥልጣናት መከል ከፍተኛ መቃቃርን ረ። በወቅቱ ወያኔ መላውን ገር በቅጡ ባለመቆጣጠሩና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ‹‹ሙሉ ሙሉ›› ተቀባይነት ባለማግኘቱ የሻዕያን ድርጊቶች በዝምታ ከማለፍ ው  የማንገራገር ምልክት አላሳየም። ምንም እንኳን እስከ ሚያዚያ 1985 ዓ.ም. ድረስ ኤርትራም የኢትዮጵያ አካል የነበረች ቢሆንም ከግንቦት 1983 ዓ.ም. እስከ ሚያዚያ 1985 ዓ.ም. ድረ በአንድ ገር ሁለት መንግታት ነበሩ፡ አንድ በአስመራ አንድ በአዲስ አበባ። እነዚህ ሁለት መንግሥታት ሥልጣን የያዙት በሕዝብ ምርጫ ሳይሆን በጠመንጃ አፈሙዝ መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።

      ኤርትራ እንደ ገር የራሷን መንግሥት ካቋቋመች በኋላም የወያኔ መራሹ መንግሥት ኤርትራንም ሆነ የኤርትራን ዜግነት የመረጡ ኤርትራውያንን እንደ ውጭ ገርና እንደ ውጭ ዜጎች ከማየት ይልቅ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ከኢትዮጵያ የበለጠ ተጠቃሚ አንዳንድ ኤርትራውያንም ከኢትዮጵያውያን የበለጠ ተጠቃሚ ሆኑ። ይህ ጉዳይ ያሳሰባቸው ዜጎች የኤርትራውያን የዜግነት ጉዳይ መፍትሔ እንዲያገኝ ቢያሳስቡም የወያኔ መራሹ መንግሥት እነዚህን ዜጎች ‹‹ፀረ ሰላም›› የሚል ታርጋ እየለጠፈ ቁም ስቅላቸውን አሳይቷቸዋል። የኢትዮጵያ መንግት አንድ የአሜሪካ ዶላር በስድስት የኢትዮጵያ ብር ሲመነዝርርትራ መንግት ደግሞ በ7.25 ብር ይመነዝር ነበር (ለማስታወስ በወቅቱ ኤርትራ የምትጠቀመው የኢትዮጵያን ብር ነበር)። ይህም ማለት ኢትዮጵያ ማኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ የምታገኘው ኤርትራ ነበረች።

በጣም የሚገርመው በመላው ዓለም የሚገኙ የኤርትራ መንግት ኤምባሲዎችና የኮሙዩኒቲ ማበራት የብር ምንዘራው ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነበር። ይህ የማንም ገር የማይፈቅደው እንዲያውም በአንድ ገር ላይ የተደረገ የኢኮኖሚ ጦርነት ተደርጎ ነው የሚቆጠረው። በአንድ ወቅት ይህ ጸሐፊ ከአምባሳደር ብርሃ ገብረ ክርስቶስ ጋር ባደረው ውይይት ጃፓን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ብታሳንስ (Devalue) አሜሪካ ያለምንም ማመንታት ጃፓንን በጦር አውሮፕላን ትደበድባለች በማለት፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ የሰነዘረችው ‹‹የኢኮኖሚ ጦርነት›› ክብደቱን ለማሳየት ሞክሯል። በዚያን ወቅት ኤርትራ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባት እህሎች ከሚልኩ አገሮች ተርታ ውስጥም ተመድባ ነበር። ብዙዎቹ እነዚህ ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ማስገባት የነበረባቸው ምርቶች ኤርትራ በሚታተም የውሸት የኢትዮጵያ ብር ነበር የተሸመቱትና ለዓለም ገበያ የቀረቡት። በዚህ የውሸት ብር በመቶ ሺዎች በሚቆጠር ኩንታል ጤፍ ለኤርትራ መንግሥት ወኪሎች የሸጡ ገበሬዎችም ለኪሳራ ተዳርገው፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት አቤቱታ ሲያቀርቡ የደረሰባቸው ወከባና ማስፈራርያ ነበር። ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ የፈለገውን የሚያስርበትና የሚፈታበት፣ እንዲሁም የሚገድልበት ሙሉ ሥልጣን ነበረው። በዚያን ጊዜ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ጥቅም ግን ቋሚም ሆነ ተጠሪም መንግሥት አልነበረም።

      ለሻዕቢያ መራሹ መንግሥት የሕዝብ እሮሮ ምኑም አልነበረም። ሻዕቢያ የመንን ሲወር ታንኩ፣ የጦር አውሮፕላኑ፣ መድፍና ጠመንጃው ከኢትዮጵያ ተቸረው። ብዙም ሳይቆይ አቶ ኢሳያስ የዚያን መሣሪያ አፈሙዝ ወደ ኢትዮጵያ አዞረ፡፡ ‹‹ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ›› ዓይነት ነው። ሻዕቢያ ለኤርትራ ሕዝብ ፍትሐዊ አስተዳደር አመጣለሁ፣ ሕዝቡን ከጭቆና ነፃ አወጣለሁና ኤርትራ የዜጎች መብት የተከበረባት አገር ትሆናለች እያለ ለዓመታት ቢለፍፍም፣ የገባውን ቃል ለመተግበር ባለመቻሉ በተለይም የኤርትራ ምሁራን አገሪቱ በሕግ እንድትተዳደር ሕገ መንግሥት እንዲኖር ግፊት በማድረጋቸው አቶ ኢሳያስ የማይወጡበት አረንቋ ውስጥ ገቡ። ለዚህ ግፊት መልስ ለመስጠትም በዶ/ር በረከት ሀብተ ሥላሴ የተመራ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ተቋቋመ፡፡ ኮሚሽኑም ሥራውን አጠናቆ ረቂቁን በ1988 ዓ.ም. ለኤርትራ መንግሥት አስረከበ። ረቂቁ ሕገ መንግሥት ብዙ ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን የያዘ ከመሆኑም በላይ፣ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ሥልጣንና የአስተዳደር ጊዜ የገደበ በመሆኑ ለአቶ ኢሳያስ ሊዋጥላቸው አልቻለም። ለሕገ መንግሥት ጊዜው አይደለም በማለትም አቶ ኢሳያስ ረቂቁን ጠረጴዛቸው ውስጥ ቆለፉበት።

      ለኤርትራ ሕዝብ ከአቅማቸው በላይ ቃል የገቡትንና አገር የማስተዳደርና የመምራት ተረስቶ፣ ምንም ብቃት የሌላቸው የሻዕቢያ መሪዎች አገሪቱን ከተለያዩ የጎረቤት አገሮች ጋር እያናቆሩ በሕዝቡ ላይ ሥጋትን ፈጠሩ። በተለይም የብሔራዊ ውትድርና ሥልጠናና ርዝመቱ፣ በሃይማኖቶች ላይ የተደረገው ተፅዕኖ፣ እንዲሁም ኢዴሞክራሲያዊ የሆነው አገዛዝ ሕዝቡ ለሚያነሳው ተገቢ ጥያቄ ምላሹ እስር ሆነ። የአሰብን ወደብ አጠቃቀም በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ውዝግብ ተጀመረ። እያረጀ የመጣው የአሰብ ወደብ በኢትዮጵያ መንግሥት በሚሊዮኖች ዶላር በሚቆጠር የገንዘብ ፍሰት እንዲታደስ፣ ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ መንግሥት ትዕዛዝ መሰል ጥያቄ አቀረበ። ጥያቄው በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ አከራካሪ ሲሆንና ቶሎ ምላሽ ባለመሰጠቱ ሻዕቢያ የአሰብ ወደብን የሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን ማዋከብ ጀመረ፡፡ የዚህ ዓላማም በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት ለመፍጠር ነበር። በኢትዮጵያ ነጋዴዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚቀርበው አቤቱታ እየበረከተ በመምጣቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ነጋዴዎች የጂቡቲን ወደብ እንደ አማራጭ እንዲጠቀሙ ፈቀደ። የነጋዴው ማኅበረሰብ የጂቡቲን ወደብ ለመጠቀም በነቂስ ተነሳ። ይህ ሻዕቢያ መቼም ይሆናል ብሎ ያልጠበቀው ነበር። ኢትዮጵያ አሰብን እንደ ወደብ ካልተጠቀመች በኤርትራ ኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣው ጫና ቁልጭ ብሎ ታየ። በኅዳር 1990 ዓ.ም. የኤርትራ የንግድ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን አዲስ አበባ ላይ በመሰብሰብ፣ ነጋዴው የአሰብ ወደብን እንዲጠቀም የወደቡም አሠራር እንደሚሻሻል ቃል በመግባት ተማፀኑ። ወደ ኋላ የሚመለስ ነጋዴ ግን አልተገኘም። ይህ በሻዕቢያና በወያኔ መካከል ሌላ ክፍተት ፈጠረ።

      ከስብሰባው ከጥቂት ቀናት በኋላም ሻዕቢያ የኤርትራን ሕጋዊ ብር ናቅፋን ሲያስተዋውቅ፣ ማንም ባልጠበቀውና በዚህ ጸሐፊ እምነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ትልቅ ዕርምጃ በመውሰድ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ወዲያው የኢትዮጵያን ትልልቅ ኖት ብሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ በመቀየርና በኤርትራና በኢትዮጵያ ድንበር የሚደረጉ ግብይቶች በዶላር እንዲሆኑ በመወሰን፣ ብዙ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችን ያስደመመ ሻዕቢያን እጅግ በጣም ያበሳጨ ዕርምጃ ተወሰደ። ሻዕቢያ በውጭ ምንዛሪ ሊቀይረው የነበረ ኤርትራ ውስጥ ሲት የነበረ ከአራት ቢሊዮን በላይ የሆነ የኢትዮጵያ ብር ወረቀት ሆነ። ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ የመቀየያ የጊዜ ገደብ በማለፉ ሻዕያ ኤርትራ ውስጥ የሚንቀሳቀሰውን የኢትዮጵያን ብር ከሕዝብ አሰባስቦ ለመቀየር አልቻለም። በተለይ የኢትዮጵያ የመገበያያ ብር መቀየርና ድንበር ላይ ግብይት በዶላር እንዲሆን መወሰን ወያኔ ከሻዕያ መንጋጋ ለመውጣቱ ትልቅ ምልክት ሆነ።

      በኋላም እንደተረዳነው በተለይ በአፋር አካባቢ በ1989 ዓ.ም. በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ግጭቶች ነበሩ፡፡ ግጭቶቹም በአቶ መለስና አቶ ኢሳያስ ፈጣን ጣልቃ ገብነት መብረድ ችለዋ። ይህ ሲሆን ደግሞ ወያኔ ውስጥ ሻዕያን በሚደግፉና በሚቃወሙ ይሎች መከል ውዝግቡ እየባሰና እየጨመረ መጣ። እንደ የሎም ገብሩ አራትና ዬ አብርሃ ዓይነቶቹ ኢትዮጵያ ኤርትራን መደጎም እንድታቆም ሻዕኢትዮጵያ ላይ የሚይሳየው ማለብኝነት እንዲገታ ይሟገቱም እንደነበር ከወያኔ ክፍፍል በኋላ ብዙ ተብሎለታል። ሻዕያ ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተቀባይነት ያላገኘና የተጠላ ነ ከሚል እምነት በመነሳት በኢኮኖሚ እያሽቆለቆለች የመጣውን የሻዕያን ኤርትራ ለመታደግግንቦት 4 ቀን 1990 ዓ.ም. አቶ ኢሳያስ ራዊቱን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ላከ። ልብ መደረግ ያለበት በስብት ኤፍሬም የሚመራው ቡድን አዲስ አበባ ስለድንበር እየተወያየ ነው የኤርትራ ራዊት ድንበር ገፍቶ የመጣው። ይህ ወረራ ለሕዝብ ይፋ ከሆነ በኋላም የኤርትራ መንግሥት ለወረራው ምክንያት ብሎ የሰጠው ድንበር ላይ በነዋሪዎች መከል ግጭት ተነስቶ የኢትዮጵያ ሚሊሽያ ኤርትራውያን ገበሬዎችን በማፈናቀሉይህ ማፈናቀል እንዲቆም የላክናቸው ሽማግሌዎች (አንድ የኤርትራ ኮሎኔልን ጨምሮ) በሚሊሻዎቹ ተገደሉብን ለዚህም ነው ራዊታችንን ወደ ድንበር ያንቀሳቀስነው የሚል ነው።

ርትራ መንግ በአንድ በኩል በገር ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲኖር ረቀቀው ሕገ መንግ በሥራ ላይ ይዋልየዜጎች ሞክራሲያዊ መብት ይከበር የሚለው ግፊት ማየሉና በሌላ በኩል ደግሞ ለኤርትራ ሕዝብ የተገባው ‹‹የኢኮኖሚ ምር›› ቃል ውን ማድረግ የሚችልበት አቅጣጫው ስለጠፋውበሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ብቃት የሌላቸውና የጎደላቸው ከመሆን አልፈው ‹‹ተዋግተን ያመጣነውን ለማንም አንሰጥም›› በሚል ደዌ ታመው ሥልጣን ለሕዝብ ለመስጠት ስላልፈለጉ የድንበር ጦርነቱ ጥሩ መደበ ምሽግ ሆናቸው። ምንእንኳን የኤርትራ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት የጀመሩበት ምክንያት ‹‹የድንበር ጉዳይ›› ነው ብለው በአደባባይ ቢስብኩምበግል ግን ጥያቄው የኢኮኖሚና ሥልጣንን ርትራ ሕዝብ ካለማስረከብ ጋር የተያያዘ መሆኑን አይደብቁም።

      በሰኔ 1990 ዓ.ም. ‹‹ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ኢንተርናሽናል ስተዲስ›› የተባለው ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ተቋም ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፣ በስብሰባው ከተገኙ ጥቂት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መካከል አንዱ ይህ ጸሐፊ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ አምባሳደሮችና የኤምባሲ ሹማምንት የተገኙ ሲሆን፣ ይህ ጸሐፊ ለኤርትራ አምባሳደር ያነሳው ጥያቄ፣ ‹‹ወደ ጦርነት ገባንበት የምትሉትን ምክንያት እውነት ነው ብዬ ልቀበልና ሽማግሌዎቻችሁ ስለተገደሉ ታንክና ወታደር ይዞ መምጣቱ ተገቢ ነው ወይ? ታንክና ሠራዊት ከማዝመታችሁ በፊት ጉዳዩን ለአፍሪካ ኅብረት ወይም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለምን አላቀረባችሁም? ዛሬ የምትጠይቁት መሬት ቢሰጣችሁ ጦርነቱን እንደማታቆሙ በእርግጠኝነት መናገር እችላላሁ፡፡ የኤርትራ ጥያቄ የመሬት ሳይሆን የኢኮኖሚ አይደለም ወይ?›› የሚል ጥያቄ በማቅረቤ፣ በአምባሳደሩና በሹማምንቱ የታየው ከፍተኛ ቁጣ ነበር። በተለይም ለቁጣው ማየል ምክንያት የሆነው ጥያቄው የኤርትራ ተወላጅ ነኝ ከሚል ሰው መቅረቡ ነበር። ከስብሰባው ለዕረፍት ስወጣ ይህ ጸሐፊ ከኤርትራ ሹማምንት ጋር ያደረገው ሙግት የተሞላበት ‹‹ውይይት››፣ በማያሻማ ሁኔታ በኤርትራ ባለሥልጣናት የተረጋገጠለት የኤርትራ ሠራዊት ወደ ‹‹ኢትዮጵያ ድንበር›› ዘልቆ የገባው ለመሬት ሳይሆን፣ ወያኔ ‹‹የኤርትራን አንገት በኢኮኖሚ ጠምዝዞ ኤርትራን ለማንበርከክ ይሠራል›› ከሚል እምነትና ሥጋት የመነጨ መሆኑን ነው። (በሚቀጥለው ሳምንት ቀሪው ክፍል ይቀጥላል)

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...