Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ ለማስነሳትና ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማ እንደሚገኙ ታወቀ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን ፍረጃ ለማስነሳትና ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማ እንደሚገኙ ታወቀ

ቀን:

የመንግሥታቸውን ዕቅድ በማብራራት የ2011 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ይፀድቃል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ፍረጃው ተነስቶላቸው በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉና ለአገራዊ መግባባት ሲባል በወንጀል ለሚፈለጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምሕረት እንዲደረግላቸው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ፣ ፓርላማው አርብ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚወያይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ታወቀ።

በዕለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥታቸውን ቀጣይ በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅዶች፣ ማስፈጸሚያና ለፓርላማው በቀረበ ረቂቅ በጀት ላይ ማብራርያ በመስጠት እንደሚያፀድቁ ምንጮች ገልጸዋል።

በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ሦስት የፖለቲካ ድርጅቶች ከአሸባሪነት ፍረጃ ነፃ እንዲደረጉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቅዳሜ ሰኔ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. መወሰኑ ይታወሳል። ፓርላማው ከሰባት ዓመታት በፊት በመንግሥት የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ የአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)፣ እንዲሁም አልቃይዳና አልሸባብን አሸባሪ ድርጅቶች በማለት መፈረጁ አይዘነጋም።

ይህ ፍረጃ ከሦስቱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ እንዲነሳና በወንጀል የሚፈለጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምሕረት እንዲያገኙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ መወሰኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሁለቱንም ውሳኔዎች በሕጉ መሠረት በማፅደቅ ፍረጃውን የማንሳት እንዲሁም ምሕረት የማድረግ የመጨረሻ ሥልጣን ያለው ፓርላማው በመሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐሙስ በፓርላማው ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2011 በጀት ዓመት የመንግሥትን ዕቅድ በማብራራት የቀረበውን ረቂቅ በጀት ለማፀደቅ በፓርላማ የመገኘት ግዴታ ያለባቸው በመሆኑ አጋጣሚውን ይጠቀሙበታል እንጂ፣ የአሸባሪነት ፍረጃውን ለማስነሳትም ሆነ ምሕረት ለማሰጠት በፓርላማው እንዲገኙ የሕግ ሥነ ሥርዓት አያስገድዳቸውም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...