Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት የማረሚያ ቤቶች አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አነሳ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት የማረሚያ ቤቶች አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አነሳ

ቀን:

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሦስት የማረሚያ ቤት አመራሮችን ከኃላፊነታቸው አንስቶ በምትካቸው አዳዲስ አመራሮችን ሾመ፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከኃላፊነታቸው ያነሳቸው የማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ረጋሳ፣ የሰው ሀብትና መሠረታዊ ፍላጎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌትዬ ደጀኔና የጥበቃና ተሃድሶ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ወልደ ሩፋኤል ናቸው፡፡

አመራሮቹ ከኃላፊነታቸው ሊነሱ የቻሉበት ምክንያት በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ፍርደኞችና የክስ ሒደታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተከሳሾች፣ በማረሚያ ቤቶቹ ባላቸው ቆይታ ሰብዓዊ ክብራቸውን የሚጥሱ በደሎች የተፈጸመባቸው መሆኑን በመግለጻቸውና በተደረገው ማጣራትም ድርጊቱ በመረጋገጡ ነው፡፡ በመሆኑም ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ኃላፊዎቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት አልቻሉም በማለት ከኃላፊነታቸው አንስቷቸዋል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተነሱት አመራሮች ምትክ፣ ሌሎች አዳዲስ አመራሮችን ሾሟል፡፡ በዚሁም መሠረት አቶ ጀማል አባስ የማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር፣ ረዳት ኮሚሽነር ያረጋል አደመ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት የፋይናንስና የሰው ሀብት ዘርፍ ኃላፊ፣ ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት የተሃድሶ ዘርፍ ኃላፊ፣ ኮማንደር ሙላት ዓለሙ በምክትል ዳይሬክተርነት የጥበቃ ደኅንነት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም ኮማንደር ወንድሙ ጫማ በምክትል ዳይሬክተርነት የመሠረታዊ ፍላጎት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...