አስፈላጊ ግብዓቶች
- 2 ኩባያ የስኳር ድንች ተቀቅሎ የተላጠ
- 3 እንቁላል፣ አስኳሉና ዞፉ የተለየ
- 1 ኩባያ ወተት
- 4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- ½ ኩባያ ስኳር
- 3 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- 1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ልጣጭ የተከተፈ
- ¾ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ
- 1 ፔስትሪ
አሠራር
- ቅቤና ስኳሩን አደባልቆ በደንብ እስኪያያዝ ድረስ በሹካ ማሸት፡፡
- የሎሚ ጭማቂ፣ የሎሚ ልጣጭ፣ የእንቁላል አስኳል፣ ቀረፋ፣ ስኳር፣ ድንችና ወተት አደባልቆ በተራ ቁጥር 1 ከተዘጋጀው የቅቤ ድብልቅ ጋር ማዋሃድ፡፡
- የእንቁላሉን ዞፍ በወፍራሙ መምታት፡፡
- በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተዘጋጀውን በአንድ ላይ አደባልቆ ፔስትሪው ላይ መገልበጥ፡፡
- ሙቀቱ 425 ዲግሪ ፋራንሃይት በሆነ ምድጃ ለአሥር ደቂቃ ማቆየት፡፡ ከዚያም ሙቀቱን ወደ 350 ዲግሪ ፋራንሃይት ዝቅ አድርጎ ለአርባ ደቂቃ ማብሰል፡፡
ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)