Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ በአዲስ አበባ ዓርብ ይጀመራል

የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ በአዲስ አበባ ዓርብ ይጀመራል

ቀን:

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን 19ኛው የምሥራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ኅብረት (አመሰያ) ጉባዔ ከሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ 11 ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታወቀች፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጉባዔው “በእግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ሕያው ብዝኃነት ሰብአዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት ለምሥራቅ አፍሪካ አገሮች” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ  ይካሄዳል። የመክፈቻው ሥነ ሥርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ የመንግሥት ከፍተኛ ሹማምንትና የሮም ፖፕ ፍራንሲስ ተወካይ በሚገኙበት ይከፈታል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን በግልጽ የሚዳስሱ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት የአመሰያ ጉባዔ፣ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት በምሥራቅ አፍሪካ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለምታከናውናቸው ሐዋርያዊና ማኅበራዊ ሥራዎች ብዝኃነትን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ እንዲቻል አቅጣጫ የምታሳይበትና ጳጳሳት ልዩ ልዩ ውሳኔዎች የሚያስተላልፉበትም ጭምር እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ወጣቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል የሚሏቸውን ጉዳዮች ለውይይት ያቀርባሉ የመፍትሔ ሐሳቦችንም ያካፍላሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ በመግለጫዋ የምሥራቅ አፍሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ለጉባዔያቸው መሪ ቃል አድርገው የመረጡትበትን ምክንያት ስትገልጽ፣ ‹‹ሁላችንንም እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረን ሲሆን ልዩነታችንም ከፈጣሪያችን ያገኘነው ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ልዩነት መነሻ በማድረግ በተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ ክፍሎች ግጭቶች ተነስተው ንብረት ይወድማል፣ ብዙዎች ይፈናቀላሉ፣ የብዙዎች ሕይወት ይጠፋል፡፡ ልዩነታችን እርስ በእርስ የምንማማርበት እሴታችን እንደመሆን ፈንታ የጥላቻ ምክንያት ሲሆን ይታያል፤›› ብላለች፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ሰላማዊ አንድነት እንዲኖር ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን   ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር፣ እንዲሁም ከመንግሥታትና ከአፍሪካ ኅብረት ጋርም በመተባበር በጋራ እንዴት መሥራት እንዳለባት በዚህ ጉባዔ እንደሚመክሩ አስታውቃለች፡፡

300 በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ጉባኤ በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ሲካሄድ፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያኗ አጋጣሚውን በመጠቀም አገሪቱ ያላትን የሰላምና የመከባበር ባህል ከሌሎች ወንድሞና እህቶች ጋር ለመካፈል የምትጠቀምበት አጋጣሚ መሆኑን ተገንዝባ፣ የአስተናጋጅ ኃላፊነቱን መቀበሏን የቤተ ክርስቲያኒቷ ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ / አባ ሥዩም ፍራንሷ ቀደም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

አመሰያ በሚለው ምኅፃረ ቃል በሰፊው በሚታወቀው ኅብረት ውስጥ ዘጠኝ አገሮች ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማላዊና ዛምቢያ አባላት  ሲሆኑ፣ ጂቡቲና ሶማሊያ ተባባሪ አባላት ናቸው፡፡

አመሰያ ከሦስት ዓመት በፊት በማላዊ ዋና ከተማ ባካሄደው 18ኛው ጉባዔ፣ ኅብረቱን በፕሬዚዳንትነት ለአራት ዓመት እንዲመሩኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስን መምረጡ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...