Monday, October 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ለመወያየት ወደ አሜሪካ ያቀናሉ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በመጪው ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ አሜሪካ በመጓዝ፣ ከኢትዮጵያዊያንና ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ብቻ እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብርቱካን አያኖ አስታውቀዋል፡፡

የውይይቱ ዋና ዓላማ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ እየተካሄደ ባላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል በመሆን፣ በአገሪቱ ልማትና አንድነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተሳታፊ በመሆን ራሳቸውን ጠቅመው አገራቸውንም እንዲጠቅሙ ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

‹‹ግንቡን እናፍርስ ድልዩን እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል በዋሽንግተን ዲሲና በሎስ አንጀለስ ከተሞች ለማድረግ ከታቀዱት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በተጨማሪ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካላትም ጋር የተለያዩ የጎንዮሽ ውይይቶችም እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉዞ የሚያስተባብር ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፣ ኮሚቴውን ወ/ሮ ብርቱካን ይመሩታል፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም የኮሚቴው ጸሐፊ ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በእነዚህ ሕዝባዊ ስብሰባዎች የፖለቲካ አመለካከት፣ ሃይማኖት፣ ብሔር፣ ፆታና የመሳሰሉት ሳይለያዩዋቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን፣ ሚኒስትር ደኤታዋ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከ25 ዓመታት በላይ ተለያይተው የሚገኙትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለማስታረቅና ወደ አንድነት ለማምጣት በ30 በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን አስታራቂ ሽማግሌዎች የተቋቋመው ኮሚቴ ስብሰባ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የዕርቀ ሰላሙን ሒደት በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሥፍራው በመገኘት ለዕርቀ ሰላሙ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች