በቅርቡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው የተሾሙት ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ከግል ባንኮች ፕሬዚዳንቶች ጋር አንድ ለአንድ ውይይት እያደረጉ እንዳሉ የሪፖርተር ምንጮች አስታወቁ፡፡
ለረዥም ጊዜ በማዕከላዊ ባንክ ገዥነት ያገለገሉትን አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉን በመተካት የተሾሙት አዲሱ ገዥ፣ ለእያንዳንዱ ባንክ ከእርሳቸው ጋር መቼ እንደሚወያይ የሚገልጽ መርሃ ግብር መላካቸውም ታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ገዥው፣ ከፕሬዚዳንቶቹ ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ባንኮቹ አሉብን በሚሏቸው ችግሮች ዙሪያ እንደሆነ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡