Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየድል በዓል የአልማዝ ኢዮቤልዩ በልዩ ዝግጅት ሊከበር ነው

የድል በዓል የአልማዝ ኢዮቤልዩ በልዩ ዝግጅት ሊከበር ነው

ቀን:

ኢትዮጵያ የኢጣሊያ ፋሺስት ወራሪ ሠራዊትን ድል የመታችበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በመጪው ሚያዝያ ወር ይከበራል፡፡ ከ1928 ዓ.ም. እስከ 1933 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት አገሪቱን የተቆጣጠረውን የፋሺስት ሠራዊት ለማስወገድ እርመኛ አርበኞች በዱር በገደሉና በየከተማው ካደረጉት ተጋድሎ በተጨማሪ በወረራው ዘመን በስደት የነበረውም ትግል ይጠቀሳል፡፡

የአልማዝ ኢዮቤልዩ እንዳለፉት ዓመታት በዋነኛነት ሚያዝያ 27 ቀን ላይ ብቻ የሚከበር ብቻ ሳይሆን ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አስታውቋል፡፡ እንደ ማኅበሩ መግለጫ፣ በኢዮቤልዩው ጀግኖች አርበኞች ለአገርና ለነፃነት መከበር የከፈሉት አኩሪ መስዋዕትነት በክብር ይዘከራል፡፡ በልማት አርበኝነቱና በሰላም አስከባሪነቱ መስክ ኃላፊነት ለተጣለበት ታሪክ ተረካቢ ትውልድም የአደራ መልዕክት ይተላለፋል፡፡

ማኅበሩ አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ (የአርበኞች ግንብ) አጠገብ መንግሥት በነፃ በፈቀደለት ቦታ ፓርክና ሙዚየምን ጨምሮ በቀጣይ ለሚተገብረው ቋሚ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያም በሞባይል ስልክ በ8400 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) ቶምቦላ ሎተሪ አዘጋጅቶ እያከናወነ ነው፡፡

የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አድርገዋል፡፡ ታላቅ በዓልነቱን ታሳቢ አድርጎ መንግሥት ከማኅበሩ የቀረበለትን አጀንዳ ተቀብሎ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚከታተሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

‹‹በ75ኛው ዓመት በዓል ላይ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና ታላላቅ ሰዎች እንዲመጡ እንፈልጋለን፤›› የሚሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ ይህንንም መሻታችን አዲስ ግንኙነት ፈጥረን የወደፊቷን ኢትዮጵያ የሰላምና የፍቅር ኢትዮጵያዊነትን የምናሳይበት ብለን ስለምናምን ነው ብለዋል፡፡ ‹‹መንግሥት ይቀበለናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ ሰላም ላይ የሚያተኩር ነውና፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የአርበኞች ማኅበር በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ዝርጋታ ፕሮጀክት ምክንያት ከቦታው ተነስቶ የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ተመልሶ በተተከለበት አጋጣሚ፣ ኢሉባቡር ጎሬ ላይ በፋሺስት ኢጣሊያ ሰማዕት የሆኑት የአቡነ ሚካኤል ሐውልትም በከተማው አደባባይ እንዲቆም ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ ልጅ ዳንኤል ጆቴ እንዳወሱት፣ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ሁሉ የአቡነ ሚካኤልም ሐውልት ኢሉባቡር በተገደሉበት ቦታ ሐውልታቸው መቆም አለበት፡፡ ‹‹ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳይሆን አደባባይ ተሰጥቷቸው የክብር ቦታቸውን እንዲያገኙ እየጠየቅን ነው፡፡ መንግሥት ይህንን አይቶ መስመር እንደሚያሲዝልን አምናለሁ፤›› ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፋሺስት ኢጣሊያ አዲስ አበባን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም. ይዞ በአምስተኛው ዓመት ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም. ድል መመታቱና ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም (1923-1967) በድል አድራጊነት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ አፄ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት መስቀላቸውና ማውለብለባቸው አይዘነጋም፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...