Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊመንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ እጥረት እንደምትመታ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ እጥረት እንደምትመታ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

ቀን:

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር)፣ በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች ለውኃ ፕሮጀክቶች የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ተገቢውን ትኩረት በመንፈጋቸው ከአንድ ዓመት በኋላ ከተማው ከፍተኛ የውኃ እጥረት ሊያጋጥመው እንደሚችል አስጠነቀቁ፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ይህን የተናገሩት ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት በተመረቀበት ወቅት ነው፡፡ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ካልወሰነ በስተቀር አዲስ አበባ በውኃ ችግር ትመታለች ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ የከተማውን የውኃ አቅርቦት ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም በቀን አንድ ሚሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ማመንጨት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል ሰቢሉና ገርቢ ግድቦች፣ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት፣ ኮዬ ፈጬ፣ ኖርዝ አያት ፋንታ፣ ሰበታ-ሆለታ የጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፕሮጀክቶችና የውኃ እጥረት በሚታይባቸው የተለያዩ የከተማው ኪስ ቦታዎች የሚቆፈሩ ጥልቅ የውኃ ጉድጓዶች ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እነዚህ ፕሮጀክቶች በተለይም የሲቪል ሥራቸው የተገባደደ ቢሆንም ለኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ የሚሆን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመጥፋቱ፣ በፕሮጀክቶች የወሰን ማስከበር በሚፈለገው ፍጥነት ባለመካሄዱና በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት እየተጓተቱ በመሆናቸው ከተማው ከፍተኛ የውኃ እጥረት እንደሚያጋጥመው ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፕሮጀክት ለ700 ሺሕ ሕዝብ የሚበቃ በቀን ከ68 ሺሕ ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውኃ ምርት ተገኝቷል፡፡ ይህ ፕሮጀክት መንግሥት በመደበው 150 ሚሊዮን ብር በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ በአገር ውስጥና በውጭ ኮንትራክተሮች የሲቪል ሥራው ተካሂዷል፡፡

‹‹የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎችን ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመጥፋቱ፣ በኅዳር 2010 ዓ.ም. ወደ ሥርጭት መግባት የነበረበት ፕሮጀክት ሳይገባ ቀርቷል፤›› በማለት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ በማምረት እስከ አንድ ሚሊዮን ለሚደርስ ሕዝብ አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለው የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በተለይ የጥልቅ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ የተገኘው ውኃ ወደ አገልግሎት ለማስገባት፣ በውጭና በአገር ውስጥ ተቋራጮች የሚከናወነው ሥራ የውጭ ምንዛሪ ችግር ማጋጠሙ ይታወቃል፡፡ በዚህም ምክንያት ለቀረበ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ የግዥ መመርያው አይፈቅድም በመባሉ፣ የግንባታ ሒደቱ ተቋርጦ በድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ መወሰኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡

‹‹ባንኮች በተደጋጋሚ የውጭ ምንዛሪ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው ሥራው እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል፤›› በማለት የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹በአገራችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ያጋጠመ መሆኑ ቢታወቅም፣ ባንኮች እየበጣጠሱ መሠረታዊ ላልሆኑ ዕቃዎች ግዥ ለተለያዩ ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሪ ከመስጠት ይልቅ ከሁሉም ነገር በላይ ለሆኑ፣ እያንዳንዱን ቤት ለሚያንኳኩ ውኃን ለመሰሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ትኩረት መስጠት ነበረባቸው፤›› በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡

የከተማውን የውኃ እጥረት ከመሠረቱ የሚያስተካክሉ ፕሮጀክቶች ከባለሥልጣኑ አቅም በላይ በመሆናቸው፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ለሕዝብ ሲሉ ኃላፊነት ወስደው በልዩ ሁኔታ ውሳኔ ባለመስጠታቸው ምክንያት መሰረዛቸው እጅግ የሚያስቆጭና የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ ‹‹መንግሥት አሁንም ጣልቃ ገብቶ፣ በከተማው የሚመጣውን ቀውስ አጢኖ፣ በድጋሚ ወደ ጨረታ መግባት ሊያመጣ የሚችለውን የማይገመት አደጋ ከግምት በማስገባት ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል፤›› ሲሉ ችግሩን አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለአዲስ አበባ ከተማ በቀን 866,540 ሜትር ኪዩብ ውኃ የሚያስፈልጋት ቢሆንም፣ ውኃ የሚያመነጩ ጣቢያዎች በቀን 618 ሺሕ ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም አላቸው፡፡ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ልዩነት ቢኖርም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የቀረበው ውኃ በሙሉ ለተጠቃሚዎች እንደማይደርስ ተገልጿል፡፡

የአንዳንድ የውኃ ጉድጓዶች ምርት በመቀነሱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ የከፋ ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የውኃ አቅርቦቱ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም የመብራትና መስመር ችግር ካላጋጠመ በቀን 525 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ከተማዋ ማግኘት እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...