Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያውያን ባለውለተኞች በስፖርት ሲዘከሩ

ኢትዮጵያውያን ባለውለተኞች በስፖርት ሲዘከሩ

ቀን:

በኢትዮጵያ በተለያዩ የክንውን ታሪክ ውስጥ አይረሴ ገድለኞችና ባለውለተኞች ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡ ከስፖርተኞች ባሻገርም ለስፖርቱ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ኖረው፣ በሕይወት ያሉና ያለፉ አንጋፋ ታሪከኞች የኢትዮጵያ ጌጦች መሆናቸውን የሚዘክር ስፖርታዊ ክንውን እሑድ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ፣ አትሌቲክስ እንዲሁም ብስክሌትና ሌሎችም ስፖርቶች ሲዘከሩ ስማቸው አብሮ የሚነሳ ጉምቱዎች በርካቶች ናቸው፡፡ የመድኃኔዓለም ስፖርት ማኅበር ስፖርታዊ የክንውን ፕሮግራም በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት ከግንቦት 3 እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሜዳ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ሜዳ፣ በብሔራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚና በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው የእግር ኳስ፣ እንዲሁም በአትሌቲክሱ የ15 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ባለፈው እሑድ አዲስ አበባ ስታዲየም ሲጠናቀቅ በሕይወት ያሉ የኢትዮጵያ ባለውለተኞች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

እንደ አዘጋጁ አቶ አብርሃም ካሳሁን ከሆነ፣ ስፖርታዊ ክንውኑ መታሰቢያነት በዋናነት በሕይወት ያሉና የሌሉ ቀደምትና አሁንም በሥራ ላይ የሚገኙትን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት በስፖርቱ አቶ ከበደ መታፈሪያ፣ አሠልጣኝ ንጉሤ ሮባ፣ ሻምበል ማሞ ወልዴ፣ አቶ አቤሴሎም ይሕደጎ፣ ኢንስትራክተር መንግሥቱ ወርቁ፣ አስቻለው ደሴ፣ አሠልጣኝ ንጉሴ ገብሬ፣ የመጀመርያው የኦሊምፒክ ብስክሌተኛ ገረመው ደምቦባና ሌሎችም ሲሆኑ፣ ከስፖርቱ ውጪ ደግሞ፣ የኢትዮጵያ ታላቁ ግድብ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስመኘው በቀለ (አንጂነር)፣ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የበላይ ጠባቂ አቶ ወርቅሸት በቀለና ሌሎችም በስፖርታዊ ክንውኑ ከታሰቡት እንደሚጠቀሱ የፕሮግራሙ አዘጋጅ አቶ አብርሃም ካሳሁን ይናገራሉ፡፡

በቀድሞ  የአገር ውስጥና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች መካከል፣ ከግንቦት 3 እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ሲከናወን በቆየው የእግር ኳስ ውድድር የቀድሞ ኪራይ ቤቶችና የቀድሞ የታደሰ ፕሮጀክት ቡድኖች ለዋንጫ ደርሰው በኪራይ ቤቶች አሸናፊነት መጠናቀቁም ታውቋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ለባለውለተኞቹ በተዘጋጀው  የጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ውድድር ደግሞ በታደሰ ፕሮጀክትና ልጆቹ አሸናፊነት መጠናቀቁ አዘጋጁ አቶ አብርሃም ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን መነሻውን የቀድሞ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ቄራ አካባቢ ከሚገኘው የአቶ አቤሴሎም ይሕደጎ ድርጅት ከሆነው ቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ አድርጎ በሁለት ዙር መድረሻውን አዲስ አበባ ስታዲየም ያደረገ የ15 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተከናውኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...