Friday, June 14, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2011 በጀት ዓመት 44.7 ቢሊዮን ብር የታክስ ገቢ አቀደ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ ገቢ 44.7 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱን ይፋ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን ዳይሬክተር አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ እንደተናገሩት፣ 22.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ገቢ ከቀጥታ ታክስ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ 11 ቢሊዮን ብር ደግሞ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች የሚሰበሰብ ነው፡፡

እንደ አቶ ሺሰማ ገለጻ፣ ይህ ዕቅድ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ3.9 ቢሊዮን ብር ወይም የ17 በመቶ ዕድገት ያሳያል፡፡

በከተማዋ ያሉ በአብዛኛው ድርጅት ካልሆኑ ታክስ ከፋዮች ባለሥልጣኑ ማሻሻያ ማድረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ካሁን ቀደም ታክስ ለማስላት ጥቅም ላይ የሚውለው የ365 የግብር የሥራ ቀናት እንደ ንግድ ባህርያቱ መሠረት ከ150 እስከ 300 ቀናት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

ትንንሽ የንግድ ተቋማት የሚከፍሉት አሥር በመቶ የተርን ኦቨር ታክስ (ቲኦቲ) ወደ አምስት በመቶ እንዲቀንስም ተደርጓል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 193, 227 የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች