Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹ዳምጠው›› እና መንገድ ገንቢዎቹ ከ78 ዓመታት በፊት

‹‹ዳምጠው›› እና መንገድ ገንቢዎቹ ከ78 ዓመታት በፊት

ቀን:

የሕዝብ ግጥሞች

ያቺን ቀጪን ኩታ ሆዴ እንዲያ ሲወዳት፣

አላዋቂ ሰፊ ባላጨማደዳት።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

•••

አትወደኝም ያልሺኝ፣ የጠላኹሽ የታል፤

አንድ አንጀት ነበረኝ፣ ተኝተሽበታል።

•••

እናትን አትውደድ ለዘጠኝ ወር ዕድሜ፤

እኔ አርግዤኻለኹ እስከ ዘላለሜ።

•••

ኧረ! ተዉ ሰዎች፣ እንደ ራስ ነው ፍርድ፤

ጭምት ያሳብዳል ዛርና መውደድ።

•••

መውደድ አይገድልም ሲሉ፣

ቄሱን ጦለበው አሉ።

•••

ሲታመሙ ታሞ፣ ሲሞቱ ካልሞቱ፣

በምን ይታወቃል ሰው ወዳጅነቱ፣

•••

መድረኩን ስዘልቀው፣ ደከመኝ እላለኹ፤

ወንዙን ስሻገረው፣ ልቀመጥ እላለኹ፤

ገመገሙን ስዞር፣ መልሱኝ እላለኹ፤

ዐደራ እማይሰጧት ዕቃ ረስቻለኹ።

  • እ.ነ.ሥ. እንዳሰባሰበችው

****

የፖለቲካ ቀን

የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርግ የዋለው ነስሩ በጣም ድክም ብሎት ማታ ወደ ቤት ገባ፡፡ በዚህ ላይ እቤት የጠበቀችው ሚስቱ ስለ ዕለት ውሎው ትጠይቀዋለች፡፡

‹‹ፍቅሬ ዛሬ ቅስቀሳህ እንዴት ነበር?››

‹‹ደህና እንደሆነ እገምታለሁ!›› አለ በረጅሙ እየተነፈሰ ‹‹ሆኖም በርካቶች ንግግሬን የተረዱት አይመስለኝም›› አላት

‹‹እንዴት እንደዚህ ልትገምት ቻልክ?››

‹‹ምክንያቱም እኔም በርካታ ንግግሮቼ አልገቡኝም ነበር፡፡››

  • መሃመድ ጣሃ ‹‹ነስሩዲን እና ቀልዶቹ›› (1998)

**********

ብቸኝነት እውነታው ምንድን ነው?

ብዙ ጓደኞች ቢኖሩህም እንኳ ብቸኝነት ሊሰማህ ይችላል።

‹‹እኔ ጓደኞቼን እወዳቸዋለሁ፤ አንዳንድ ጊዜ ግን እኔ ለእነሱ የሚሰማኝን ያህል እንደማይወዱኝ ይሰማኛል። ጓደኞችህ እንደማይወዱህ ወይም ቦታ እንደማይሰጡህ የሚሰማህ ከሆነ በብዙ ጓደኞች ብትከበብም እንኳ በብቸኝነት ስሜት መዋጥህ አይቀርም።›› አን

የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚ ብትሆንም እንኳ ብቸኝነት ሊሰማህ ይችላል።

‹‹አንዳንድ ሰዎች ከጓደኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት አሻንጉሊቶችን መሰብሰብ የሚወዱ ሰዎች ከሚያደርጉት ነገር ጋር ይመሳሰላል። እነዚህ ሰዎች ብዙ አሻንጉሊቶች ቢኖሯቸውም አሻንጉሊቶቻቸው፣ እንደሚወደዱ እንዲሰማቸው ሊያደርጉ እንደማይችሉ የታወቀ ነው። ኢንተርኔት ላይ ከምታገኛቸው ጓደኞችህ ጋር ያለህ ግንኙነት የጠበቀ ካልሆነ ሕይወት ከሌላቸው ከእነዚህ አሻንጉሊቶች የተሻለ ነገር ሊያደርጉልህ አይችሉም።›› ኢሌይን

ከሌሎች ጋር የጽሑፍ መልእክት በመለዋወጥ ብዙ ጊዜ ብታሳልፍም እንኳ ብቸኝነት ሊሰማህ ይችላል።

‹‹አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነት ይሰማህና መልእክት ተልኮልህ እንደሆነ ለማየት አሥር ጊዜ ስልክህን ትመለከታለህ። ማንም መልእክት እንዳልተላከልህ ስትመለከት የበለጠ ብቸኝነት ይሰማሃል!›› ሴሪና

ለሌሎች ጥሩ ነገር ብታደርግም እንኳ ብቸኝነት ሊሰማህ ይችላል።

‹‹ለጓደኞቼ ብዙ ነገር አደርጋለሁ፤ እነሱ ግን ለእኔ እንደዚያ እንደማያደርጉ ይሰማኛል። ለእነሱ መልካም በማድረጌ ባልቆጭም አንዴም እንኳ በምላሹ ደግነት እንዳላሳዩኝ ሳስብ ትንሽ ይከፋኛል።›› ሪቻርድ

ዋናው ነጥብ፦ ዞሮ ዞሮ ብቸኝነት ከአመለካከታችን ጋር የተያያዘ ነው። ጃኔት የተባለች ወጣት እንዲህ ብላለች፦ ‹‹ብቸኝነት ከውስጥህ የሚመጣ ነገር እንጂ ከውጭ ባሉ ነገሮች ላይ የተመካ አይደለም።

  • ጄደብሊው ዶትኦርግ

**********

ቻይና የውጭ አገር ስም ያላቸውን ሠፈሮች ስያሜ ልትቀይር ነው

በቻይና በተለይም የውጭ አገር ስም የተሰጣቸውን የመኖሪያ አካባቢዎች ስያሜ እንዲቀየር የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማክሰኞ ዕለት ማሳወቃቸውን ዥንዋ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ እንደገለጹት በአገሪቱ የመንገዶችና የድልድዮች፣ የሕንፃዎችና የሠፈሮች ስም ወጥነት በጎደለው መልኩ በውጭ አገር ስም የተሰየመ ነው፡፡ ከዚህም በላይ የአገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ማኅበራዊና ባህላዊ እሴቶችን የሚያንቋሽሹ ስያሜዎችም አሉ፡፡ ቻይና በጣም እየሠለጠነችና ለቀሪው ዓለም ክፍት እየሆነች በሔደች ቁጥር ደግሞ እነዚህ ስሞች በጣም እየታወቁ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ችግር ስያሜዎቹ ወጥነት እንዲኖራቸው በማድረግ መፍታት ያስፈልጋል፡፡

ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ የቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግም የተባለው ችግር በስፋት ይታይበታል፡፡

***********

በጩኸት ገበያ ለመሳብ የሞከሩ የመጠጥ ቤት አስተናጋጆች ተፈረደባቸው

በዑጋንዳ ካምፓላ የሁለት መጠጥ ቤቶች አስተናጋጆቹ ፉሪዳ ናኪቡሌ እና ናኩላቤይ አለን፣ በየበራቸው ሆነው በመጮህና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ደንበኛ ለመሳብ በመሞከር ክስ ተመሥርቶባቸው ጥፋተኛ መባላቸውን ዘኒው ቪዥን ዘግቧል፡፡

ሁለቱ አስተናጋጆች ወደ ፍርድ ቤት የተወሰዱት በከፍተኛ ጩኸት የአካባቢውን ነዋሪ ሰላም በመንሳታቸው ነው፡፡ ጥፋተኛ የተባሉት ሁለቱ አስተናጋጆች ፍርድ ቤቱ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ተማፅነዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም አስተናጋጆቹ ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ሕግ የመጣስ ሪከርድ የሌለባቸው በመሆኑ ቅጣታቸው እንዲቀልላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

በዚህም መሠረት አንደኛዋ አስተናጋጅ የአንድ ወር እሥራት ሲጣልባት ሌላኛዋ ደግሞ በተመሳሳይ የአንድ ወር እሥራትና 40 ሺሕ የዑጋንዳ ሽልንግ ተቀጥታለች፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...