Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያና ሩሲያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር ለማድረግ ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሩሲያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር ለማድረግ ተስማሙ

ቀን:

ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ጉብኝት ያደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ ከሩሲያ ጋር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመተባበር ተስማማ፡፡ ልዑኩ ሁለቱ አገሮች በሰላምና በፀጥታ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረክ ስለሚያደርጉት ትብብሮችም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይቷል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓብይ አሕመድ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግሩም ዓባይ የተካተቱበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ደመቀ፣ ከምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ የሩሲያ ልዩ ተወካዩ ሚካኤል ቦግዳሮቭ ጋር በተለያዩ የአገራቱ ግንኙነቶች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያና የሩሲያ ፖለቲካዊ ግንኙነት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር እንዲሁም ትምህርትና ፈጠራ ከተወያዩባቸው ጉዳዮች ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አቶ ደመቀ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተላከውን ደብዳቤም አስረክበዋል፡፡

ከሩሲያ ኤምባሲ የተላከው የፕሬስ መግለጫ እንደሚያሳየው አቶ ደመቀ የሩሲያን የትምህርትና ሳይንስ ሚኒስትር፣ የፕሬዚዳንቱን ልዩ የሳይንስና የትምህርት አማካሪ እንዲሁም የተለያዩ የሩሲያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ኃላፊዎችንም አነጋግረዋል፡፡

የኢትዮጵያው ልዑክ ንድፈ ሐሳባዊና ተግባራዊ ምርምር የሚካሄድበትን በዱብና የሚገኘውን የሩሲያ ኒውክሌር ምርምር ኢንስቲትዩት ጎብኝቷል፡፡ በልዑኩ ጉብኝት ወቅት አምባሳደር ዓብይ አህመድ ከአገሪቱ ኒውክሌር ኃይል ኮርፖሬሽን ትብብር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ኒኮላይ ስፓሰሲ ጋር ተነጋግረዋል፡፡

በሌላ በኩልም ልዑኩ በሞስኮና አካባቢዋ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተወሰኑ ዞኖች፣ ወረዳዎችና በአማራ ክልል ከቅማንት ማኅበረሰብ የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዘው የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማረጋጋት መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመሆን የወሰዳቸውን ዕርምጃዎችም በውይይቱም የተነሱ ጉዳዮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...